ወደዝዋይ ማረሚያ ቤት ተዘዋውረው ከነበሩት እስረኞች መካከል 300 የሚሆኑት ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት መመለሳቸው ተዘገበ

Posted on Oct 15, 2016

ወደዝዋይ ማረሚያ ቤት ተዘዋውረው ከነበሩት እስረኞች መካከል 300 የሚሆኑት ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት መመለሳቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 5/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተነሳውን እሳት ቃጠሎ ተከትሎ ወደ ዝዋይ እና ሸዋሮቢት እንዲዘዋወሩ ከተደረጉት እስረኞች መካከል በዝዋይ ማረሚያ ቤት ተወስደው ከነበሩት እስረኞች መካከል 300 የሚሆኑትን ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲመለሱ መደረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በጥቅምት 2/2009 ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እስረኞቹን የመለሷቸው ሲሆን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በዞን 2 ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል፡፡ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት የተመለሱትን እስረኞች በዞን ሁለት ውስጥ በልዩ ጥበቃ ስር እንዲታሰሩ መደረጉ የታወቀ ሲሆን ከማንም ታሳሪም ሆነ ከቤተሰባቸው ጋር እንዳይገናኙ መደረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ታሳሪዎቹ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መዘዋወራቸውን የሰሙ ቤተሰቦች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለመጠየቅ በዛሬው እለት ሄደው የነበረ ቢሆንም መጠይቅ አትችሉም እንደተባሉ ታውቋል፡፡ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በነበረው በሶስት ዞን ውስጥ ታስረው የነበሩ እስረኞች በአሁኑ ወቅት በዞን 1 ውስጥ በአንድ ላይ ተፋፍነው ታስረው እንደሚገኙ ከዚህ ቀደም መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ከቤተሰብ ጋርም 15 ደቂቃ ባልበለጡ ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ እንዲገናኙ እየተደረገ መሆኑ ተገልፆል፡፡ ከዝዋይ ወደ ቂሊንጦ የተመለሱት ታሳሪዎች ቤተሰቦች ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ቤተሰበቸውን መጠየቅ እንዲችሉ ጥያቄ አቅርበው የነበረ...

መንግስት የህዝቡን ተቃውሞ ከአቅም በላይ ስለሆነበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

Posted on Oct 9, 2016

መንግስት የህዝቡን ተቃውሞ ከአቅም በላይ ስለሆነበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 29/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

የኢትዬጲያ መንግስት ባለፈው ሳምንት የኢሬቻ በዓልን ለማክበር በወጡ በሚሊዬን በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ በወሰደው የሃይል እርምጃ በርካቶች ህይወታቸውን ማለፉን ተከትሎ ከባድ ቁጣ በህዝቡ በመቀስቀሱ በኦሮሚያ ክልል በሰፈነው ከባድ ተቃውሞ የተነሳ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ሃይለማርያም ደሳለኝ በዛሬው እለት ማስታወቁ ተዘግቧል፡፡

የሀገሪቱን ሰላም የማይሹ ኃይሎች ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር በሀገሪቱ ህዝብ ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ላይ የደቀኑትን ከፍተኛ ስጋት ለመቀልበስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከትንናንት ጀምሮ የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በይፋ ለህዝቡ በሚዲያ ያስታወቁ ሲሆን የዚህ መሰሉ አስኳይ ጊዜ አዋጅ ሲታወጅ በ 25 አመት ውስጥ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

መንግስት በህዝቡ ዘንድ የገጠመው ከባድ ተቃውሞ ብዙሃኑን ቢጨፈጭፍም ሊቆም ባለመቻሉ ተጨማሪ የሃይል እርምጃዎችን ለመውሰድ ያመቸው ዘንድ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀ ሲሆን ይህ ያስቸኳይ ጊዜም ለ 6 ወራት የሚቆይ መሆኑ ተገልፆል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የገበሬውን መሬት ነጥቀው ፋብሪካ የገነቡ እና የመንግስት ንብረቶች መውደማቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህን የህዝቡን ቁጣም የውጪ ሃይሎች ተግባር ነው በሚል በመንግስት ፕሮፖጋንዳ እየተሰራ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ተቃውሞ በሚካሄድባቸው ቦታዎች ሁልጊዜም ያስቸኳይ ጊዜ...

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ   በዲላ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች 4 መስጂዶች መቃጠላቸው ተዘገበ

Posted on Oct 8, 2016

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ

በዲላ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች 4 መስጂዶች መቃጠላቸው ተዘገበ

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 28/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በደቡብ ክልል በጌድኦ ዞን በዲላ ከተማ እና አጎራባች ከተሞች የሚገኙ 4 መስጂዶች በእሳት መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

መስጂዶቹ የተቃጠሉት በጌድኦ ብሄረሰብ በሆኑ የፕሮቴስታንት እምንት ተከታዬች ሲሆን በዞኑ የሚገኙ የጉራጌ፣የስልጤ እና የአማራ ተወላጆች ንብረት በእሳት መውደሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡

የዚህ መሰሉ አሳዛኝ ድርጊት በይርጋጨፌ፣በዲላ፣ በወናጎ፣ በጨለለቅቱ/ኮቸሬ/ እና በሌሎችም በጌድኦ ዞን ስር በሚገኙ ከተሞች እየተፈመ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የንግድ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች በእሳት እንዲወድሙ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

የጌድኦ ዞን በብዛት የፕሮቴስታንት እምነነት ተከታዬች ሲሆኑ የሌላ ብሄር ተወላጆችን ንብረት ከማውደም አልፎ የእምነት ተቋማትን ወደማውደም መሸጋገራቸው ተዘግቧል፡፡

በዲላ ከተማ 2 መስጂዶች መቃጠላቸው የተዘገበ ሲሆን በዲላ ዙሪያ በሚገኘው በቱምቲቻ ወረዳ አንድ መስጂድ እንዲሁም ከዲላ 15 ኪሎትር ርቀት ላይ በምትገኘው በዎናጎ ከተማም አንድ መስጂድ በጌዶኦ ፕሮቴስታንቶች መቃጠሉ ን የአካባው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በኮፌ የጋሞ መስጂድ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የዋናው ካምፓስ መስጂድ በእሳት መቃጠሉ የተዘገበ ሲሆን በወረዳው ብቸኛ የነበረው በቱምቲቻ ቀበሌ የሚገኘው መስጂድም...

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የሞባይል ኢተርኔት ለ 2ኛ ቀን በመንግስት እንደተዘጉ መሆኑ ታወቀ

Posted on Oct 6, 2016

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የሞባይል ኢተርኔት ለ 2ኛ ቀን በመንግስት እንደተዘጉ መሆኑ ታወቀ

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 26/2009

۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩

መንግስት በቢሾፍቱ የኢሬቻ በኣል ለማክበር በተሰበሰቡ በሚሊዬን በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የሃይል እርምጃ በመውሰድ በንፁሃን ላይ ባደረሰው ግድያ ከፍተኛ ቁጣ በህዝቡ ዘንድ በመቀስቀሱ የሰጋው መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ ተቃውሞ በህዝቡ መሃል በመቀስቀሱ መረጃ ለህዝቡ እንዳይዳረስ ለማፈን በሚል ከትላንት እሮብ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ታውቋል፡፡

ዛሬ ለሁለተኛ ቀን የሞባይል ኢንተርኔት ተዘግቶ የዋለ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጥ የህዝቡን ቁጣ እና ተቃውሞ ለማቀዛቀዝ መንግስት እየጣረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎት ቢቋረጥም በተለያዩ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከተሞች ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃወሞ እየተካሄደ መሆኑ የተዘገበ ሲሆን የመንግስት ታጣቂ ሃይሎችም ወደ ህዝቡ በመተኮስ ዜጎችን እየገደሉ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በጅማ ፣በሃዋሳ እና በአዳማ ዩኒቨርሰቲ የሚገኙ ተማሪዎችም ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸው የታወቀ ሲሆን በጅማ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የኦሮሚያ እና የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች በጋራ ትግላቸውን ለማድረግ መወያየታቸውን እና መስማማታቸው ተዘግቧል፡፡

መንግስት አሁንም የሃይል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን...

በወልዲያው ሰላም መድረሳ ለመጀመሪየ ጊዜ የዲን ትምህርት ቀርቶ አካዳሚክ ትምህርት ብቻ እንዲሰጥ መደረጉ ታወቀ

Posted on Oct 6, 2016

በወልዲያው ሰላም መድረሳ ለመጀመሪየ ጊዜ የዲን ትምህርት ቀርቶ አካዳሚክ ትምህርት ብቻ እንዲሰጥ መደረጉ ታወቀ

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 26/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ ከአወልያ ቀጥሎ ግዙፉ የሙስሊሙ ተቋም የነበረው የወልዲያ መስጂዶች እና ትምህርት ቤቶች ማዕከል በህገ ወጡ መጅሊስ እና በመንግስት ለአህባሾች እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ ተቋሙን የማዳከም ስራ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በማዕከሉ ስር የነበረውን የሰላም መድረሳ የዲን ትምህርት መስጠት እንዲያቆም በማድረግ የአካዳሚክ ትምህርት ብቻ እንዲሰጥ መደረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከ 1965 ጀምሮ የወልዲያን ሙስሊም ማህበረሰብ ሲያገለግል የቆየው ይህ ተቋም በርካታ ምሁንን እና ለሃገር የሚጠቅሙ ዜጎች ያፈራ ሲሆን የዲን እውቀትም ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ በማስተማር በአካዳሚክም በመንፈሳዊ እውቀትም የበለፀጉ እንዲሆኑ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአህባሽ መራሹ መጅሊሽ በሰላም መድረሳ የሚሰጠውን ትምህርት የአካዳሚክ እና የዲን ትምህርቱ እንዲለይ ከመንግስት ጋር በመተባበር ማድረጉ የታወቀ ሲሆን የአካዳሚክ ትምህርቱን በህዝባዊ ኮሚቴው እንዲመራ በማድረግ የዲን ትምህርቱን ደግሞ በአህባሽ መራሹ መጅሊስ እንዲመራ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ለረጅም አመታት የዲን ትምህረቱን ሲያስተምሩ የቆዩ መምህራንን ለረጅም ወራት ደሞዛቸውን በመከልከል ከስራ ማሰናበቱ የሚታወቅ ሰሆን በመድረሳው ላይም አዳዲስ የአህባሽ መምህራንን በመቅጠር...

በቢሾፍቱ በሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ መንግስት የወሰደውን ኃላፊነት የጎደለውን አረመኔያዊ እርምጃ በጽኑ እንደሚያወግዝ ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ

Posted on Oct 5, 2016

በቢሾፍቱ በሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ መንግስት የወሰደውን ኃላፊነት የጎደለውን አረመኔያዊ እርምጃ በጽኑ እንደሚያወግዝ ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 25/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

መንግስት የኢሬቻ በአልን ለማክበር በተሰበሰቡ በሚሊዬን በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የወሰደውን የሃይል እርምጃ እና እልቂት ድምፃችን ይሰማ እንደሚያወግዘው ዛሬ መስከረም 15/2009 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከመንግስት በርካታ ኃላፊነቶች መካከል የአገርን ህልውና እና የህዝብን ሰላም ማስጠበቅ ቀዳሚዎቹ ቢሆንም በአገራችን ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ በሚያሳዝን መልኩ በአገራችን እየተከሰቱ ያሉ ሰላም የሚያደፈርሱና ህልውናችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ ክስተቶች በአብዛኛው ምንጫቸው መንግስት ሆኖ እንደሚገኝ ድምፃችን ይሰማ አስታውቋልል፡፡

ከሰሞኑም ኃላፊነት በጎደለው የመንግስት እርምጃ በርካታ ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ለሞት መዳረጋቸውን ድምፃችን ይሰማ የገለፀ ሲሆን ይህ ድርጊት በየትኛውም መመዘኛ በጽኑው የሚወገዝ እና ስርዓቱ ምንግዜም ከስህተቱ የማይማር፣ ሰላማዊ ጥያቄን ከሚያነሱ ዜጎች ጋር ለመግባባት ከኃይል እና አፈሙዝ ውጭ ሌላ ቋንቋ እንደሌለው በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ድምፃችን ይሰማ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ከሰሞኑ በቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) የተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ማቆሚያ ያልተበጀለት የመንግስታዊው ጥቁር ሽብር ውጤት ነው ሲል ድምፃችን ይሰማ ያስታወቀ ሲሆን ይህ ክስተት በአገራችን ታሪክ በህዝብ ላይ የማይሽር ጠባሳ ጥለው ካለፉ አሳዛኝ ክስተቶች መካከል...

የኢትዬጲያ ሁጃጆች የሚሳፈሩበት የኢትዬጲያ አየር መንገድ የናይጄሪያ ሁጃጆችን እያመላለሰ በመሆኑ የሚሳፈሩበት አየር መንገድ አጥተው በጅዳ ኤርፖርት እየተንገላቱ መሆኑ ታወቀ

Posted on Oct 5, 2016

የኢትዬጲያ ሁጃጆች የሚሳፈሩበት የኢትዬጲያ አየር መንገድ የናይጄሪያ ሁጃጆችን እያመላለሰ በመሆኑ የሚሳፈሩበት አየር መንገድ አጥተው በጅዳ ኤርፖርት እየተንገላቱ መሆኑ ታወቀ

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 20/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

የዘንድሮውን ሃጅ ለማድረግ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ያቀኑ ኢትዬጲያውያን ሃጃጆች ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የሚሳፈሩበት አውሮፕላን በማጣታቸው በጅዳ ኤርፖርት እንግልት ላይ መሆናቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ህገ ወጡ የአህባሽ መጅሊስ በኢትዬጲያ ሃጃጆች ታሪክ ተከፍሎ የማያውቅ ክፍያ በዘንድሮ አመት ከእያንዳንዱ ሃጃጅ 70ሺህ ብር በመቀበል የሃጅ ጉዞ ማስደረጉ የሚታወቅ ሲሆን ሃጃጆች በኢትዬጲያ አየር መንገድ ትኬት የቆረጡ ቢሆንም በመመለሻቸው ቀን የኢትዬጲያ አየር መንገድ የናይጄሪያ እና የሌላ ሃገር ዜጎችን በማመላለስ ላይ በመጠመዱ ኢትዬጲያውያን ሃጃጆች በጅዳ ኤርፖርት ለሁለት ቀናት እንግልት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሁጃጆቹ በቆረጡት የአየር ትኬት መሰረት የበረራ ቀናቸው ሲቃረብ ህገ ወጡ መጅሊስ ከመካ ከተማ ወደ ጅዳ ኤርፖርት የወሰዷች ሲሆን በጅዳ ኤርፖርት ከደረሱ ቡኋላም የሚሄዱበት አውሮፕላን ሌሎች ሃጃጆችን እያመላለሰ በመሆኑ እነሱን ሊያስተናግዱ አለመቻሉ ታውቋል፡፡

በርካታ ቁጥር ያላቸው ሃጃጆች በጅዳ ኤርፖርት ላይ አሳፍሩን በማለት ሲጠይቁ እንደነበር የታወቀ ሲሆን የህገ ወጡ መጅሊስ አባላቶች ቆይ ትንሽ ጠብቁ አውሮፕላን ይመጣል በሚል ሃጃጆቹን ሲያንገሏቷቸው እንደነበር ተዘግቧል፡፡...