የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በሜልቦርን ተቃውሞ ላይ የተሳተፉ ዜጎችን ለመበቀል ሃገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸው እንዲታሰሩ ማድረጉ ተዘገበ

Posted on Nov 8, 2016

የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በሜልቦርን ተቃውሞ ላይ የተሳተፉ ዜጎችን ለመበቀል ሃገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸው እንዲታሰሩ ማድረጉ ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 29/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የተለያዩ ሰብአዊ መብት ጥሰት በመፈፀም የሚታወቀው በአቶ አብዲ መሐመድ የሚመራው የሶማሌ ክልል አስተዳደር በሰኔ ወር በአውስትራሊያ ሜልቦርን በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ የሶማሌ ተወላጆችን ለመበቀል በሀገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸውን እንዲታሰሩ ማስደረጉን ሂውማን ራይተስ ዎች የተሰኘው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ የሶማሌ ክልል የልኡካን ቡድንን ወደ አውስትራሊያ ባመራበት ወቅት የአውስትራሊያ የኢትዬጲያውያን ኮሚኒቲ አባላት በተለይም የሱማሌ ክልል ተወላጆች የልኡካን ቡድኑን በመቃወም ከባድ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያትም የልኡካን ቡድኑ በታሰበለት ፕሮግራም ላይ ሳይገኙ የቀረበ ሲሆን የተያዘላቸውም ፕሮግራም መሰረዙ ይታወቃል፡፡ በሜልቦርን በተካሄደው በዚህ ተቃውሞ ላይ የአውስትራሊያ መንግስት ለአንባገነኑ የኢትዬጲያ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ ኢትዬጲያውያኑ መቃወማቸው ተዘግቧል፡፡ በተቃውሞ ላይ የተሳተፉት የሶማሌ ክልል ተወላጆች የሆኑ ዜጎች ከሰልፉ መጠናቀቅ ቡኋላ በሶማሌ ክልል የሚኖሩ በርካታ ቤተሰቦቻቸው ለእስራት መዳረጋቸውን መስማታቸው ተገልፆል፡፡ በሰልፉ ላይ የተሳተፉ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በሃገር ቤት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለአስከፊ እስር የተዳረጉባቸው ሲሆን ያለምንም ፍትህ ለ 4 ወራት በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ሂውማን ራይተስ ዎች አስታውቋል፡፡...

የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ አዲሱ መጽሃፍ በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ

Posted on Nov 6, 2016

የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ አዲሱ መጽሃፍ በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 27/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከ4አመት ከ 2 ወራት በግፍ እስር ያሳለፈው እና በቅርቡ የተፈታው የየቲሞች አባት በመባል የሚታወቀው ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የቲምነት የማህበረሰቡ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው የተሰኘ አዲስ መፅሀፍ ፅሆ በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ በእምቢልታ አዳራሽ ማስመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ይህን መፅሃፍ ያዘጋጀው በዝዋይ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን የግድያ ሙከራ ከተደረገበት ቡኋላ ለኡማው የሚጠቅም ምንም ሳላበረክት ሞቼ ነበር በሚል ተነሳሽነት የቲምነት የማህበረሰቡ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው የተሰኘ አዲስ መፅሀፍ ለማዘጋጀት መቻሉን ለፍትህ ራዲዬ ገልፆል፡፡ መፅሃፉ 112 ገፆች ያሉት እና የቲም ምን ማለት እንደሆነ፣ የቲሞችን መንከባከብ በኢስላም ያለውን ደረጃ፣የቲሞችን መበደል ያለውን አደጋ ከቁርአን እና ከሃዲስ በማጣቀስ ሰፊ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ያለውን የየቲሞች ችግር እና መፍትሄዎቻቸውንም በመፅሃፉ ተዳሰዋል፡፡ በዛሬው እለት ጥቅምት 27/2009 በእምቢልታ አዳራሽ በርካታ ህዝበ ሙስሊም በታደመበት በደማቅ ሁኔታ የተመረቀ ሲሆን በምረቃ ነ ስርአቱ ላይም የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣የተለያዩ ኡስታዞች እና መሻይኮች መካፈላቸው ተዘግቧል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የክብር እንግዶች ከነበሩት አሊሞች እና ኡስታዞች መካከል ሸኽ ሰኢድ፣ሀጅ መሀመድ አወል ረጃ ፣ኡስታዝ አብዱፈታህ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ፣ኡስታዝ...

ከሊቢያ ጠረፍ የተነሱ 239 ስደተኞች ሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው መሞታቸው ተዘገበ

Posted on Nov 4, 2016

ከሊቢያ ጠረፍ የተነሱ 239 ስደተኞች ሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው መሞታቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 25/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከተለያዩ ሃገራት ወደ አውሮፓ ለመግባት ከሊቢያ የተነሱ ስደተኞች በሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ ስደተኞቹ ከሊቢያ ኮስት በመነሳት ወደ ጣልያን ለመጓዝ ጥረት ሲያደረጉ በነበረበት ወቅት ጀልባው ተገልብጦ ህይወታቸውን ማለፉ ተዘግቧል፡፡ በሁለት የተለያዩ ጀልባዎች ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 31 የሚሆኑ ስደተኞች በህይወት መትረፋቸው የተዘገበ ሲሆን በመጀመሪያው ጀልባ የነበሩ 29 ሰዎች ሲተርፉ ከሁለተኛው ጀልባ ውስት ደግሞ ሁለት ሴቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲዋኙ በህይወት አድን ሰራተኞች መትረፋቸው ተገልፆል፡፡ ሕይወታቸውን ያጡት ስደተኞች ከምዕራብ አፍሪካ እና ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሃገራት ዜጎች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ዝርዝር መረጃቸው እስካሁን አለመታወቁ ተዘግቧል፡፡ ከኤርትራ እና ከኢትዬጲየ በርካታ ስደተኞች በባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን የሚገቡ ሲሆን በርካቶችም በባህር ላይ ሰምጠው ህይወታቸው እንደሚያልፍ ይታወቃል፡፡ በዚህ አመት ብቻ 4220 የሚሆኑ ስደተኞች በባህር ሰምጠው መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን ከጊዜ ወደጊዜ አደጋው እየጨመረ ቢመታም ስደተኛው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በተያያ ዜናም በባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን የሚገቡ ስደተኞችን የጣሊያን ፖሊስ ስደተኞችን በኤሌክትሪክ ማሰቃያና በድብደባ ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃ ይፈጽምባቸዋል ሲል ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል...

የሙስሊሙ ቀንደኛ ጠላት የሆነው ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የትምህርት ሚኒስተር ተደርጎ ተሾመ

Posted on Nov 1, 2016

የሙስሊሙ ቀንደኛ ጠላት የሆነው ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የትምህርት ሚኒስተር ተደርጎ ተሾመ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 22/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከምርጫ 2007 ቡኋላ አቋቁመውት የነበረውን ካቢኔ በመበተን አዲስ የአካቢኔ አባላትን በዛሬ እለት ይፋ ማድረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በዘንድሮ አመት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የተከሰተውን ከባድ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነኝ በሚል ፕሮፖጋንዳ እየሰራ የሚገኘው ገዢው መንግስት ህዝቡን ያስቆጡትን ችግሮች እቀርፋለው በሚል አዲስ ካቢኔ መመስረቱ ታውቋል፡፡ በዛሬው እለት ጠ/ሚኒስተር ሃይለማርያም የተወካዬች ምክር ቤት ቀርበው አዲሱ ካቢኔያቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከህዝቡ በኩል ሲነሳ የነበረውን የብሄር ጭቆና ምላሽ እንዳገኘ ለማስመሰል ከኦሮሚያ ክልል ከፍ ያለ ቁጥር ያለው ሚኒስተሮችን መሾማቸው ተዘግቧል፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዶ/ር ወርቅነህ ገበየው ሲተኩ ውሸት በሚዲያዎች በማሰራጭ ወደር የማይገኝለት የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ጉዳዬች ፅ/ቤት ሃላፊ ሚኒስተር አቶ ጌታቸው ረዳ በዶ/ር ነገሪ ሌንጮ መተካታቸው ታውቋል፡፡ በጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነኝ እያለ የሚገኘው መንግስት ስልጣንን ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ አመራሮችን ከቦታቸው በማንሳት ብቃት ያላቸውን አመራሮችን እንተካለን ሲል ቢቆይም በሙስሊም ኢትዬጲያውያን ላየ ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ አሳርፎ የሚገኘውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያምን የትምህርት ሚኒስተር አድረጎ መሾሙ ሙስሊሙን አበሳጭቷል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተ/...

በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ለህዳር 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸ

Posted on Oct 24, 2016

በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ለህዳር 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 14/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በራያ አዘቦ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ለእስር የተዳረጉት ኡለሞች እና ኡስታዞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ጥቅምት 7 ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ኡለሞቹ እና ኡስታዞቹ በራያ አዘቦ ወረዳ ኩኩፍቶ በተባለ ቦታ የተያዙ ሲሆን ማይጨው በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ከታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች መካከል ከሳኡዲ አረቢያ ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኡስታዝ አብዱልመናንን ጨምሮ በአፍሪካ ቲቪ የትግርኛ ዳዕዋ በማድረግ የሚታወቀው ኡስታዝ ከድር ሁሴን፣ሼህ አህመድ ዩሱፍ እና ሌሎችም ሙስሊሞች በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ መዘገቧ ይታወሳል፡፡ አቃቤ ህጉ ካቀረበባቸው ክስ መካከል ቅሬ(እድር) ላይ አትሳተፉም፣ ዋሃቢያ ናችሁ፣ አብደላህ አል ሃረሪን አትቀበሉም፣ልጆች መልምላችሁ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ትልካላችሁ የሚሉን አሳፋሪ የሃሰት ክሶች እንደሚገኙበት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በቀረበባች ሃሰተኛ ክስ ላይም ፍርድ ቤቱ በሰጠው ቀነ ቀጠሮ መሰረት ጥቅምት 7 ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ዳግም ለህዳር 14 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠጡን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ እነዚህ በግፍ የታሰሩ ኡለሞች ከ10 ወራት በላይ በእስር እየተንገላቱ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቀነ ቀጠሮውን በማራዘም ኡለሞቹ...

በሸዋሮቢት በግፍ ታስር የሚገኙት እስረኞች ቤተሰቦች ለአንድ ሳምንት ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዳይመጡ እንደተነገራቸው ተዘገበ

Posted on Oct 19, 2016

በሸዋሮቢት በግፍ ታስር የሚገኙት እስረኞች ቤተሰቦች ለአንድ ሳምንት ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዳይመጡ እንደተነገራቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 9/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተነሳውን እሳት ቃጠሎ ተከትሎ ወደ ሸዋሮቢት እንዲዘዋወሩ ከተደረጉት እስረኞች መካከል በሸዋሮቢት እንዲታሰሩ የተደረጉት ሙስሊሞች ቤተሰቦቻቸው ለአንድ ሳምንት ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዳይመጡ እንደተከለከሉ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ከፍተኛ በደል እና ስቃይ እየተፈፀመባቸው መሆኑን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በሚፈፀምባቸው ድብደባ እና ስቃይም መራመድ እንዳቃታቸው ቤተሰቦቻቸው ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ በጥቅምት 6/2009 ወደ ሸዋሮቢት የተጓዙት የነዚህ ሙስሊም እስረኞች ቤተሰቦች ለአንድ ሳምንት ያህል ወደ ማረሚያ ቤቱ ተመልሰው እንዳይመጡ የተነገራቸው ሲሆን ቢመጡም ከታሳሪዎች ጋር እንደማያገናኟቸው እንደገለፁላቸው ታውቋል፡፡ ምክንያቱ በግልፅ ባልተቀመጠበት ሁኔታ ለምን አትምጡ ተባልን በማለት ወላጅ እናቶች ወደ ማረሚያ ቤቱ ምግብ ይዘው ቢሄዱም ከልጆቻቸው እና ከቤተሰባቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ተዘግቧል፡፡ ለቤተሰባቸው ይዘውት የሄዱት ምግብም አይገባም ተብሎ የተመለሰባቸው ሲሆን ለ 1 ሳምንት ቆይታችሁ ተመልሳችሁ ኑ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ በሸዋሮቢት የታሰሩት እስረኞች አካላቸው ተጎሳቁሎ፣መራመድ አቅቷቸው ከፍተኛ ጉዳት ላይ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለፍትህ ራዲዬ የገለፁ ሲሆን አሁን ደግሞ ለ 1 ሳምንት እንዳትመጡ መባላቸው ምን ተፈጥሮ ይሆን በሚል ጭንቀት ውስጥ መውደቃቸው...

በማዕከላዊ ለወራት ታስረው የነበሩት በወንድም አልአሙዲን ኩመል የክስ መዝገብ የተከሰሱት 6 ሙስሊሞች የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት ተዘዋወሩ

Posted on Oct 18, 2016

በማዕከላዊ ለወራት ታስረው የነበሩት በወንድም አልአሙዲን ኩመል የክስ መዝገብ የተከሰሱት 6 ሙስሊሞች የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት ተዘዋወሩ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 8/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአዲስ አበባ በደህንነቶች አማካኝነት ከስድስት ወራት በፊት ከቤተል እና አካባቢዋ ታድነው ወደ ማዕከላዊ ተወስደው ከነበሩት 9 ሙስሊሞች መካከል ስድስቱ ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ቂሊንጦ መዘዋወራቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ የሙስሊሙን ትግል ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን ከ 6 ወራት በፊትም 9 ሙስሊሞች ከአዲስ አበባ ከተማ በደህንነቶች ታፍነው በማዕከላዊ ታስረው እንደነበር ተዘግቧል፡: ሚያዚያ 20/2008 ቀን ለእስር መዳረጋቸውን የገለፁ ሲሆን በለሊት ለምረመራ በሚል ከእንቅልፋቸው እየተቀሰቀሱ መርማሪዎች ሲያሰቃዩዋቸው እንደነበር ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤትም ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ ሲካሄድባቸው እንደነበር የተዘገበ ሲሆን አብረው ከታሰሩት 9 ሙስሊሞች መካከል ሶስቱ የሚሆኑትን ያለምንም ምክንያት ድንገት ከእስር ቤቱ እንዲፈቱ እንዳደረጓቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ የተፈቱት ሶስት ሙስሊሞችም የክስ መዝገቡ ተጠሪ የሆነው ወንድም አልአሙዲን ኩመል፣አብዲ ሸናኔ እና መካ መሐመድ መሆና ቸው ይታወቃ፡፡ በማዕከላዊ በነበሩበት ቆይታ አስጨናቂ እና የስቃይ ጊዜ ማሳለፋቸውን በወቅቱ የገለፁ ሲሆን ቀሪዎቹ 6 ሙስሊም ወጣቶችም ጉዳያቸው አላለቀም በሚል እስካሁን ሳይፈቱ እንደቀሩ ይታወቃል፡፡ ሳይፈቱ የቀሩትን 6 ሙስሊሞች የሽብር ክስ...