በትግራይ ክልል በኹኩፍቶ ወረዳ ቀንደኛ የአህባሽ አቀንቃኞች የሙስሊሙን ገንዘብ መመዝበራቸው ተገለፀ

Posted on Nov 27, 2016

በትግራይ ክልል በኹኩፍቶ ወረዳ ቀንደኛ የአህባሽ አቀንቃኞች የሙስሊሙን ገንዘብ መመዝበራቸው ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር18/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በርካታ ሙስሊሞች በሚኖሩበት ኹኩፍቶ በተባለው አካባቢ ለሙስሊሙ ትምህርት ቤት ማሰሪያ በሚል የተሰበሰበውን ገንዘብ የወረዳው የአህባሽ አቀንቃኞች መመዝበረቸውን የአካባቢው ተወላጆች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

ኹኩፍቶ በትግራይ ደቡባዊ ዞን ያለ ሙስሊም ማህበረሰብ የሚበዛበት ኣከባቢ ሲሆን በርካታ ታላላቅ አሊሞችን ያፈራ ቦታ እንደነበር ተገልፆል፡፡

የአህባሽ አስተሳሰብ በግዳጅ በመንግስት አማካኝነት ሲጫን በትግራይ ክልል በአህባሾች ሰለባ እንዲሆን ከተደረገው መካከል ይህ አካባቢ ተጠቃሽ ሲሆን አቶ ኢድሪስ ጀማል የተባለው የቀድሞ የህወሃት ታጋይ እና የአህባሽ አቀንቃኝ የሆነው ግለሰብ የሙስሊሙን ገንዘብ እየመዘበረ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡

አቶ ኢድሪስ በአካባቢው ሼህ አብዱልአዚዝ ከሚባል ሰው ጋርበመተባበር በሙስሊሙ ላይ ከፍተና በደል እና ግፍ እየፈፀሙ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በራያ የታሰሩት በርካታ ኡለሞች እንዲታሰሩ ዋነኝ ምክንያት መሆኑም ተገልፆል፡፡

በሼህ አብዱልመናን መዝገብ ተከሰው በግፍ እስራት ላይ የሚገኙት ኡለሞች እና ኡስታዞችም በዚህ አቶ ኢድሪስ በተባለ ግለሰብ ጠንሳሽነት ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል፡፡

በትግራይ...

የቂሊንጦ ማ/ቤት እንዲቃጠል ምክንያት ሆነዋል በሚል 38 እስረኞች ክሰ እንደተመሰረተበቸው ታወቀ

Posted on Nov 23, 2016

የቂሊንጦ ማ/ቤት እንዲቃጠል ምክንያት ሆነዋል በሚል 38 እስረኞች ክሰ እንደተመሰረተበቸው ታወቀ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር14/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእሳት አደጋ ጉዳት ከደረሰበት ቡኋላ ማረሚያ ቤቱን ያቃጠልነው እና ነን ብላችሁ እመኑ በሚል በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ሲያስተናግዱ የነበሩት እስረኞች ክስ እንደተመሰረተባቸው የመንግስት ሚዲያ የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ አስታውቋል፡፡

ፋና በዘገባው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በተከፈተው ክስ፥ ታራሚዎቹ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድረገዋል ሲል ክስ እንደተመሰረተባቸው ገልፆል፡፡

በዚህ ክስ የተወነጀሉትበሸብር ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች 1ኛ ማስረሻ ሰጤ፣ 2ኛ ወልዴ ሞቱማ፣ 3ኛ አሸናፊ አካሉ ጨምሮ 38 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ መሆናቸውን ዘግቧል፡፡

ተከሳሾቹ ከጥር ወር 2008 ዓ. ጀምሮ የኦነግ፣ ግንቦት ሰባት እና በአልሸባብ የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈጸም በማረሚያ ቤቱ በተለያዩ ወንጀሎች በእርማት ላይ ያሉ ታራሚዎችን በድብቅ በመመልመል አመጽ ለመፍጠር መረጃ መለዋወጣቸውን የጠቅላይ አቃቢ ህግ ክስ እንደሚያስረዳ ተገልፆል፡፡

አመጽ ማስነሳት እንዲችሉም በውጭ እና ሃገር ውስጥ ከሚገኙ አባላትና ማረሚያ ቤት ውስጥ ከሚገኙ ታራሚዎች ገንዘብ በማሰባሰብ የአመጹን ድርጊት በሃይል ይመራሉ ብለው ለመለመሏቸው ታራሚዎች ከተሰበሰበው ገንዘብ በተለያየ ጊዜ ክፍያ...

በማሻ ማቅደላ የሚገኘው ታላቁን መስጂደል ረህማንን ለማቃጠል የተደረገው ሙከራ መክሸፉ ተገለፀ

Posted on Nov 22, 2016

በማሻ ማቅደላ የሚገኘው ታላቁን መስጂደል ረህማንን ለማቃጠል የተደረገው ሙከራ መክሸፉ ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር13/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎዞን በማሻ መቅደላ የሚገኘውን ትልቁን መስጂደል ረህማንን ለማቃጠል የተደረገው ሙከራ መክሸፉን የአካባበው ሙስሊሞች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

ባሳለፍነው ጁምዓ ከኢሻ ሰላት ቡኋላ ማንነተቸው ያልታወቁ ግለሰቦች መስጂዱን ለማቃጠል የሞከሩ ሲሆን በወቅቱ የመስጂዱ ጥበቃ የይድረሱልኝ ጥሪ በማሰማቱ የአካባቢው ማህበረሰብ በቦታው ደርሶ መስጂዱን ከቃጠሎ ማትረፍ መቻላቸው ተዘግቧል፡፡

በመቅደላ ወረዳ በአቶ ካሳ ፈቀደ እና በአቶ አለሙ አማካኝነት ከዚህ ቀደም በወረዳው የሚገኙ ቤተክርስቲያኖች እንዲቃጠሉ ተደርገው በመቅደላ ወረዳ እጅግ በርካታ ሙስሊሞች ለግፍ እስራት እና ስቃይ መዳረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

በወረዳው ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ለማጋጨት በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን ቤተ እምነቶችን በማቃጠል የሁለቱን እምነት ተከታዬች ለማጋጨት እየተሞከረ መሆኑ ተገልፆል፡፡

በመስጂደል ረህማን የተደረገው የማቃጠል ሙከራ በተመሳሳይ በወረዳው በሚገኘው የደፈርጌ ቤተክርስቲያንንም ለማቃጠል ተሞክሮ የቤተክርስቲያኑ የጥበቃ ሰራተኞች ሊያከሽፉት መቻላቸው ይታወቃል፡፡

በመቅደላ ወረዳ የመንግስት ካድሬዎች ባቃጠሉት ቤተክርስቲያን እስካሁን በርካታ ሙስሊሞች በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ እውነታውን በመረዳቱ በሰላም ተከባብሮ እየኖረ...

  በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ስቃይ ሲያስተናገዱ የነበሩት ሙስሊም እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዘዋወሩ

Posted on Nov 21, 2016

በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ስቃይ ሲያስተናገዱ የነበሩት ሙስሊም እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዘዋወሩ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር12/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳው እሳት ቃጠሎ ወደ ሸዋሮቢት ተዘዋውረው ከነበሩት እስረኞች መካከል ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ ሲያስተናግዱ የነበሩት ሙስሊም እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መመለሳቸውን የፍትህ ራዲዬ በልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ሙስሊም እስረኞቹ በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ውስጥ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን ያቃጠልነው እኛ ነን ብላችሁ እመኑ በሚል ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ሲፈፀምባቸው እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በአዲስ መልኩም ክስ ሊመሰርቱባቸው መዘጋጀታቸውን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ከሸዋሮቢት ወደ ቂሊንጦ ከተመለሱት መካከል

1 ኡስማን አብዶ

2 ሸህአብዲን ነስረዲን

3 ፍፁም ቸርነት

4 ኢብራሂም ካሚል

5 ከድር ታደለ

6 ኡመር ሁሴን

7 እስማኤል ሀሰን

8 ነዚፍ ተማም እንደሚገኙበት ታውቋል፡:

ከሸዋሮቢት ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ቢደረጉም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ከማዕከላዊ የመጡ መርማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ በመፈጸም እና ፂማቸውን...

7 ሙስሊሞች በሽብር ወንጀል ተከሰው እስከ ዘጠኝ አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተበየነባቸው

Posted on Nov 11, 2016

7 ሙስሊሞች በሽብር ወንጀል ተከሰው እስከ ዘጠኝ አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተበየነባቸው ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 2/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ተንቀሳቅሰዋል በሚል የሃሰት ክስ የመሰረተባቸው ሰባት ሙስሊሞች ላይ ከሁለት እስከ ዘጠኝ አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ተዘገበ፡፡ ፍርድ ቤቱ የእስር ቅጣቱን የወሰነው 1ኛ መሐመድ አብዱራህማን፣ 2ኛ መሐመድ አህመድ፣ 3ኛ መሐመድ አብዱላሂ፣ 4ኛ መሐመድ አሊ፣ 5ኛ አነሰ ኡስማን፣ 6ኛ ኡስማን ሀሰን፣ 7ኛ መሀመድ አዌስ በተሰኙ ሙስሊሞች ላይ ነው፡: የኢትዬጲያ መንግስት ላልፉት 6 አመታት ሙስሊሞችን በሽብርተንነት በመወንጀል ከአልሸባብ እና ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ ነበር በሚል በርካቶችን ለግፍ እስራት መዳረጉ የሚታወስ ነው፡፡ የመሀመድ አብዱላሂ የክስ መዝገብ ተከሰው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩት እነዚህ 7 ሙስሊሞች የ አልሸባብ ቡድን አባል በመሆን፣ ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድና የሽብር ቡድኑ አስታጥቋቸው ሞቃዲሾ ከቆዩ በሁዋላ በተለያዩ ጊዜያት በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመግባት ለሽብር ተግባር ተንቀሳቅሰዋል የሚል ውንጀላ እንደቀረበባቸው ታውቋል፡፡ ጥቅምት 3 ቀን 2006 በ አዲስ አበባ ውስጥ ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ፈንጂ በማፈንዳት ጥቃት ለማድረስ ተሰማርተው ከነበሩ ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ጋር በመገናኘት በሽብር ተግባሩ ላይ ተባባሪ ሆነው ተግኝተዋል ሲል...

የወልድያው መድረሰተል ሰላም አል ኢስላሚያ መምህራን በህገወጡ መጅሊስ ላይ ባቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ ዳግም ለታህሳስ 11 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Nov 10, 2016

የወልድያው መድረሰተል ሰላም አል ኢስላሚያ መምህራን በህገወጡ መጅሊስ ላይ ባቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ ዳግም ለታህሳስ 11 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 1/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ ከአወልያ ቀጥሎ ለሙስሊሙ ትልቁ ተቋም የነበረው የወልዲያ መስጂዶች እና ትምህርት ቤቶች ማዕከል ከህዝብ ተወስዶ ለህገ ወጡ መጅሊስ ከተሰጠ ቡሃላ ህገ ወጡ መጅሊስ ለማስተዳደር ባለመቻሉ ዳግም ለህዝቡ ቢመለስም በተቋሙ ስር የነበሩትን የዲን መድረሳዎች አህበሽ መራሹ መጅሊስ ማስተዳደር የሚገባኝ እኔ ነኝ የሚል ጥያቄ በማንሳቱ መንግስት መድረሳዎቹን ለመጅሊሱ አሳልፎ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ የወልዲያ ከተማ የመንግስት አካላት በተቋሙ ስር የነበሩትን ትምህርት ቤቶች የዲን እና የአካዳሚክ ትምህርቶች ተለይተው እንዲሰጡ ማስደረጉ የሚታወስ ሲሆን በህዝብ የተመረጠውን ኮሚቴ አካዳሚኩን ብቻ እንዲያስተዳደር፣ የዲን መድረሳዎችን ግን በአህባሾች እንዲተዳደር እንዲደረግ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ የወልዲያ መድረሳዎች የሚተራደሩበት የነበረው የማዕከሉ ገቢ ማስገኛዎችን ህገ ወጡ መጅሊስ በጉልበት የተረከባቸው ቢሆንም በመድረሳዎቹ የሚያስተምሩትን መምህራኖች ደሞዝ ሊከፍል አለመቻሉ ተዘግቧል፡፤ በተደጋጋሚ መምህራኖቹ ለ 11 ወራት የሰሩበትን ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው ለህገ ወጡ መጅሊስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሊያገኙ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸውን የፍትህ ራዲዬ መዘገቧ ይታወሳል፡፤ መምህራኖቹ ህገ ወጡ መጅሊስ እየፈፀመበቸው የሚገኘውን በደል ለፍርድ በቱ በማስረጃ በማቅረባቸው ህገ ወጡ መጅሊስ...

የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞች በከተማው ለሚገኙ የቲሞች እና ወላጆቻቸው ደካማ ለሆኑባቻው ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ

Posted on Nov 8, 2016

የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞች በከተማው ለሚገኙ የቲሞች እና ወላጆቻቸው ደካማ ለሆኑባቻው ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 29/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በሃርቡ ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች በከተማቸው የሚገኙ የቲሞችን እና አቅመ ደካማ ወላጆቸች ላሏቸውን ታዳጊዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ ህፃናቱ የቲም በመሆናቸው እና ወላጆቻቸው አቅመ ደካማ በመሆናቸው ለትምህርት የሚስፈልጋቸውን ነገሮች ማሟላት ባለመቻላቸው ተቸግረው የነበረ ሲሆን የሃርቡ ከተማ ሙስሊም ጀምዓዎች የነዚህን ታዳጊ ህፃናት ችግር በመረዳት ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ተዘግቧል፡፡ በዛሬዉ እለት ጥቅምት 29 የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞች ለየቲሞች እና ወላጆቻቸዉ ደካማ ለሆኑባቸዉ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ሰሰላ ተማሪዎች ሙሉ ዩኒፎርም አሰፍተው እንዳለበሷቸው ተገልፆል፡፡ የከተማው ሙስሊሞች ይህን ኸይር ስራ ለመሰራት ከእስር የተለቀቁትን ኮሚቴዎች እና ሃያተል ኩብራን ዘይረው በተመለሱበት ወቅት በገቡት ቃልኪዳን መሰረት መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተማሪዎቹ የቲም በመሆናቸው እና ወላጆቸቸው አቅመ ደካማ በመሆናች ከትምህርት ገበታቸው ሊሰናከሉ አይገባም በሚል ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ተዘግቧል፡፡ የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞች 360 ኪሎሜትር በማቋረጥ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ከእስር የተፈቱትን ኮሚቴዎች መዘየራች የሚታወስ ሲሆን በዚያራቸውም ለሁሉም ለተፈቱት ኮሚቴዎቻችም የሰላም መገለጫ የሆነውን ነጭ ሻል እንዲሁም ለእህት አያተል ኩብራም መስዋትነት የከፈለችለትን ሂጃብ አንድ ሙሉ ጅልባበ ከክሬም ጋር በስጦታነት...