በከድር መሐመድ  የክስ መዝገብ የተከሰሱት 19 ሙስሊም ወንድሞቻችን የ 5 አመት ከ 6 ወራት የእስራት ቅጣት ተበየነባቸው

Posted on Jan 3, 2017

በከድር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 19 ሙስሊም ወንድሞቻችን የ 5 አመት ከ 6 ወራት የእስራት ቅጣት ተበየነባቸው

በፍትህ ራዲዬ/ታህሳስ 25/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ከድር መሃመድ የክስ መዝገብ ተከሰው ከአዲስ አበባ እና ከጅማ ከተማ በደህንነት ሃይሎች ታፍነው ለእስር የተዳረጉት 19 ሙስሊም ወንድሞቻችን የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔያቸውን ለመስማት በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት በዛሬው እለት የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ ባቀረበባቸው ክስ መሰረት ፍርድ ቤቱ በሁሉም ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፈ ቡሃላ እንዲከላከሉ ብይን ቢያስተላልፍ ተከሳሾቹ በፍርድ ቤቱ ገለልተኝነት አመኔታ የሌላቸው በመሆኑ፣በቂሊንጦ ማረሚያ ቤትም እየተፈፀመባቸው ባለው ግፍ እና ስቃይ በማረሚያ ቤቱ ተጨማሪ ጊዜያትን ለመቆየት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መከላከያ ምስክሮቻቸውን ማቅረባቸው ጥቅም የሌለው መሆኑን በማስረዳት መከላከያ እንደማያቀርቡ እና ፍርድ ቤቱም የመጨረሻ የሚለውን የቅጣት ውሳኔ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ይታወቃል፡

ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪን እና ጋዜጠና ካሊድ መሐመድን ያካተት ይህ የክስ መዝገብ ኮሚቴውን በሃይል ለማስፈታት በማሴር፣ በአዲስ አበባ ፣በወልቂጤ እና በጅማ ከተሞች ህገ ወጥ ሰልፍ እና ብጥብት ለመቀስቀስ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ ነበር በሚል ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፍርድ ቤቱ መበየኑ ይታወቃል፡፡

በሃሰት የተወነጀሉት ወንድሞቻችን በፀር ሽብር ህጉ አንቀፅ 7/1 እና...

በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ለጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Dec 27, 2016

በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ለጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ፍትህ ራዲዬ/ታህሳስ 18/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በራያ አዘቦ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ለእስር የተዳረጉት ኡለሞች እና ኡስታዞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀነ ቀጠሯቸው ወደ ጥር 18 እንዲዘዋወር መደረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኡለሞቹ እና ኡስታዞቹ በራያ አዘቦ ወረዳ ኩኩፍቶ በተባለ ቦታ የተያዙ ሲሆን ማይጨው በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

ከታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች መካከል ከሳኡዲ አረቢያ ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኡስታዝ አብዱልመናንን ጨምሮ በአፍሪካ ቲቪ የትግርኛ ዳዕዋ በማድረግ የሚታወቀው ኡስታዝ ከድር ሁሴን፣ሼህ አህመድ ዩሱፍ እና ሌሎችም ሙስሊሞች በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

አቃቤ ህጉ ካቀረበባቸው ክስ መካከል ቅሬ(እድር) ላይ አትሳተፉም፣ ዋሃቢያ ናችሁ፣ አብደላህ አል ሃረሪን አትቀበሉም፣ልጆች መልምላችሁ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ትልካላችሁ የሚሉን አሳፋሪ የሃሰት ክሶች እንደሚገኙበት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በቀረበባች ሃሰተኛ ክስ ላይም አቃቤ ህጉ አሉኝ ያለቸውን ምስክሮቹን ለፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ትዕዛዝ መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን ከቀነ ቀጠሮ በፊት ታህሳስ 11 ቀን ቀነ...

በነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው

Posted on Dec 7, 2016

በነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 27/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ለእስር የተዳረጉት በነብዩ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 27 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኮሚቴውን በሃይል ለማስፈታትን እና ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል ብላቹሃል በሚል በሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህጉን ምስክሮች በመስማት ጉዳዩን ከመረመረ ቡኋላ በሁሉም ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዳስተላለፈባቸው የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ሆናችሁ አግኝቻቹሃለው በሚል እንዲከላከሉ የበየነባቸው ሲሆን ፍትህ በሌለበት ሃገር መከላከያ ማቅረብ ጥቅም የለውም በሚል አንከላከልም የሚል ውሳኔያቸውን ለፍርድ ቤቱ አሳውቀዋል፡፡

የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው 7ቱ ሙስሊሞች

1. ነብዩ ሲራጅ

2. ሰፋ በደዊ

3. መሃመድ ሰዒድ

4. ሰላሃዲን ከድር

5. ሙጂብ አደም እረሺድ

6. ከድር ታደለ

7. አህመድ ኡመር መሆናቸው ታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱም...

በከድር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 19 ሙስሊሞች በቀረረባቸው ክስ እንዲከላከሉ ተበየነባቸው

Posted on Dec 7, 2016

በከድር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 19 ሙስሊሞች በቀረረባቸው ክስ እንዲከላከሉ ተበየነባቸው

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 27/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ከድር መሃመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ከአዲስ አበባ እና ከጅማ ከተማ በደህንነት ሃይሎች ታፍነው ለእስር የተዳረጉት 19 ሙስሊሞች ለብይን በተሰጣቸው ቀነ ቀጠሮ መሰረት በዛሬው እለት የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት መቅረባቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ እና ጋዜጠኛ ካሊድ መሀመድን ጨምሮ ቁጥራቸው 19 የሚደርሱት ሙስሊሞች አቃ ህጉ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ ኮሚቴውን በሃይል ለማስፈታት ሞከረዋል እና ህዝብን ለአመፅ ለማነሳሳት በጅማ እና በአዲስ አበባ ከተማ ወረቀት በትነዋል በሚል በሽብር ወንጀል እንደከሰሳቸው የሚታወስ ሲሆን አቃቤ ህጉ የሐሰት ምስክሮቹን ካስደመጠ ቡኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠጥ ለጀርም ወራት በቀነ ቀጠሮ ሲያንገላታቸው ቆይተዋል፡፡

ተከሳሾቹ በሚቀርቡበት ችሎት ዳኞቹ ገለልተኛ ባለመሆናቸው ዳኞች ይቀየሩልን በሚል አቤቱታ አሰምተው ዳኞች እንደተቀየሩላቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ችሎትም ጉዳዩን ሲመለከቱ የነበሩት ዳኞች ተቀይረው የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አዲስ ዳኞች እንዳነበቡት ተዘግቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም የአቃቤ ህጉን ምስክር በመመርመር በ 19ኙም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን...

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በአህባሾች ሰበብ እየታሰሩ እና እየተዋከቡ መሆኑ ተዘገበ

Posted on Dec 5, 2016

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በአህባሾች ሰበብ እየታሰሩ እና እየተዋከቡ መሆኑ ተዘገበ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር26/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች ወሃቢይ አክራሪ በሚል ለእስር እየተዳረጉ መሆናቸውን ተማሪዎቹ ለፍትህ ራዲዬ ገልጸዋል፡፡

ፅንፈኛ የአህባሽ አመራሮች የሚመሩት የአማራ ክልል ህገ ወጡ መጅሊስ በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ አህባሽን የማስፋፋት ስራ እየሰራ የሚገኘው ሲሆን ጠንካራ ሙስሊሞች ይወጡበታል ተብሎ የሚገመተውን የዩኒቨርሲቱ ሙስሊም ጀምዓዎችንም በመበታተን ተማሪዎችን እያሳሰሩ መሆናቸው ተገልፆል፡፡

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች የሚገለገሉበትን መስጂድ ህገ ወጡ የአህባሽ መጅሊስ ባሳፍነው ሃሙስ አዲስ የአህባሽ ኢማም የሾመባቸው ሲሆን ኢማሙን ተከትለን አንሰግድም ያሉ ተማሪዎች ለእስራት መዳረጋቸውን ተማሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በሳለፍነው ጁምዓ የአህባሽ ኢማሙን ተከትለን አንሰግድም በሚል ሁለተኛ ጀምዓ የሰገዱ 9 ተማሪዎች መታሰራቸው የተዘገበ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሁለተኛ ጀምዓ የሰገዱ ሶስት ተማሪዎች መታሰራቸው ታውቋል፡፡

አህባሾቹ ከመንግስት ሃይሎች ጋር በመተባበር ጠንካራ ሙስሊሞችን እያሳሰሩ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በወሎ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥም በየዶርሙ የወሃቢይ መፅሃፍ...

የቂሊንጦ ማ/ቤትን አቃጥላቹሃል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 38 እስረኞች ለታህሳስ 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Dec 2, 2016

የቂሊንጦ ማ/ቤትን አቃጥላቹሃል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 38 እስረኞች ለታህሳስ 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር23/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ እንዲነሳ አድረገዋል በሚል እና 23 ታራሚዎች ላይ አሰቃቂ ድብደባ ፈፅመው በእሳት እንዲቃጠል አድርገዋል በሚል የሃሰት ክስ የተመሰረተባቸው 38 እስረኞች በዛሬው እለት አርብ ህዳር 23 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ መቅረባቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው 38ቱ እስረኞች አቃቤ ህጉ የመሰረተባቸውን የሃሰት ክስ በዛሬው ችሎት በንባብ የቀረበላቸው ሲሆን በተለያየ ጊዜ በድብቅ መረጃ በመለዋወጥ የአመጽ ጥሪ በማስተላለፍ በማረሚያ ቤቱ አመጽ ማስነሳት፣ ማቃጠልና ማውደም የሚል እቅድ በመያዝ በነሃሴ 28 ቀን 2008 ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ የዞን ሁለት ታራሚዎች ባስነሱት አመጽ የዋጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት የማረሚያ ቤቱን ንብረት አውድመዋል ሲል አቃቤ ህጉ ክስ ማቅረቡ ታውቋል፡፡

በውጭና በአገር ውስጥ ከሚገኙ ታራሚዎች ገንዘብ በማሰባሰብ የአመፁን ድርጊት በኃይል ይመራሉ ያሉዋቸውን በከባድ ወንጀልና በውንብድና የተከሰሱትን ታራሚዎች በመመልመል፣ ‹‹የሽብርና የዱርዬው ቡድን›› የሚል ስያሜ በመስጠት ሲመካከሩ ከርመዋል ሲል አቃቤ ህጉ በክሱ ላይ ማቅረቡ...