በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ጉዳያቸውን የያዙት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች ብቁ ለመሆናችሁ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው በመባሉ በድጋሚ ለየካቲት 13 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Jan 28, 2017

በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ጉዳያቸውን የያዙት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች ብቁ ለመሆናችሁ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው በመባሉ በድጋሚ ለየካቲት 13 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 20/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በራያ አዘቦ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ለእስር የተዳረጉት ኡለሞች እና ኡስታዞች በቀነ ቀሯቸው መሰረት ጥር 18 ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኡለሞቹ እና ኡስታዞቹ በራያ አዘቦ ወረዳ ኩኩፍቶ በተባለ ቦታ የተያዙ ሲሆን ማይጨው በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

ከታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች መካከል ከሳኡዲ አረቢያ ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኡስታዝ አብዱልመናንን ጨምሮ በአፍሪካ ቲቪ የትግርኛ ዳዕዋ በማድረግ የሚታወቀው ኡስታዝ ከድር ሁሴን፣ሼህ አህመድ ዩሱፍ እና ሌሎችም ሙስሊሞች በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

አቃቤ ህጉ ካቀረበባቸው ክስ መካከል ቅሬ(እድር) ላይ አትሳተፉም፣ ዋሃቢያ ናችሁ፣ አብደላህ አል ሃረሪን አትቀበሉም፣ልጆች መልምላችሁ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ትልካላችሁ የሚሉን አሳፋሪ የሃሰት ክሶች እንደሚገኙበት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የመንግስት አቃቤ ህግ የሆነው አቶ ኢድሪስ ጀማል የሃሰት ምስክሮቹን ለማቅረብ በመቸገሩ ከዳኞቹ ጋር በመነጋገር ተከሳሾችም ሆኑ ጠበቆቻቸው ባልተገኙበት ቀነ...

ከ166 በላይ ስደተኞች በሜዴትራንያን ባህር ሰምጠው መሞታቸው ተዘገበ

Posted on Jan 26, 2017

ከ166በላይ ስደተኞች በሜዴትራንያን ባህር ሰምጠው መሞታቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 18/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ከ170 በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ከአቅሙ በላይ የጫነ ጀልባ ቅዳሜ ለሊት በሚዲትራኒያን ባህር ሰምጦ አራት ስደተኞች ብቻ ሲተርፉ ሌሎቹ ህይወታቸውን ማጣታቸውን አንድ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ከተረፉት ስደተኞች ሁለቱ ኤርትራዊ ሁለቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ አንዷ ነፍሠ ጡር እንደሆነች አጀንሲያ አበሻ የተባለው ስደተኞችን የሚረዳው ቡድን መሪ አባ ሙሴ ዘርዓይ፤ የጣሊያን ባህር ሃይልን ጠቅሰው ገልጸዋል፡፡ አዲሱ የፈረንጆች አመት ከገባ ወዲህ የዚህ መሰሉ አደጋ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ባሳለፍነው ቅዳሜ በደረሰ አደጋ 160 የሚደርሱ ስደተኞች ባህር ውስጥ ገብተው መሞታቸው ተዘግቧል፡፡ ስደተኞቹ ከኢትዬጲያ፣ከኤርትራ፣ከሱዳን ፣ከሶማልያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ወደ አውሮፓ ለማቅናት ሲሞክሩ የነበሩ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ጀልባው መያዝ ከሚችለው በላይ ስደተኞች በመጫናቸው ጀልባው ተገልብጦ በርካቶችህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል፡፡ ከሞቱት መካከል በርካታ ሴቶች እንደሚገኙበት የታወቀ ሲሆን አንድ ነፍሰ ጡረ የሆነች ሴት በህይወት መትረፏ ታውቋል፡፡ ከስደተኞቹ መካከል ቁጥራቸው 8 የሚደርሱ ህፃናትም እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ስደተኞች ቁጥር ከ 166 ሊበልጥ እንደሚችል ተዘግቧል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሜዴትራንያን ባህር ከፍተኛ የባህር ሞገድ ያለበት ሲሆን ህገ ወጥ ደላሎች የባህሩን የማዕበል ሁኔታ አደገኛ መሆኑን እያወቁም ስደተኞቹ...

በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት  የደሴ ወጣቶች ከ3 አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተበየናቸው

Posted on Jan 26, 2017

በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት የደሴ ወጣቶች ከ3 አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተበየናቸው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 18/2009

۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩

በደሴ ከተማ ከ 3 አመት በፊት በመንግስት ደህንነቶች አቀናባሪነት የተገደሉትን ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል ሰበብ እና በሽብር ተግባ ላይ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከደሴ ከተማ ለእስር የተዳረጉት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የሚገኙት 13 ወጣት ሙስሊሞች የቅጣት ውሳኔያቸውን ለመስማት በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት በዛሬው እለት ጥር 18 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በታህሳስ 27 በነበራቸው ችሎት በ13ቱም ተከሳሾች ላይ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ብይን ያስተላለፈ ሲሆን አቃቤ ህጉ እና ተከሳሾች የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያቸውን ለፍ/ቤቱ እንዲያቀርቡ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት በሁሉም ታሳሪዎች ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን ከ 3አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት ፅኑ እስራት እንደበየነባቸው ተዘግቧል፡፡

አስራ ሶስቱ ተከሳሾች በሶስት ደረጃ ተከፍለው በተለያዩ አንቀፆች ጥፋተኛ መባላቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህም መሰረት ጥፋተኛ በተባሉበት አንቀፅ የቅጣት ብይን እንደተላለፈባቸው ታውቋል፡፡

በዚህም 8ኛ ተከሳሽን በ16 አመት ፅኑ እስራት፣ 1ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ እና በ15 እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽን በ15 አመት ከ6 ወር፣ 6ኛ እና 11ኛ...

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት 7 ሙስሊም ወንድሞች ላይ ከ 4አመት እስከ 4 አመት ከ 5 ወር የሚደርስ እስራት ቅጣት በየነባቸው

Posted on Jan 23, 2017

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት 7 ሙስሊም ወንድሞች ላይ ከ 4አመት እስከ 4 አመት ከ 5 ወር የሚደርስ እስራት ቅጣት በየነባቸው ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 15/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በጃፈር መሐመድ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው በነበሩት 7 ሙስሊሞች ላይ የእስራት ቅጣት መበየኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ሰባቱ ሙስሊሞች ከጅማ ከተማ ከ 3አመታት በፊት ለእስር የተዳረጉ ሲሆን በሶማልያ ከሚገኘው አልሸባብ ጋር ግንኙት ነበራቸው በሚል በሽብር መከሰሳቸው ታውቋል፡፡ ሰባቱ ተከሳሾች 1. ጃፈር መሐመድ፣ 2. መሐመድኑር፣ 3. ሃጂ መሐመድ ታሚ፣ 4. ሙህዲን ጀማል፣ 5. አህመድ አባቢያ ፣ 6. አንዋር ትዳኔ እና 7. ሼኽጀማል አባ ጫቦ መሆናቸው ታውቋል፡ በኢትዬጲያ ውስጥ የጀሃድ ጦርነት ለማወጅ እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመሄድ ስልጠና ወስደዋል ሲል አቃቤ ህጉ የከሰሳቸው ሲሆን ከጅማ ከተማ ወደ ሶማልያ በመጓዝ ከአልሸባብ ጋር በመቀላቀል ስልጠና ሊወስዱ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል አቃቤ ህጉ ክሱን አቅርቧል፡፡ ከ 3 አመታት በላይ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በ1ኛ፣በ4ኛ.በ5ኛ እናበ6ኛ ተከሳሾች ላይ 4አመት ከ 5 ወራት እስራት ቅጣት የበየነ ሲሆን በተቀሩት ሶስት ተከሳሾች ላይ ደግሞ የ4አመት ፅኑ እስራት እንደተበየነባቸው ተዘግቧል፡፡ መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብን በማሰር የግፍ ብይኑን ማስተላለፉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል

በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው  ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው     የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ  ከአእስር መፈታታቸው ተገለፀ

Posted on Jan 22, 2017

በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ ከአእስር መፈታታቸው ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 14/2009 ۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩ ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት 10 የሚሆኑት ከእስር ሲለቀቁ ከወልቂጤ ከተማ የታሰሩት 2 ሙስሊሞች ደግሞ እስከዛሬ ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ መገለፁ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ መሰረትም ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ የተበየነባቸውን የ 3 አመት ከአራት ወር እስራት ጨርሰው በዛሬው እለት መፈታታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ወንድም ጃፈር ዲጋ ከቀናት በፊት ሲፈታ የተቀሩት ሁለቱ ወንድሞችም በዛሬው እለት ተፈተው ከቤተሰባቸው ጋር መቀላቀላቸው ተዘግቧል፡፡ አልሃምዱሊላህ

ሳይፈቱ የቀሩት በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ ከአእስር ተፈቱ

Posted on Jan 22, 2017

ሳይፈቱ የቀሩት በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ ከአእስር ተፈቱ

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 14/2009

۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩

ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት 10 የሚሆኑት ከእስር ሲለቀቁ ከወልቂጤ ከተማ የታሰሩት 2 ሙስሊሞች ደግሞ እስከዛሬ ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ መገለፁ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ መሰረትም ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ የተበየነባቸውን የ 3 አመት ከአራት ወር እስራት ጨርሰው በዛሬው እለት መፈታታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ወንድም ጃፈር ዲጋ ከቀናት በፊት ሲፈታ የተቀሩት ሁለቱ ወንድሞችም በዛሬው እለት ተፈተው ከቤተሰባቸው ጋር መቀላቀላቸው ተዘግቧል፡፡

አልሃምዱሊላህ

በይግባኝ የእስር ቅጣቱ ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰለት የወልቂጤው ወንድም ጃፈር ዲጋ ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉ ተገለፀ

Posted on Jan 19, 2017

በይግባኝ የእስር ቅጣቱ ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰለት የወልቂጤው ወንድም ጃፈር ዲጋ ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉ ተገለፀ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 11/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት 10 የሚሆኑት ከእስር ሲለቀቁ ከወልቂጤ ከተማ የታሰሩት 3 ሙስሊሞች ደግሞ እስካሁን ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ ጠበቃቸው አዲስ መሐመድ ለፍትህ ራዲዬ መግለፆ የሚታወስ ሲሆን ወንድም ጃፈር ዲጋም በዚሁ መሰረት የተበየነበትን የ 3 አመት ከአራት ወር እስራት ሲጨርስ በዛሬው እለት መፈታቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን የተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ ያት ከቀናት ቡሃላ ስለሚጠናቀቅ ቀሪዎቹ ሁለት ወንድሞችም ከእስር ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልፆል፡፡ በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ የወልቂጤ ከተማ ሙስሊም ወንድሞች ወንድም ፋሩቅ ሰኢድ እና ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን ሲሆኑ በቀጣይ ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁ ማረሚያ ቤቱ ለቤተሰቦቻቸው ማስታወቁ...