በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው  ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው     የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ  ከአእስር መፈታታቸው ተገለፀ

Posted on Jan 22, 2017

በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ ከአእስር መፈታታቸው ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 14/2009 ۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩ ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት 10 የሚሆኑት ከእስር ሲለቀቁ ከወልቂጤ ከተማ የታሰሩት 2 ሙስሊሞች ደግሞ እስከዛሬ ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ መገለፁ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ መሰረትም ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ የተበየነባቸውን የ 3 አመት ከአራት ወር እስራት ጨርሰው በዛሬው እለት መፈታታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ወንድም ጃፈር ዲጋ ከቀናት በፊት ሲፈታ የተቀሩት ሁለቱ ወንድሞችም በዛሬው እለት ተፈተው ከቤተሰባቸው ጋር መቀላቀላቸው ተዘግቧል፡፡ አልሃምዱሊላህ

ሳይፈቱ የቀሩት በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ ከአእስር ተፈቱ

Posted on Jan 22, 2017

ሳይፈቱ የቀሩት በይግባኝ የእስር ቅጣታቸው ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰላቸው የወልቂጤዎቹ አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ ከአእስር ተፈቱ

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 14/2009

۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩

ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት 10 የሚሆኑት ከእስር ሲለቀቁ ከወልቂጤ ከተማ የታሰሩት 2 ሙስሊሞች ደግሞ እስከዛሬ ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ መገለፁ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ መሰረትም ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን እና ፋሩቅ ሰኢድ የተበየነባቸውን የ 3 አመት ከአራት ወር እስራት ጨርሰው በዛሬው እለት መፈታታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ወንድም ጃፈር ዲጋ ከቀናት በፊት ሲፈታ የተቀሩት ሁለቱ ወንድሞችም በዛሬው እለት ተፈተው ከቤተሰባቸው ጋር መቀላቀላቸው ተዘግቧል፡፡

አልሃምዱሊላህ

በይግባኝ የእስር ቅጣቱ ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰለት የወልቂጤው ወንድም ጃፈር ዲጋ ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉ ተገለፀ

Posted on Jan 19, 2017

በይግባኝ የእስር ቅጣቱ ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰለት የወልቂጤው ወንድም ጃፈር ዲጋ ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉ ተገለፀ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 11/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት 10 የሚሆኑት ከእስር ሲለቀቁ ከወልቂጤ ከተማ የታሰሩት 3 ሙስሊሞች ደግሞ እስካሁን ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ ጠበቃቸው አዲስ መሐመድ ለፍትህ ራዲዬ መግለፆ የሚታወስ ሲሆን ወንድም ጃፈር ዲጋም በዚሁ መሰረት የተበየነበትን የ 3 አመት ከአራት ወር እስራት ሲጨርስ በዛሬው እለት መፈታቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን የተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ ያት ከቀናት ቡሃላ ስለሚጠናቀቅ ቀሪዎቹ ሁለት ወንድሞችም ከእስር ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልፆል፡፡ በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ የወልቂጤ ከተማ ሙስሊም ወንድሞች ወንድም ፋሩቅ ሰኢድ እና ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን ሲሆኑ በቀጣይ ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁ ማረሚያ ቤቱ ለቤተሰቦቻቸው ማስታወቁ...

ለቅጣት ውሳኔ የተቀጠሩት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት የደሴ ወጣቶች ለጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Jan 17, 2017

ለቅጣት ውሳኔ የተቀጠሩት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት የደሴ ወጣቶች ለጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 9/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በደሴ ከተማ ከ 3 አመት በፊት በመንግስት ደህንነቶች አቀናባሪነት የተገደሉትን ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል ሰበብ እና በሽብር ተግባ ላይ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከደሴ ከተማ ለእስር የተዳረጉት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የሚገኙት 13 ወጣት ሙስሊሞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት በዛሬው እለት ጥር 9 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ በፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጵ 6/1 እንዲሁም 6/7 በመወንጀል የተወሰኑትን ወጣቶች ሼህ ኑር ይማምን ገድላቹሃል፣ኢስላማዊ መንግስት ልትመሰርቱ ነበር እና በደሴ ከተማ ሲካሄዱ የነበሩ የሰደቃ እና አንድነት መድረኮች ላይ ተሳትፋቹሃል በማለት በሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወቃል፡፡

ፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ በመመርመር የቀረበባቸውን በፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጵ 3 እና 1 እንዲሁም አንቀጵ 6 እና 7 በመተላለፍ የሚለውን ክስ በመመርመር በሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በታህሳስ 27 ነበረበው ችሎት ማስተላለፉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ከመዝገቡ ተከሳሽ ከሆኑት መካከል በአምስቱ ላይ ቀርቦባቸው የነበረውም የሽብር ክስ ዝቅ በማድረግ በሌላ አነስተኛ አንቀፅ ጥፈተኛ በሚል ብይን ያስተላለፈባቸው ሲሆን እነሱም አብዱራህማን እሸቱ ፣...

የአንጋፋው የወልዲያው ሰላም መድረሳ የ 3አመት ሙሉ ባጀቱን ሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲን እንደሚሸፍኑ ቃል ገቡ

Posted on Jan 15, 2017

የአንጋፋው የወልዲያው ሰላም መድረሳ የ 3አመት ሙሉ ባጀቱን ሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲን እንደሚሸፍኑ ቃል ገቡ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 7/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ ከአወልያ ቀጥሎ ግዙፉ የሙስሊሙ ተቋም የነበረው የወልዲያ መስጂዶች እና ትምህርት ቤቶች ማዕከል በህገ ወጡ መጅሊስ እና በመንግስት ለአህባሾች እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ ተቋሙን የማዳከም ስራ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በማዕከሉ ስር የነበረውን የሰላም መድረሳን የአካዳሚኩን ክፍል ህዝባዊ ኮሚቴው እንዲያስተዳድረው በማድረግ ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዲከሰትበት በህገ ወጡመጅሊሶች ሲደረግ መቆቱ ይታወሳል፡፡ ማዕከሉ በስሩ የነበሩ የገቢ ማስገኛዎቹን በሙሉ አህባሽ መራሹ መጅሊስ በመውረሱ ትምህርት ቤቱ በአቅም ማነስ ምክንያት ለመዘጋት አደጋ ላይ ወድቆ የነበረ ሲሆን የማዕከሉ መስራች የሆኑት ሃጂ ሲራጅን ጨምሮ ሌሎች በመረባረብ በሳኡዲ አረቢያ ለ 2 ጊዜ ያህል ለመድረሳው ድጋፍ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ እንዲካሄድ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ሰላም ትምህርት ቤት ከፍተኛ ወጪ ያለበት በመሆኑ አመታዊ በጀቱ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ የነበረ ሲሆን የወልዲያ ስታዲዬምን ያስገነቡት ባለሃብት ሼህ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን መድረሳውን ከጎበኙ ቡሃላ የ3አመት ወጪውን ለመሸፈን ቃል መግባታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ሼህ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን የወልዲያ ተወላጅ ሲሆኑ ከሰላም ት/ቤት መስራች ከሆኑት ከሃጂ ሲራጅ ጋር አብሮ አደግ መሆናቸውን መድረሳውን በጎበኙበት ወቅት ገልፀዋል፡፡ መድረሳው አሁን...

የኡስታዝ አህመዲን ጀበል "ሶስቱ አፄዎች" የተሰኘው መፅሃፍ የተገኘበት ሙስሊም ታሳሪ " የህዝብን አመለካከት ለማናወጥ" በሚል ክስ እንደተመሰረተበት ተዘገበ

Posted on Jan 12, 2017

የኡስታዝ አህመዲን ጀበል "ሶስቱ አፄዎች" የተሰኘው መፅሃፍ የተገኘበት ሙስሊም ታሳሪ " የህዝብን አመለካከት ለማናወጥ" በሚል ክስ እንደተመሰረተበት ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 4/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ባሳለፍነው አመት በነሀሴ 6 ቀን 2008 በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኙ ከተማዎች በተካሄደው አፈሳ ለእስር ተዳርገገው ከነበሩ በርካታ ሙስሊም እስረኞች መካከል የኡስታዝ አህመዲን ጀበል "ሶስቱ አፄዎች" የተሰኘው መፅሃፍ የተገኘበት ሙስሊም ታሳሪ" የህዝብን አመለካከት ለማናወጥ" የሚል ክስ ተመስርቶበት እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን አሁንም ድረስ በርካታ ሙስሊሞች እየታፈሱ መሆናቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ወደ ኮምቦልቻ ማረሚያ ቤት እና ወደ ጦላይ የጦር ማሰልጠኛ እየተወሰዱ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በ 2008 በ በመላው የወሎ ከተማዎች በተካሄደው አፈሳ ከደሴ ሰኞ ገበያ አካባቢ ከመኖሪያ ቤቱ የታፈነው ወጣት ሁሴን አራጌ የሚገኝበት ሲሆን ወጣት ሁሴን አራጌ በተያዘበት ወቅት ፓሊስ በማስረጃነት ፣ የአህመዲን ጀበል "ሶስቱ አፄዎች" ፣ የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ "የኦሮሞና አማራ የዘር ግንድ" ፣ እንዲሁም ሌሎች የታሪክ መፅሀፍቶች እና የግል ማስታወሻ ወረቀቶች እንደተያዘበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፖሊስ በፍተሸ ወቅት በቤቱ ያገኛቸውን የታሪክ መፅሃፍቶች በመውሰድ ሃሰተኛ ክስ ለማዘጋጀት ሲጥር የቆየ ሲሆን ከወጣት ሁሴን አራጌ ጋር 22 የሚደርሱ እስረኞችን ለ 81 ቀናት በደሴ ከተማ ማረሚያ ቤት እንዲታሰሩ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡ ፖሊስ በግፍ ለ 81 ቀናት...

የመቱ ነጃሺ መስጂድ ምክትል ኢማም ኡስታዝ ሚስባህ መሀመድ  ከእስር ተፈቱ

Posted on Jan 11, 2017

የመቱ ነጃሺ መስጂድ ምክትል ኢማም ኡስታዝ ሚስባህ መሀመድ ከእስር ተፈቱ

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 3/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኦሮሚያ ክልል የህዝበ ሙስሊሙን የመብት ትግል ተከትሎ በመቱ ከተማ በነጃሺ መስጂድ ይካሄድ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ለእስር ተዳርገው የነበሩት የመቱ ነጃሺ መስጂድ ምክትል ኢማም የሆኑት ኡስታዝ ሚስባህ መሀመድ ከእስር መፈታታቸውን የፍህ ራዲዬ በልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በጥር 23/2008 የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 7 አመት ከ8 ወር የግፍ እስራት በይኖባቸው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የተበየነባቸውን የእስር ጊዜ በአመክሮ በማጠናቀቃቸው ከእስር መፈታታቸው ተዘግቧል፡፤

ኡስታዝ ሚስባህ ለእስር ሲዳረጉ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በመጀመሪያው እስራታቸው ለስምንት ወራት ያክል በኢሊባቡር ዞን ማረሚያ ቤት ቆይተው የዞኑ አስተዳደር በነፃ አሰናብቷቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኡስታዝ ሚስባህ በነፃ ከተለቀቁ ከአራት ቀናት ቆይታ በኋላ ዳግም እንደሚፈለጉ ተነግሮአቸው የዞኑ ፖሊስ ወደ ማረሚያ ቤት ዳግም እንደወሰዳቸው ይታወቃል፡፡

የክስ ሂደታቸው በውል ሳይታወቅ ለስምንት ወራት ያለ ምንም ፍርድ በእስራት ከቆዩ በኋላ ዳግም ሲታሰሩ የኦርሞያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶባቸው ነበር፡፡

በክሱም ላይ ሰዎቹን ለጅሃድ አነሳስታችኋል ፣ህገ መንግስቱን በሃይል ለመናድ ሙከራ አድርጋችኋል በሚል እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ኡስታዝ ሚስባህ መሀመድ በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ተወዳጅ እንደነበሩ እና ብዙ...