በመካ ካዕባ አጠገብ እራሱን ለማቃጠል የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

Posted on Feb 7, 2017

በመካ ካዕባ አጠገብ እራሱን ለማቃጠል የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 30/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በሳኡዲ አረቢያ በተቀደሰችው በመካ ከተማ ኡምራ በማድረግ ላይ የነበረ ግለሰብ ካዕባ አጠገብ በመሆን እራሱን ለማቃጠል ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ግለሰቡ የሳኡዲ ዜጋ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ካዕባ አጠገብ በመሆን እራሱን በቤንዚን አርከፍክፎ ለማቃጠል ያደረገው ሙከራ በሙስሊሙ እና በፖሊሶች ትብብር መክሸፉ ተዘግቧል፡፤ ግለሰቡ ይህን ተግባር የፈፀመው ካዕባ አጠገብ በመሆኑ ካዕባን ለማቃጠል ሙከራ እያደረገ እንደሆነ በማሰብ ጠዋፍ እያደረጉ የነበሩ ሙስሊሞች ተግባሩን በሃይል እንዳስቆሙት ታውቋል፡፤ ግለሰቡ ይህን ተግባር ለመፈፀም የተነሳሳው ወላጅ አባቱ ባለሃብት እና በርካታ ንብረቶች የነበሩት ሰው ሲሆን ወላጅ አባቱ ሲሞት የወላጅ አባቱ ወንድም ልጆቹን በተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም ሙሉ ለሙሉ ያባታቸው ንብረት በመንጠቁ ለተለያዩ አካላቶች አቤቱታውን ቢያቀርብም ሰሚ ባማጣቱ ትኩረት ለመሳብ ብሎ የፈፀመው መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ግለሰቡ ፍትህ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሊሳካለት ባለመቻሉ ካዕባ አጠገብ እራሱን በማቃጠል ትኩረት ለመሳብ እና ብሶቱን ለመግለፅ መሞከሩ ተሰምቷል፡፤ በወቅቱ በቦታው ላይ የነበሩ ጠዋፍ በማድረግ ላይ የነበሩ ሙስሊሞች በግለሰቡ ተግባር እጅግ የተበሳጩ ሲሆን በኢስላም ትልቅ ቦታ በሚሰጠው ቦታ ላይ የዚህ መሰሉን ተግባር መፈፀሙ ቁጣን ቀስቅሶበታል፡፡ የካዕባ ጠባቂ ፖሊሶች ግለሰቡን...

በአዳማ ከተማ በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች የሰርግ ስነ ስርአት ላይ ቅዱስ ቁርአን ተቀዳዶ መገኘቱ ተዘገበ

Posted on Feb 7, 2017

በአዳማ ከተማ በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች የሰርግ ስነ ስርአት ላይ ቅዱስ ቁርአን ተቀዳዶ መገኘቱ ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 30/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በአንድ የሰርግ ስነ ስርአት ላይ ቅዱስ ቁርአን ተቀዳዶ መሬት ላይ ተበትኖ መገኘቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ ቅዱስ ቁርአኑ ተቀዳዶ የተገኘው በአዳማ ከተማ በቁባ መስጂድ አካባቢ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህ ተግባር የተፈፀመውም በአንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች የሰርግ ስነ ስርአት ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በርካታ የቁርአን ገፆች ተቀዳደው መሬቱ ላይ ተበትነው የተገኘ ሲሆን የሰርግ ስነ ስርአትን ለማድመቅ በሚል መሬት ላይ ከሚበተነው ወረቀቶች ጋር አብሮ መበተኑ ታውቋል፡: ይህን ድርጊት ሆን ብለው የፈፀሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተሰማ ሲሆን ድርጊቱ ሙስሊሙ ማህበረሰብን ማስቆጣቱ ታውቋል፡፡ ለሰርግ ስነ ስርአት ማድመቂያ በሚል ወረቀቶች ተቀዳደው መሬት ላይ እንደሚበተኑ የሚታወቅ ሲሆን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬችም ቅዱስ ቁርአንን በብዛት በመቀዳደድ መሬት ላይ እንዲበተን በማደረግ በሰዎች በጫማ እንዲረጋገጥ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡ የዚህ መሰሉ ቁርአንን የመቀዳድ፣የማቃጠል እና ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎት የማዋል ተግባር በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች ዘንድ በብዛት እንደሚፈፀም የሚታወቅ ሲሆን በጅማ ከተማ በተከሰተው የሃይማኖት ግጭትም ዋነኛ መነሻ ምክንያት የነበረው በአንድ የፕሮቴስታንት የእምነት ተቋም ውስጥ ቁርአንን ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎት እንዲውል መፀዳጃ ቤት በር ላይ እንደ...

ወጣት ሙጂብ አሚኖ በሃሰት ምስክርነት ቃል በመስጠት በሚል ለቀረበበት 2ኛ ክስ የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ለሚዚያ 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው

Posted on Jan 31, 2017

ወጣት ሙጂብ አሚኖ በሃሰት ምስክርነት ቃል በመስጠት በሚል ለቀረበበት 2ኛ ክስ የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ለሚዚያ 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 23/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኤልያስ ከድር መዝገብ በተከሰሱት የአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊሞች ላይ በሃሰት እንዲመሰክር የማዕከላዊ ደህንነቶች እና መርማሪዎች አስፈራርተውት ፍድ ቤት ቀርቦ እውነታውን በመመስከሩ በሃሰት በመመስከር ወንጀል በሚል ክስ የተመሰረተበት ወጣት ሙጂብ አሚኖ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተብሎ እንዲከላከል በተወሰነበት መሰረት ሰባራ ባበሩ በሚገኘው የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ የመከላከያ ምስክሩን ለፍርድ ቤቱ ማስደመጡ የሚታወስ ነው፡

አቃቤ ህጉ ወጣት ሙጂብ አሚኖ ፍርድ ቤት ቀርቦ በሃሰት የምስክር ቃሉን ሰጥቷል በማለት ክስ ያቀረበበት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ወንድም ሙጂብ አሚኖም ተገዶ በሃሰት ምስክር መባሉን በድጋሚ ለፍርድ ቤቱ ቢያስረዳም ፍርድ ቤቱ በቀረበበት ክስ ላይ እንዲከላከል በህዳር 24/2008 በተሰየመው ችሎት ውሳኔ እንዳስተላለፈበት የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ለሙጂብ አሚኖ የመከካለያ ምስክር ሆነው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ፣ የሙጂብ አሚኖ እህት ቀደሪያ አሚኖ፣ ኤልያስ ከድር፣ ፋሩቅ ሰኢድ፣አብዱልመጂድ አብዱልከሪም ፣ እህት ሃያተልኩብራ እና ሌሎች ወንድሞችም በችሎቱ መቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ተከሳሽ ሙጂብ አሚኖ...

በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ጉዳያቸውን የያዙት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች ብቁ ለመሆናችሁ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው በመባሉ በድጋሚ ለየካቲት 13 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Jan 28, 2017

በትግራይ ክልል በራያ አዘቦ ወረዳ የታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች ጉዳያቸውን የያዙት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች ብቁ ለመሆናችሁ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው በመባሉ በድጋሚ ለየካቲት 13 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 20/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በራያ አዘቦ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ለእስር የተዳረጉት ኡለሞች እና ኡስታዞች በቀነ ቀሯቸው መሰረት ጥር 18 ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ኡለሞቹ እና ኡስታዞቹ በራያ አዘቦ ወረዳ ኩኩፍቶ በተባለ ቦታ የተያዙ ሲሆን ማይጨው በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

ከታሰሩት ኡለሞች እና ኡስታዞች መካከል ከሳኡዲ አረቢያ ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኡስታዝ አብዱልመናንን ጨምሮ በአፍሪካ ቲቪ የትግርኛ ዳዕዋ በማድረግ የሚታወቀው ኡስታዝ ከድር ሁሴን፣ሼህ አህመድ ዩሱፍ እና ሌሎችም ሙስሊሞች በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

አቃቤ ህጉ ካቀረበባቸው ክስ መካከል ቅሬ(እድር) ላይ አትሳተፉም፣ ዋሃቢያ ናችሁ፣ አብደላህ አል ሃረሪን አትቀበሉም፣ልጆች መልምላችሁ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ትልካላችሁ የሚሉን አሳፋሪ የሃሰት ክሶች እንደሚገኙበት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የመንግስት አቃቤ ህግ የሆነው አቶ ኢድሪስ ጀማል የሃሰት ምስክሮቹን ለማቅረብ በመቸገሩ ከዳኞቹ ጋር በመነጋገር ተከሳሾችም ሆኑ ጠበቆቻቸው ባልተገኙበት ቀነ...

ከ166 በላይ ስደተኞች በሜዴትራንያን ባህር ሰምጠው መሞታቸው ተዘገበ

Posted on Jan 26, 2017

ከ166በላይ ስደተኞች በሜዴትራንያን ባህር ሰምጠው መሞታቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 18/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ከ170 በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ከአቅሙ በላይ የጫነ ጀልባ ቅዳሜ ለሊት በሚዲትራኒያን ባህር ሰምጦ አራት ስደተኞች ብቻ ሲተርፉ ሌሎቹ ህይወታቸውን ማጣታቸውን አንድ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ከተረፉት ስደተኞች ሁለቱ ኤርትራዊ ሁለቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ አንዷ ነፍሠ ጡር እንደሆነች አጀንሲያ አበሻ የተባለው ስደተኞችን የሚረዳው ቡድን መሪ አባ ሙሴ ዘርዓይ፤ የጣሊያን ባህር ሃይልን ጠቅሰው ገልጸዋል፡፡ አዲሱ የፈረንጆች አመት ከገባ ወዲህ የዚህ መሰሉ አደጋ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ባሳለፍነው ቅዳሜ በደረሰ አደጋ 160 የሚደርሱ ስደተኞች ባህር ውስጥ ገብተው መሞታቸው ተዘግቧል፡፡ ስደተኞቹ ከኢትዬጲያ፣ከኤርትራ፣ከሱዳን ፣ከሶማልያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ወደ አውሮፓ ለማቅናት ሲሞክሩ የነበሩ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ጀልባው መያዝ ከሚችለው በላይ ስደተኞች በመጫናቸው ጀልባው ተገልብጦ በርካቶችህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል፡፡ ከሞቱት መካከል በርካታ ሴቶች እንደሚገኙበት የታወቀ ሲሆን አንድ ነፍሰ ጡረ የሆነች ሴት በህይወት መትረፏ ታውቋል፡፡ ከስደተኞቹ መካከል ቁጥራቸው 8 የሚደርሱ ህፃናትም እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ስደተኞች ቁጥር ከ 166 ሊበልጥ እንደሚችል ተዘግቧል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሜዴትራንያን ባህር ከፍተኛ የባህር ሞገድ ያለበት ሲሆን ህገ ወጥ ደላሎች የባህሩን የማዕበል ሁኔታ አደገኛ መሆኑን እያወቁም ስደተኞቹ...

በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት  የደሴ ወጣቶች ከ3 አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተበየናቸው

Posted on Jan 26, 2017

በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት የደሴ ወጣቶች ከ3 አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተበየናቸው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 18/2009

۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩

በደሴ ከተማ ከ 3 አመት በፊት በመንግስት ደህንነቶች አቀናባሪነት የተገደሉትን ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል ሰበብ እና በሽብር ተግባ ላይ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከደሴ ከተማ ለእስር የተዳረጉት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የሚገኙት 13 ወጣት ሙስሊሞች የቅጣት ውሳኔያቸውን ለመስማት በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት በዛሬው እለት ጥር 18 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በታህሳስ 27 በነበራቸው ችሎት በ13ቱም ተከሳሾች ላይ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ብይን ያስተላለፈ ሲሆን አቃቤ ህጉ እና ተከሳሾች የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያቸውን ለፍ/ቤቱ እንዲያቀርቡ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት በሁሉም ታሳሪዎች ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን ከ 3አመት ከ8 ወር እስከ 16 አመት ፅኑ እስራት እንደበየነባቸው ተዘግቧል፡፡

አስራ ሶስቱ ተከሳሾች በሶስት ደረጃ ተከፍለው በተለያዩ አንቀፆች ጥፋተኛ መባላቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህም መሰረት ጥፋተኛ በተባሉበት አንቀፅ የቅጣት ብይን እንደተላለፈባቸው ታውቋል፡፡

በዚህም 8ኛ ተከሳሽን በ16 አመት ፅኑ እስራት፣ 1ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ እና በ15 እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽን በ15 አመት ከ6 ወር፣ 6ኛ እና 11ኛ...

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት 7 ሙስሊም ወንድሞች ላይ ከ 4አመት እስከ 4 አመት ከ 5 ወር የሚደርስ እስራት ቅጣት በየነባቸው

Posted on Jan 23, 2017

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት 7 ሙስሊም ወንድሞች ላይ ከ 4አመት እስከ 4 አመት ከ 5 ወር የሚደርስ እስራት ቅጣት በየነባቸው ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 15/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በጃፈር መሐመድ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው በነበሩት 7 ሙስሊሞች ላይ የእስራት ቅጣት መበየኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ሰባቱ ሙስሊሞች ከጅማ ከተማ ከ 3አመታት በፊት ለእስር የተዳረጉ ሲሆን በሶማልያ ከሚገኘው አልሸባብ ጋር ግንኙት ነበራቸው በሚል በሽብር መከሰሳቸው ታውቋል፡፡ ሰባቱ ተከሳሾች 1. ጃፈር መሐመድ፣ 2. መሐመድኑር፣ 3. ሃጂ መሐመድ ታሚ፣ 4. ሙህዲን ጀማል፣ 5. አህመድ አባቢያ ፣ 6. አንዋር ትዳኔ እና 7. ሼኽጀማል አባ ጫቦ መሆናቸው ታውቋል፡ በኢትዬጲያ ውስጥ የጀሃድ ጦርነት ለማወጅ እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመሄድ ስልጠና ወስደዋል ሲል አቃቤ ህጉ የከሰሳቸው ሲሆን ከጅማ ከተማ ወደ ሶማልያ በመጓዝ ከአልሸባብ ጋር በመቀላቀል ስልጠና ሊወስዱ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል አቃቤ ህጉ ክሱን አቅርቧል፡፡ ከ 3 አመታት በላይ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በ1ኛ፣በ4ኛ.በ5ኛ እናበ6ኛ ተከሳሾች ላይ 4አመት ከ 5 ወራት እስራት ቅጣት የበየነ ሲሆን በተቀሩት ሶስት ተከሳሾች ላይ ደግሞ የ4አመት ፅኑ እስራት እንደተበየነባቸው ተዘግቧል፡፡ መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብን በማሰር የግፍ ብይኑን ማስተላለፉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል