በታላቁ አንዋር እና ኑር መስጂዶች ዙሪያ ከፍተኛ ፍትሻ እና ውክቢያ በወታደሮች ሲፈጸም እንደነበር ተዘገበ

Posted on Mar 18, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 9/2008

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለተከታታይ ጁምአዎች ባደረጋቸው ድንገተኛ ተቃውሞዎች የተደናገጠው መንግስት በዛሬው ጁምአም ድንገተኛ ተቃውሞ እንዳያደርግ ለማሸማቀቅ በሚል በታላቁ ኑር መስጂድ እና በታላቁ አንዋር መስጂድ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ ሲያካሂድ እንደነበር ሪፖርተራቸው ከቦታቸው ዘግቧል፡፡

በዛሬው ዕለት በታላቁ ኑር መስጂድ እና በአንዋር መስጂድ ዙሪያ በከባዱ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች ጥበቃ ሲያካሄዱ የነበረ ሲሆን ለጁምአ ሰላት ወደ መስጂድ የሚሄደውን ሙስሊም ሲፈትሹ እና ሲያዋክቡ እንደነበር ታውቋል፡፡

ባሳለፍነው ጁምኣ ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ ድንገተኛ ተቃውሞ መካሄዱን ተከትሎ ፖሊሶች ሙስሊችን ለማሰር ጥረት በማድረጋቸው በተነሳ ግርግር የጁምአ ሰላት ሰግዶ ከመስጂድ ሲወጣ የነበረውን ህዝበ ሙስሊም ፖሊሶች ሲደበድቡ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በዛሬው ጁምዓ በሁለቱም መስጂዶች ከባድ ጥበቃ ሲካሄድ የነበረ ሲሆን ከመስጂዲቹ ዙሪያ ብቻ ሳይሆን አካባቢው በሙሉ በታጠቁ የፌደራል ፖሊሶች ሲጠበቅ እንደነበር ሪፖርተራችን ከፎቶ ማስረጃ ጋር ዘግቧል፡፡

ወደ መስጂዶቹ ለጁምዓ ለሰላት የሚመጡ ሙስሊሞችን በሁሉም አቅጣጫ ፖሊሶች ከፍተኛ ፍተሻ ሲያደርጉ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ከመስጂዱ ውጪ ለሰላት ማንጠፍ አይቻልም በሚል ፖሊሶቹ ውክብያ ለመፍጠር ሞከረው እንደነበር ተገልፆል፡፡

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በፖሊሶች የሚደረግበትን ውክብያ በመታገስ የጁምዓ ሰላቱን በሰግዶ በሰላም...

መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ የማህበራዊ ሚዲያዎችን መዝጋቱ ተገለጸ

Posted on Mar 18, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 9/2008 በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ መንግስት ማህበራዊ ሚዲያዎችን መዝጋቱን ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማዳከም እና የሙስሊሙን ትግል ለማዳከም በማሰብ መንግስት ህዝቡ መረጃዎችን ይለዋወጡበታል የሚላቸውን ማህበራዊ ሚዲያዎች በሻሸመኔ ከተማ መዝጋቱ ታውቋል፡፡ ህዝቡ በብዛት የሚጠቀምበት የነበረውን Whats Up አገልግሎት እንዲዘጋ መንግስት ያደረገ ሲሆን VIber፣IMO፣ Tango, Skypi እና ሌሎች መረጃ መለዋወጫ መንገዶችንም ከ 15 ቀናት በላይ የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎችን መጠቀም አለመቻላቸውን ለፍትህ ራዲዬ ገልጸዋል፡፡ መንግስት በከተማው የሚፈጽማቸውን ግፎች እና በደሎች በቀላሉ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በፍጥነት እየተዳረሰ መምጣቱ ለመንግስት እራስ ምታት የሆነ ሲሆን እነዚህን ፈጣን የመረጃ መለዋወጫ መንገዶች በኢትዬጲያ ውስጥ እንዳይሰሩ በማድረግ ለማስቆም እየጣረ መሆኑ ተገልፆል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሚበዛበት በዚህ ከተማ የሙስሊሙን ትግል እና በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከመረጃ ውጪ በማድረግ ትግሉን ለማቀዛቀዝ መንግስት እየጣረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የከተማዋ ነዋሪዎችም እየተደረገባቸው የሚገኘውን የሚዲያ አፈና በመበጣጠስ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የዚህ መሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን የመዝጋት እንቅሰቃሴ በስፋት በተለያዩ ኦሮሚያ ከተሞች እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን ህዝቡን ከመረጃ ውጪ በማድረግ እንቅስቃሴውን ለማፈን መንግስት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሻሸመኔ...

ታላቁ የደሴ አሊም አባባ ሼኽ አደም ወደ አኼራ ሄዱ

Posted on Mar 6, 2016

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

ፍትህ ራዲዬ/የካቲት 26/2008 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በደሴ ከተማ በአረብ ገንዳ መስጂድ ከ 40 አመት በላይ በኢማምነት እና ህዝበ ሙስሊሙን በቁርአን ተፍሲር እና በሌሎች ኢስላማዊ ትምህርቶችን በማስተማር የሚታወቁት ታላቁ አሊም ሼኽ አደም ሙሳ(አባባ አደም) ባደረባቸው ግመም በኢትዬ ጠቢብ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ወደ አኼራ መሄዳቸው ታውቋል፡፡

በደሴ ከተማ ሙስሊሙም ሆነ የሌላ እምነት ተከታዬች እጅግ የሚወዷቸው እና የሚያከብሯቸው እኚህ ታላቅ ኢማም የኢህአዴግ መንግስት በደሴ ሙስሊሞች ላይ በፈጸመው የሽብር ጥቃት ለ40 አመታት ሲያገለግሉበት ከነበረው ከመስጂድ ኢማምነታቸው እንዲነሱ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

የደሴ ህዝብ አባባ ሼኽ አደም እያለ የሚጠራቸው እኚህ ታላቅ ኢማም ባደረባቸው ህመም በተለያዩ ጊዜያቶች ህክምና ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ከዚህ በፊት ህመሙ ጠና ሲልባቸው ወደ ታይላንዳ ባንኮክ በማምራት ህክምናቸውን መከታተላቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም የዲስክ መንሸራተት የሚል ህመም ገጥሟቸው የነበረ ሲሆን በደረሰባቸው የዲስክ መንሸራተትም አንድ የጀርባ አጥንታቸው ከቦታው ለቆ በመውጣቱ መራመድ እንዳይችሉ አድረጓቸው የነበረ ሲሆን በታይላንድ ባንኮክ ሆስፒታል በተደረገላቸው የተሳካ የቀደ ጥገና ሙሉ አፊያቸው ተመልሶላቸው ነበር፡፡

እኚህ የእድሜ ባለጸጋ ታላቅ አሊም በድጋሚ ባደረባቸው ህመም ወደ ሆስፒታል ገብተው ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቢቆዩም የዚህ አለም ቆይታቸው ማብቂያ በመድረሱ...

ለደሴ ከተማ ሙስሊሞች ምስክር ለመሆን ወደ ቃሊቲ ማ/ቤት የመጡት...

Posted on Mar 4, 2016

ለደሴ ከተማ ሙስሊሞች ምስክር ለመሆን ወደ ቃሊቲ ማ/ቤት የመጡት በነኤልያስ የክስ መዝገብ የሚገኙት ሙስሊሞች ፂማቸውን እንዲላጩ ማ/ቤቱ ጫና ሲያደርግባቸው እንደነበር ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/የካቲት 25/2008 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በሃሰት የሽብር ወንጀል ተመስርቶባቸው የ 7 አመታት የግፍ እስራት የተበየነባቸው በኤልያስ ከድር መዝገብ የሚገኙት ሙስሊሞች በሼህ ኑሩ ግድያ በሃሰት ለተወነጀሉት የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች የመከላከያ ምስክር ለመሆን ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲመጡ ከተደረገ ቡሃላ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር እነዚህን ሙስሊሞች ከሌላው በመነጠል ከፍተኛ ጫና እያደረሰባቸው መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከህግ አግባብ ውጪ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ለምስክርነት የመጡት በኤልያስ ከድር መዝገብ የሚገኙትን 7 ሙስሊሞች ፂማቸውን እንዲላጪ እና ሱሪያቸውን እንዳያሳጥሩ ሲያስገድዳቸው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር እናንተ አሸባሪዎች፣ እነዚህ የድምፃችን ይሰማ አባላት ናቸው፣ፂማችሁን መላጨት አለባችሁ፣ሱሪያችሁንም ማስረም አለባችሁ በማለት በሃይል መብታቸውን ለመግፈፍ ጥረት ሲያደርግባቸው እንደነበር ተገልፆል፡፡

ሰባቱ ሙስሊሞች ግን ፂማችንን እንድንላጭ እና ሱሪያችንን እንድናስረዝም የሚያስገድደን ህግ ካላችሁ አምጡና አሳዩን፡፡ እኛ ሙስሊሞች ነን፡፡ ፂማችሁን ተላጩ የሚል ህግ ቢኖር እንኳን እኛ ፂማችንን አንላጭም፣ሱሪያችንንም አናስረዝምም፡፡ እነዚህ ነገሮች የሃይማኖታችን...

በአማን አሰፋ መዝገብ የጥፋተኝነት ብይን የተሰጠባቸው ሙስሊሞች ....

Posted on Mar 3, 2016

በአማን አሰፋ መዝገብ የጥፋተኝነት ብይን የተሰጠባቸው ሙስሊሞች የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔያቸውን ለመስማት ለየካቲት 30 ቀነ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ፍትህ ራዲዬ/የካቲት 24/2008 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በኢትዬጲያ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል በሚል በነ አማን አሰፋ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሙስሊሞች የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በ 24ቱ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ካስተላለፈ ቡሃላ በዛሬው ዕለት የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔውን ለማስተላፍ ለየካቲት 30 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

28 ሙስሊሞች በተከሰሱበት የክስ መዝገብ 14 የሚሆኑት በሌሉበት ክሳቸው ሲታይ የቆየ ሲሆን አቃቤ ህጉ ላቀረበባቸው ክስ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ናቸው በሚል እንዲከላከሉ ወስኖባቸው ነበር፡፡

በአማን አሰፋ የክስ መዝግብ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደን ጨምሮ 24 ሙስሊሞች የጥፋተኝነት ብይን የተሰጠባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔነውን ከማስተላለፉ በፊት የአቃቤ ህጉን እና የተከሳሾችን የቅጣት ማክበጃ እና ማቅያ ለመስማት ለየካቲት 18 ቀነ ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወስ ሲሆነ በቀነ ቀጠሯቸው መሰረትም ፍርድ ቤት ቀርበው አቃቤ ህጉ የቅጣት ማቅለያውን ለፍርድ ቤቱ ማቅረቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህጉን የቅጣት ማክበጃ በፅሁፍ ከተቀበለ ቡሃላ ተከሳሾችም እያንዳንዳቸው የቅጣት ማቅለያቸውን ለፍርድ ቤቱ በፅሁፍ በፅህፈት ቤቱ በኩል እንዲያስገቡ እስከ የካቲት 24 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን ተከሳሾችም ያላቸውን...