በሼህ ኑሩ ግድያ የተወነጀሉት የደሴ ከተማ ሙስሊሞች የዞን 9ጦማሪ የሆነውን በፍቃዱ ዘሃይሉን ጨምሮ ሁለት ምስክሮችን ለፍርድ ቤቱ አስደመጡ

Posted on May 11, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት 3/2008

በደሴ ከተማ ከ 2 አመት በፊት በመንግስት ደህንነቶች አቀናባሪነት የተገደሉትን ሼህ ኑሩን ገድላቹሃል በሚል ሰበብ ከደሴ ከተማ ለእስር የተዳረጉት በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የሚገኙት ሙስሊሞች 13 ወጣት ሙስሊሞች አቃቤ ህጉ ባቀረበባቸው የሽብር ክስ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ በወሰነባቸው መሰረት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለፍርድ ቤቱ እያስደመጡ ሲሆን ቀሪ ምስክሮቻቸውን ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት በዛሬው ዕለት እሮብ ግንቦት 3/2008 በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡

ከጥቅምት 29 ጀምሮ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለፍርድ ቤቱ እያስደመጡ የሚገኙ ሲሆን እስካሁን ለፍርድ ቤቱ ለማቅብ ከተዘጋጁት 200 ምስክሮች መካከል ከ 70 በላይ ምስክሮችን ማስደመጣቸው ታውቋል፤

ከየካቲት 17 ጀምሮ ፍርድ ቤቱ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቀነ ቀጠሮውን ሲያራዝም የቆየ ሲሆን ቀሪ ምስክሮቻቸውን እንዲያሰሙ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ግንቦት 3 በሰጠው ቀነ ቀጠሮ መሰረት ሁለት ምስክሮቻቸውን በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በመገኘት ማስደመጣቸውን ፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ኮሚቴዎቻችን ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ፣ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እንዲሁም የአዳማው ተከሳሽ ወንድም አብዱልአዚዝ ፍርድ ቤት በመገኘት ለኮሚቴዎቻችን የመከላከያ ምስክር በመሆን በችሎት ቀርበው እንደመሰከሩላቸው መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በኤልያስ ከድር መዝገብ...

በአፋር ክልል የአሳይታው ቢላል መስጂድ ግንባታን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርርበ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ

Posted on May 10, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ግንቦት2/2008 በአፋር ከልል የአይሳኢታው ቢላል መሰጅድን ግንባታ እሰከ ነህሴ 30/2008 ድረሰ ለመጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተካሄደ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በታላቁ ሰሀባ በሃበሻዊው ቢላል ስም የተሰየም የረህ ባለ ፎቅ መስጂ ተገንብቶ ባጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጥ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ሙስሊሙ ማህረሰብም መስጂዱን ለማጠናቀቅ አቅሙ በፈቀሰደው መልኩ ድጋፍ እንዲያደግ አሰረ ኮሚቴዎቹ ጥሪ አቅረበዋል፡፡

በአፋር ክልል የአክፍሮት ሃይላት እምነታቸውን የሚያራምዱበት ቤተ ክርስቲያኖችን በመገንባት ሙስሊሙን ለማክፈር በስፋት እየተንቀሳቀሱ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት ከ 99.6ፐርሰንት በላይ ሙስሊም በሆነባት አፋር ክልል መስጂድ ለመገንባት አቅም እጥረት መፈጠሩ አሳዛኝ መሆኑ ተገልፆል፡፡

የመስጂዱ ግንባታን ለማጠናቀቅ የተለያዩ አካላት ርብርብ እያደረጉ ሲሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራምም ከዚህ ቀደም በአፋር በአሳይታ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

ይህን መስጂድ ግንባታ አጠናቆ በ 2009 ለሙስሊሙ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማደረግ በአድሰ መልክ ፈጣን እንቅሰቃሴ በታቀደው መልኩ የቡሉኬት ግንባታ የተጀመረ ሲሆን በዚህ ሁለት ሳምንት ውሰጥ የግንባታ ሥራ ለማጠናቀቅ መታቀዱ ታውቋል፡፡

ይህን ታላቅ መስጂድ ግንባታው እንዲጠናቀቅ በገንዘብ : በማቴሪያል : በጉልበት ሙስሊሙ እንዲረዳ ጥሪ የቀረበ ሰሲሆን ለመስጂዱ ግንባታ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ሙስሊሞች በመሰጅዱ ሥም በተከፈተው የኢትዬጲ ንግድ ባንክ በአሳይታ...

በአዳማ ከተማ ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

Posted on May 8, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 30/2008 በኢድ ሰላት በሚሰገድበት በአዳማው ኡመር መስጂድ ታላላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ዝግጅቱ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አስተበባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን ታላላቅ ዳዒያንም በእንግድነት ተጋብዘዋል፡፡

ዝግጅቱ በየአመቱ የሚካሄድ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይም ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ፣ ኡስታዝ መሀመድ ፈረጅ፣ኡስታዝ ሃይደል እና ሌሎችም ተካፍለዋል፡፡

በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ለማበረታታት ታስቦ የተዘጋጀ ፕሮግራም ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአዳማ ከተማ ሙስሊም በፕሮግራም ላይ ተካፍሏል፡፡

አላሁ አክበር

የሼኽ ሆጀሌ መስጂድ የቀድሞ ኮሚቴ የነበሩት ሼህ ዩሱፍ ሙዘሚልን ጨምሮ 6 ሙስሊሞች ከጁምዓ ሰላት በኋላ ትፈለጋላችሁ በሚል በፖሊስ መወሰዳቸው ተዘገበ

Posted on May 6, 2016

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 28/2008

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የሆኑት እና የሼህ ሆጀሌ መስጂድን ከ 20 አመት በላይ በአስተዳዳርነት የመሩት ሼህ ዩሱፍ ሙዘሚልን ጨምሮ 6 ሙስሊሞች ከጁምዓ ሰላት ቡሃላ በፖሊሶች ተፈለጋላችሁ በሚል ወደ ፖሊስ ጣብያ መወሰዳቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ህገ ወጡ አዲስአበባ መጅሊስ መስጂዱንበጉልበት ከተረከቡ ወዲህ መስጂዱንለማዳከም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ይህን ተግባራቸውንም ለማስቆም በሚል ትላንት ሃሙስ ሚያዚያ 27/2008 የመስጂዱ ጀምዓ እና የአካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎች ከዙሁር ሰላት በኋላ በመሰባሰብ መስጂዱን እየረበሹ ለሚገኙት የአህባሽ አቀንቃኝ ለሆኑት ለአቶ ሲራጅ እና ለግብረአበሮቻቸው እንፈልጋቹሃለን በሚል ሙስሊሙ ያልወከላቸው እና የማይፈልጋቸው መሆኑን በመግለፅ መስጂዱን እንዲለቁላቸው መጠየቃቸው ታውቋል፡፡

የመስጂዱ አካባቢ ነዋሪዎች ቁጭት በተሞላበት መንገድ መስጂዱን በደህንነቶቸ እና በፖሊስ ሃይል በመታገዝ ቁልፍ ሰብራችሁ ቀይራቹሃል.፣ ለ 1 ወር ያህልም መስጂዱን ይዛችሁ አይተናቹሃል ፣ እስካሁን እየሰራችሁ የሚገኘው ተግባር ሁሉ ከኢስላም ጋር የሚፃረር እና መስጂዱን የሚያዳክም በመሆኑ በግዳጅ በመስጂዳችን ላይ ልትጫኑብን አይገባም ፣ከበላይ አካል ጋር ተነጋግረን መፍትሄ እስክናስመጣ መስጂዳችን እኛ በመረጥነው አላህን በሚፈሩ ሰዎች እንጂ መመራት ያለበት በካድሬ እና እስልምናን ምንም በማያውቁ ግለሰቦች መሆን የለበትም በሚል ለአቶ...

በነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች የአቃቤ ህጉ ምስክሮችን ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ለግንቦት 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Apr 28, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 20/2008

ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ለእስር የተዳረጉት በነብዩ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ዛሬ ሚያዚያ 20 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በ ሚያዚያ 5 በነበራቸው ቀነ ቀጠሮ አቃቤ ህጉ ምስክሮቹን ሊያቀርብ ባለመቻሉ ለዛሬ ሚያዚያ 20ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

በነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሱት 7 ሙስሊሞች 1. ነብዩ ሲራጅ 2. ሰፋ በደዊ 3. መሃመድ ሰዒድ 4. ሰላሃዲን ከድር 5. ሙጂብ አደም እረሺድ 6. ከድር ታደለ 7. አህመድ ኡመር መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ኮሚቴውን በሃይል ለማስፈታትን እና ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል ብላቹሃል በሚል በሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነዚህ 7 ሙስሊሞች ጉዳያቸው በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት እየታየ ሲሆን ጉዳዩን ሲመለከቱት የነበሩት ዳኛ ገለልተኛ ሆነው ጉዳዩን ሊመለከቱ ባለመቻላቸው ተከሳሾች ችሎቱ እንዲቀየርላቸው ጠይቀው እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ችሎቱ ይቀየርልን የሚለውን የተከሳሾች አቤቱታ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት የረጅም ወራትቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በመጋቢት 16 በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ያቀረቡትን አቤቱታ በመቀበል ጉዳያቸው በሌላ ችሎት እንዲታይ ብይን መስጠቱ ታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ክስ ያቀረበው አቃቤ ህጉ ላቀረበው ክስ ያስረዱልኛል ያላቸውን...

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱ ሙስሊሞች ለግንቦት18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Apr 27, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 19/2008 በደህንነቶች ከያሉበት ታፍነው ለእስር የተዳረጉት የአዲስ አበባ እና የጅማ ከተማ ሙስሊሞች ተቋርጦ የነበረው ችሎት እንዲቀጥል ተወስኖ የአቃቤ ህጉ ቀሪ ምስክሮቹን ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት በዛሬው ቀነ ቀጠሮ መያዚያ 19 ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ ላቀረበው ክስ የስረዱልኛል ያላቸውን 30 የሰው እና ተያያዝ ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ ለማቅረብ በክሱ ላይ አስፍሮ የነበረ ቢሆንም 16 የሚሆኑትን ብቻ ካቀረበ ቡሃላ ቀሪ ምስክሮቹን ላገኛቸው አልቻልኩም በማለቱ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥ አንደነበር ይታወቃል፡፡

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱት 20 ሙስሊሞች ዋና ዳኛው ገለልተኛ አለመሆናቸውን፣ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት አሸባሪ ብለው በመጥራታቸው፣ በተደጋጋሚ በማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች የሚፈፀምባቸውን ግፍ እና በደል ለፍርድ ቤቱ በቃል እና በፅሁፍ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሊሰጥ ባለመቻሉ ችሎቱ እንዲቀየርላቸው በጠየቁት መሰረት ጉዳያቸው ሲታይ ከነበረው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ወደ 14ኛው ምድብ ችሎት እንዲቀየርላቸው መደረጉ ተዘግቧል፡፡

በዛሬው ቀነ ቀጠሮ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት 19ኙ ሙስሊሞች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛው ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን በቃሊቲ ማ/ቤት ታስራ የምትገኘው ብቸኛዋ የመዝገቡ ሴት ተከሳሽ የሆነችው ሃያተል ኩበራ ግን በችሎቱ ሳትቀርብ መቅረቷን የፍትህ ራዲዬ...

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱት 20 ሙስሊሞች በነገው ዕለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለፀ

Posted on Apr 26, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 18/2008

በደህንነቶች ከያሉበት ታፍነው ለእስር የተዳረጉት የአዲስ አበባ እና የጅማ ከተማ ሙስሊሞች ተቋርጦ የነበረው ችሎትእንዲቀጥል ተወስኖ የአቃቤ ህጉ ቀሪ ምስክሮቹን ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት በነገው ዕለት ሚያዚያ 19 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ ላቀረበው ክስ የስረዱልኛል ያላቸውን 30 የሰው እና ተያያዝ ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ ለማቅረብ በክሱ ላይ አስፍሮ የነበረ ቢሆንም 16 የሚሆኑትን ብቻ ካቀረበ ቡሃላ ቀሪ ምስክሮቹን ላገኛቸው አልቻልኩም በማለቱ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥ አንደነበር ይታወቃል፡፡

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱት 20 ሙስሊሞች ዋና ዳኛው ገለልተኛ አለመሆናቸውን፣ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት አሸባሪ ብለው በመጥራታቸው፣ በተደጋጋሚ በማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች የሚፈፀምባቸውን ግፍ እና በደል ለፍርድ ቤቱ በቃል እና በፅሁፍ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሊሰጥ ባለመቻሉ ችሎቱ እንዲቀየርላቸው መጠቃቸው ይታወሳል፡፡

በየካቲት 14 በነበረው ችሎት ተከሳሾቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ዳኛው ከዚህ ቡሃላ ጉዳዩን እንደማይመለከተው በመግለፅ ወደ ሌላ ችሎት መዘዋወሩን በጠበቆች በኩል በፍርድ ቤቱ ፅ/ ቤት በኩል እንደደረሳቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን እንዲመለከቱ የተመራላቸው ዳኞችም በስራ መደራረብ ምክንያት ጉዳዩን ሊመለከቱት እንደማይችሉ በማስታወቃቸው ጉዳዩ ለሬጀስትራር አና ለከፍተኛው ፍርድ...