በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱ ሙስሊሞች ለግንቦት18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

Posted on Apr 27, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 19/2008 በደህንነቶች ከያሉበት ታፍነው ለእስር የተዳረጉት የአዲስ አበባ እና የጅማ ከተማ ሙስሊሞች ተቋርጦ የነበረው ችሎት እንዲቀጥል ተወስኖ የአቃቤ ህጉ ቀሪ ምስክሮቹን ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት በዛሬው ቀነ ቀጠሮ መያዚያ 19 ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ ላቀረበው ክስ የስረዱልኛል ያላቸውን 30 የሰው እና ተያያዝ ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ ለማቅረብ በክሱ ላይ አስፍሮ የነበረ ቢሆንም 16 የሚሆኑትን ብቻ ካቀረበ ቡሃላ ቀሪ ምስክሮቹን ላገኛቸው አልቻልኩም በማለቱ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥ አንደነበር ይታወቃል፡፡

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱት 20 ሙስሊሞች ዋና ዳኛው ገለልተኛ አለመሆናቸውን፣ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት አሸባሪ ብለው በመጥራታቸው፣ በተደጋጋሚ በማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች የሚፈፀምባቸውን ግፍ እና በደል ለፍርድ ቤቱ በቃል እና በፅሁፍ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሊሰጥ ባለመቻሉ ችሎቱ እንዲቀየርላቸው በጠየቁት መሰረት ጉዳያቸው ሲታይ ከነበረው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ወደ 14ኛው ምድብ ችሎት እንዲቀየርላቸው መደረጉ ተዘግቧል፡፡

በዛሬው ቀነ ቀጠሮ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት 19ኙ ሙስሊሞች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛው ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን በቃሊቲ ማ/ቤት ታስራ የምትገኘው ብቸኛዋ የመዝገቡ ሴት ተከሳሽ የሆነችው ሃያተል ኩበራ ግን በችሎቱ ሳትቀርብ መቅረቷን የፍትህ ራዲዬ...

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱት 20 ሙስሊሞች በነገው ዕለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለፀ

Posted on Apr 26, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 18/2008

በደህንነቶች ከያሉበት ታፍነው ለእስር የተዳረጉት የአዲስ አበባ እና የጅማ ከተማ ሙስሊሞች ተቋርጦ የነበረው ችሎትእንዲቀጥል ተወስኖ የአቃቤ ህጉ ቀሪ ምስክሮቹን ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት በነገው ዕለት ሚያዚያ 19 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

አቃቤ ህጉ ላቀረበው ክስ የስረዱልኛል ያላቸውን 30 የሰው እና ተያያዝ ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ ለማቅረብ በክሱ ላይ አስፍሮ የነበረ ቢሆንም 16 የሚሆኑትን ብቻ ካቀረበ ቡሃላ ቀሪ ምስክሮቹን ላገኛቸው አልቻልኩም በማለቱ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥ አንደነበር ይታወቃል፡፡

በከድር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱት 20 ሙስሊሞች ዋና ዳኛው ገለልተኛ አለመሆናቸውን፣ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት አሸባሪ ብለው በመጥራታቸው፣ በተደጋጋሚ በማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች የሚፈፀምባቸውን ግፍ እና በደል ለፍርድ ቤቱ በቃል እና በፅሁፍ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሊሰጥ ባለመቻሉ ችሎቱ እንዲቀየርላቸው መጠቃቸው ይታወሳል፡፡

በየካቲት 14 በነበረው ችሎት ተከሳሾቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ዳኛው ከዚህ ቡሃላ ጉዳዩን እንደማይመለከተው በመግለፅ ወደ ሌላ ችሎት መዘዋወሩን በጠበቆች በኩል በፍርድ ቤቱ ፅ/ ቤት በኩል እንደደረሳቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን እንዲመለከቱ የተመራላቸው ዳኞችም በስራ መደራረብ ምክንያት ጉዳዩን ሊመለከቱት እንደማይችሉ በማስታወቃቸው ጉዳዩ ለሬጀስትራር አና ለከፍተኛው ፍርድ...

በወሎ ቦረና ለጋምቦ ወረዳ ገነቴ ከተማ የሚገኘው የመስጂደ ረህማን በአዲስ መልኩ ተገንብቶ ለምረቃ በቃ

Posted on Apr 22, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 13/2008

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በወሎ ቦረና ለጋምቦ ወረዳ ገነቴ ከተማ በሰላም በር በሚገኘው መስጅደ ረህማን በአዲስ መልኩ ተገንብቶ በዛሬው ዕለት ጁምዓ መመረቁን ፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

መስጂዱ በአካባቢው ሙስሊሞች ርብርብ በአዲስ መልኩ የተገነባ ሲሆን በዛሬው ዕለት ጁምዓ ታላላቅ ኡለሞች እና ኡስታዞች በተገኙበት መመረቁ ተዘግቧል፡፡

ይህ መስጂድ ከዚህ ቀደም በከተማው ታላቅ አሊም የነበሩት ሼህ ሎጎ በሺዎች የሚቆጠሩ ደረሶችን በመያዝ ኢልም ሲያስተምሩበት የነበረ ቦታ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሳቸው ልጅ እና ደረሳቸው ተረክቦ በርካታ ደረሶችን በማቅራት ላይ እንደሚገኝ የአካባቢው ሙስሊሞች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በምረቃ ስነ ስርቱ ላይ ተወዳጁ ዳዒ ኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ የተገኘ ሲሆን በመስጂዱ ለተገኘው ህዝበ ሙስሊም ጠቃሚ ትምህርት ማቅረቡ ታውቋል፡፡

የወረዳው የመንግስት ባለስልጣንም በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በመገኘት ተስፋ ሰጪ ንግግር ማድረጉ የተዘገበ ሲሆን የመንግስት ባለስልጣኑ በተናገረው ንግግር የዝግጅቱ ታዳሚያን መደሰታቸውን ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ መስጂዱ በሃገር ውስጥ ተወላጆች ተገነባ ሲሆን መስጂዱን ወደፊትም ለማጠናቀር በመስጂዱ ተምረው በየቦታው የተበተኑ ሙስሊሞችም የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡ ተዘግቧል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኘውን ወንድም ስለ መስጂድ ምረቃቱ አነጋግረል፡፡ ዝርዝሩን በምሽቱ ፕሮግራማችን ይጠብቁን

...

ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ተልኮ በተሰጠው እስረኛ በመቆፈሪያ አንገቱን ተመቶ እንደነበር ተገለፀ

Posted on Apr 16, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 7/2008

በኡስታዝ አቡበከር አህመድ የክስ መዝገብ 7 አመት እስራት በግፍ ተፈርዶበት በዝዋይ ማረሚያ ቤት የሚገኘው ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በማረሚያ ቤቱ ታስሮ በሚገኝ እስረኛ በመቆፈሪያ አንገቱን መመታቱን ለፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ገልፆል፡፡

ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ሃሙስ እለት መጋቢት 6 ከአስር ሰላት በፊት ዘያሪዎቹን አናግሮ ለእስር ሰላት ወደ ማረሚያ ቤቱ ወደሚገኘው የሰላት ስፍራ በማምራት ላይ በነበረበት ወቅት የ 12 አመት እስራት የተበየነበት አንድ እስረኛ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪን ጠብቆ አንገቱን በመቆፈሪያ ብረት እንደወጋው የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ግለሰቡ ከኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ጋር ምንም አይነት ንክኪም ሆነ ግንኙነት ከዛ ቀን በፊት ያልነበረው ሲሆን በደህንነቶች ተልዕኮ ተሰጥቶት ሊሆን እንደሚችል ተገልፆል፡፡

ግለሰቡ በያዘው መቆፈሪያ የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪን አንገት ከመታ በኋላ ኡስታዝ ኑረ ቱርኪ ለ 2 ሰዓታት ያህል እራሱን ስቶ ወድቆ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

በማረሚያ ቤቱ 12 አመት እስራት ተበይኖበት ታስሮ የሚገኘው ይህ ግለሰብ የኡስታዝ ኑሩ ቱርን አንገት በመምታት ከጣለው በኋላም ሆዱን በመቆፈሪያ በተደጋጋሚ ለመውጋት ሙካራ ማድረጉ የተዘገበ ሲሆን በወቅቱ መሬት ላይ ወድቆ ሲንከባለል ሆዱን ሳይወጋው ሊተርፍ መቻሉ ታውቋል፡፡

የየቲሞቸ አባት በመባል የሚታወቀው ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ግለሰቡ አንገቱን የመታበት መቆፈሪያ ስለቱ ያልተሞረደ በመሆኑ ከፍተኛ ጉዳት ያላደረሰበት ሲሆን በአላህ ፈቃድ ግለሰቡ...

የፌዴራል ጉዳዬች ሚኒስቴር ወይስ የወንጌል ሚኒስቴር

Posted on Apr 12, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ2/2008

በፌዴራልና በአርብቶ አደሮች ጉዳዬች ሚኒስትር የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ከቀናት በፊት mani የተሰኘ ተቋም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ ክርስቲያኖች ወንጌል ላልደረሰባቸው አካባቢዎች ለማድረስ በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዬች ሚኒስተር የብዙሀን የሙያ ማህበራትና የሀይማኖት ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አቀል ወግሪስ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን አስነብቦናል፡፡ ይህ ክስተት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ለምን ተቋቋመ አላማውስ ምንድን ነው ብሎ ለመጠየቅ የሚያስገድድ ነው፡፡ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሀሳብና ትዕዛዝ ሲዋቀር በርካቶች በሚስተር ደረጃ መዋቀር የሚገባው መሰሪያ ቤት እንዳልሆነ ገልጸው ሲቃወሙ ነበር፡፡ በወቅቱም ሰለ ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ስልጣን፣የስራ መስክ እና ተያያዥ ጉዳዬች ግልፅ አልተደረጉም ነበር፡፡ የፌዴራል ጉዳዬችንና የአርብቶ አደሮችን ልማት አንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ማጠቃለሉም ጥያቄ አስነስቶ ነበር፡፡ ሰለ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ለማውራት አስተዳደራዊ መዋቅሩንና ያከናወናቸውን ተግባራት በጥንቃቄ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ አዲሱ ካቢኔ በ2008 መጀመሪያ ላይ በጠ/ሚኒስተር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከመዋቀሩ በፊት በዚህ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ውስጥ በሚኒስተር ማዕረግ ደረጃ ከሚሰሩ ባለስልጣናት መካከል ከወ/ሮ ሽታዬ ውጪ ሁሉም የፐሮቴስታንት አምነት ተከታይ ናቸው፡፡ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመበት ቅፅበት አንስቶ በፌዴራል ጉዳዬችና በአረብቶ አደር ልማት ጉዳዬች ሳይሆን...

አህባሽ መራሹ መጅሊስ በፌደራል ፖሊስ እና በደህንነቶች በመታጀብ በሼህ ሆጀሌ መስጀድ አዲስ የጥበቃ ሰራተኛ በጉልበት ማስገባቱ እና የመስጂዱን በር ቁልፍም በጉልበት መቀየራቸው ታወቀ

Posted on Apr 11, 2016

ፍትህ ራዲዬ/ሚያዚያ 2/2008 በህዝበ ሙስሊሙ መዋጮ የተገነባው ታላቁ የሼህ ሆጀሌ መስጂድ በግዳጅ ለአህባሽ መራሹ መጅሊስ መንግስ በፍርድ ቤቱ በኩል እንዲሰጥ ካደረገ ወዲህ መስጂዱን ሙሉ ለሙሉ ከሙስሊሙ በመንጠቅ የአህባሽ ማሰራጫ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተጠናከሮ መቀጠሉን ፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት አህባሾቹ ከፍተኛ ግብረሃይል በማሰባሰብ ወደ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ በመሄድ በጉልበት የመስጂዱን ቁልፍ በጉልበት መረከባቸው ተዘግቧል፡፡ የአህባሽ አመራሮች፣የፌደራል ፖሊሶች እና ደህንነቶች ወደ መስጂዱ በመግባት የመስጂዱን ቁልፍ በግዳጅ እንዲያስረክቧቸው የጠየቁ ሲሆን ቁልፉን ለኮሚቴው እንጂ ለንናት አናስረክብም የሚል ምላሽ ቢሰጣቸውም ደህንቶቹ እና የአህባሽ መጅሊስ አመራሮቹ ወዳችሁ የማታስረክቡ ከሆነ ታስራችሁ ስትገረፉ ታሰረክባላችሁ በማለት አስገድደው ቁልፉን መረከባቸውን በወቅቱ በቦታው ከደህንነቶቹ ጋር ሲዛትባቸው የነበሩ ወንድም ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ መስጂዱ ጭር ባለቤት ወቅት ግብረ ሃይል በማሰባሰብ የመጡት እነዚህ ሃይሎች መስጂዱን ዙሪያውን በፌደራል ፖሊስ ሲያስጠብቁ የነበረ ሲሆን የመስጂዱን ቁልፍ ከተረከቡ ቡሃላ ይዘውት በመጡት አዲስ ቁልፎች መቀየራቸው ታውቋል፡፡ በዛሬው ዕለት እሁድም ሁሉንም የመስጂዱ በሮች በአዲስ ቁልፍ ያስቀየሩ ሲሆን አዲስ 4 ዘበኛ እና የመስጂዱ አስተዳደርም መስጂዱን እንዲረከቡ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ መስጂዱ በአሁኑ ሰአት ሙሉ በሙሉ በአህባሾች ቁጥጥር ስር የወደቀ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ጉዳይም በነገው ዕለት መጋቢት 3 ከሰአት ቡሃላ በመስጂዱ ዙሪያ...

ህገ ወጡ የፌደራሉ መጅሊስ ለ3ቀናት የሚቆይ የአህባሽ ስልጠና በኡማ ሆቴል እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀ

Posted on Mar 30, 2016

ፍትህ ራዲዬ/መጋቢት 202008 አህባሽ መራሹ የፌደራሉ መጅሊስ ከሁሉም ክልል የተውጣጡ የአህባሽ ኡለሞችን በመሰብሰብ አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ሽፋን ለ ሶስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በኡማ ሆቴል እየሰጠ እንደሚገኝ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ከመጋቢት 19-21-2008 በሚቆየው በዚህ ሃገር አቀፍ ስልጠና ላይ ከዚህ ቀደም የአህባሽ ስልጠና ሲሰጥ በስልጠናው መጀመሪያ ላይ ለሁሉም ሰልጣኞች የሚሰጠውን አክራሪነትና ፅንፈኝነት ከህገ መንግሥቱ እይታ አንፃር ምን እንደሚመስል የሚያብራራ ገለፃ ከፌዴራልና አርብቶአደር ልማት ሚኒስቴር የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መሰጠቱ ታውቋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ቀናትም የአህባሽ አስተምህሮ በስፋት ለሰልጣኞቹ የሚሰጥ ሲሆን ከስልጣናው ቡሃላም ሁሉም ወደየክልላቸው ሲመለሱ ሊሰሩት የሚገባቸውን የቤት ስራ ይዘው እንደሚሄዱ ተገልፆል፡፡ የሰላም የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶቻችንን እናጎልብት በሚል የፖለቲካ መሪ ቃል የተዘጋጀው በዚህ ስልጠና መክፈቻ ላይ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያምን የተኩት የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለስልጠናው ፖለቲካዊ ቡራኬ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡ በስልጠናው ላይ ከዘጠኙም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ማለትም ከድሬዳዋ እና ከአዲስ አበባ የተውጣጡ የአህባሽን አስተምህሮ የሚከተሉ እና የሚደግፉ ኡለሞችን እንዲሁም በመንግስት እና በአህባሽ መጅሊሾች የተሾሙ የሸሪኣ ፍርድ ቤት ቃዲዎች እንዲሁም የአንዋር መስጂድ ኢማም ሀጂ ጠሃ በስልጠናው ላይ መካፈላቸው ታውቋል...