የቂሊንጦ ማ/ቤትን በሃሰት አቃጥላቹሃል በሚል በተወነጀሉት እስረኞች ላይ በሐሰት እንዲመሰክሩ የተስማሙ ፖሊሶች በዋስ መለቀቃቸው ተዘገበ

Posted on May 14, 2017

የቂሊንጦ ማ/ቤትን በሃሰት አቃጥላቹሃል በሚል በተወነጀሉት እስረኞች ላይ በሐሰት እንዲመሰክሩ የተስማሙ ፖሊሶች በዋስ መለቀቃቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 6/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥለዋል በሚል በሐሰት በተወነጀሉ እስረኞች ላይ አቃቤ ህጉ በሃሰት እንዲመሰክሩለት ካቀዳቸው ምስክሮች መካከል ለእስር ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት እንደሚገኙበት የተዘገበ ሲሆን በሐሰት እንዲመሰክሩ በመስማማታቸው ከእስር መለቀቃቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በማረሚያ ቤቱ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎም ወደ ማረሚ ቤቱ በሚሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ በድብቅ አስገብተዋል በሚል የተወሰኑ ፖሊሶች ለእስር ተዳርገው የቆዩ ሲሆን በማዕከላዊ መርማሪዎች በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በተከሳሾቹ ላይ በሐሰት ለመመስከር መስማማታቸው ተዘግቧል፡፡ ፋሲል የተባለን የፖሊስ አባል ጨምሮ ሌሎች አብረውት የታሰሩት ፖሊሶች በሃሰት በተወነጀሉት እስረኞች ላይ ለመመስከር መስማማታቸው የታወቀ ሲሆን በተስማሙት መሰረትም በዋስ ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉ ተዘግቧል፡፡ ከፖሊስ ምስክር በተጨማሪ ሌሎች እስረኞች በሀሰት እንዲመሰክሩ እየተገደዱ መሆናቸው የተዘገበ ሲሆን በሐሰት እንዲመሰክሩ ከተመለመሉት መካከል የመንግስት አቃቤ ህጉ በሚፈልገው መልኩ አንመሰክርም ያሉ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ እየተፈፀመባቸው ያለው ድብደባ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በንፁሃን እስረኞች ላይ አስገድደው በሃሰት ሊያስመሰክሯቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከነዚህ ምስክሮች በተጨማሪም በሌላ ክስ ተከሰው ወደ...

የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት “ሙስሊም ጀምዓ” የተሰኘ የሽብር ቡድን ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል በሚል 23 ሙስሊም እስረኞች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ

Posted on May 10, 2017

የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት “ሙስሊም ጀምዓ” የተሰኘ የሽብር ቡድን ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል በሚል 23 ሙስሊም እስረኞች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 2/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በእስማኤል በቀለ የክስ መዝገብ ለእስር በተዳረጉት 23 ሙስሊሞች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ማስተላለፉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ አቃቤ ህጉ በነዚህ 23 ሙስሊሞች ላይ የሽብር ክስ ያቀረበባቸው ሲሆን በኢትዬጲያ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል ሲል ቅስ እንዳቀረበባቸው ታውቋል፡፡ ተከሳሽ ሙስሊሞቹ ከ 2004 እስከ 2014 ድረስ ሙስሊም ጅመዓ የተሰኘ የሽብር ቡድን መመስረታቸውን አቃቤ ህጉ በክሱ ያቀረበ ሲሆን ከሽብር ክሱ በተጨማሪ በግድያ እና በዘረፋ ወንጀልም ተጨማሪ ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡ የሙስሊም ጀምዓ የተሰኘ ቡድን ከመመስረታቸው በተጨማሪም “አቂዳ” የተሰኘ ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ አባል እንደነበሩም በክሱ ላይ ሰፍሯል፡፡

ክስ የተመሰረተባቸው ወንድሞች የአዲስ አበባ፣የኦሮምያ እና የደቡብ ክልል ነዋሪ የነበሩ ሙስሊሞች ሲሆኑ በነዚህ ክልሎች ላይም ዘረፋ ሲያካሄዱ ነበር በሚል ክስ እንደቀረበባቸው ታውቋል

አቃቤ ህጉ ለዚህ ላቀረበው ሃሰተኛ ክስ 41 የሐሰት ምስክሮችን እና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾችም የቀረበባቸውን ሃሰተኛ ክስ አለመፈፀማቸውን የተለያዩ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ መከላከላቸው ታውቋል፡፡ ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው...

በከሚሴ በኹለፋኡል ራሺዱን መስጂድ የሚገኘው መድረሰተ ሰላም 2ኛ ዙር የቁርአን ሃፊዞቹን አስመረቀ

Posted on May 7, 2017

በከሚሴ በኹለፋኡል ራሺዱን መስጂድ የሚገኘው መድረሰተ ሰላም 2ኛ ዙር የቁርአን ሃፊዞቹን አስመረቀ ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 29/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በኦሮሚ ልዩ ዞን በከሚሴ ከተማ የሚገኘው መድረሰተ ሰላም ለ2ኛ ዙር የቁርአን ሃፊዞቹን ማስመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ የምረቃ ስነ ስርአቱ በከሚሴ ከተማ በሚገኘው በገልማ አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በርካታ የከተማው ህዝበ ሙስሊም በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ መካፈሉ ተዘግቧል፡፡ በከሚሴ ከተማ እና በዙሪያዋ የሚገኙ በርካታ ኡለሞች እና ኡስታዞችበምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ መካፈላቸው የተዘገበ ሲሆን መድረሳው ላለፉት ሁለት አመታት ሲያስተምራቸው የቆየውን የቁርአን ሂፍዝ ተማሪዎቹን በመደቀ ሁኔታ ማስረመቁ ታውቋል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎቹ ነጭ ጀለብያ ፣ቀይ አማይማ እና ሰማያዊ ሪቫን በማድረግ በምረቃው ላይ የቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ፊት ሆነው ለምረቃቱ ድምቀት ሰጥተው እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተለያዩ የዳዕዋ እና አዝናኝ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎችም የሽልማት ፕሮግራም መካሄዱ ተገልፆል፡፡ በተመሳሳይ ዜናም በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የመርከዝ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል የቁርዓን ሂፍዝ ማዕከል አራተኛ ዙር ተማሪዎቹን ማስመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ የምረቃ ስነ ስርአቱ በድሬዳዋ ከተማ በኡጋዝ ሐሰን አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን ጨምሮ ኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ እና ሌሎችም በክብር እንግድነት መካፈላቸው ተዘግቧል፡፡ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና...

አህባሽ መራሹ መጅሊስ በየቦታው መስጂድ እና መድረሳ ለማሰራት እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኡስታዞች ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድባቸው ጠየቁ

Posted on May 4, 2017

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ አህባሽ መራሹ መጅሊስ በየቦታው መስጂድ እና መድረሳ ለማሰራት እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኡስታዞች ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድባቸው ጠየቁ ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 26/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በመንግስት ተሹመው በግዳጅ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተጫኑት የፌደራሉ መጅሊስ አመራሮች በተለያዩ ክልሎች ስብሰባ በማካሄድ በኮሚቴዎቻችን እና በኡስታዞቻችን ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድባቸው እየጠየቁ መሆናቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በሐዋሳ፣በሐረር እና በአዲስ አበባ ከተሞች በተካሄደው የአህባሽ መራሹ ህገ ወጡ መጅሊስ ጉባኤዎች ላይ ተቀዛቅዞ የነበረው የአክራሪዎች እንቅስቃሴ ዳግም እያንሰራራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙን መስጂድ እና መድረሳ እናሰራላቹሃለን በማለት እያታለሉ የፖለቲካ ቅስቀሳ እያደረጉ ናቸው ሲሉ መወንጀላቸው ታውቋል፡፡ ፀረ አክራሪነትን አስመልክቶ በተሰጡት የአህባሽ ስልጠናዎች ላይ መስጊድና መድረሳ እንሰራላችኋለን በሚል ሽፋን የሚካሄዱ ገንዘብ የማሰባሰብ ኮንፈረንሶች በአስቸኳይ ይቁሙልን ሲሉ አህባሾቹ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡ መጅሊስና መንግስት ሳያውቀው ሰባቱ ቤተእምነቶች ሳይነገራቸው የሚካሄደው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ህገወጥ ተግባር በመሆኑ መቆም አለበት ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በየቦታው የገቢ ማሰባሰቢ በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ሀገር ለማተራመስ የሚንቀሳቀሱ አሉና መንግስት አፋጣኝ እርምጃ ይውድባቸው ሲሉ መንግስትን አበክረው መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ ባደረጉት ምክክር በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች...

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ በውርጌሳ እና በመርሳ ከተማ ህገ ወጡ መጅሊሶች መስጂዶች እንዳይታደሱ እና እንዳይሰሩ እያገዱ መሆናቸው ተገለፀ

Posted on May 2, 2017

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ በውርጌሳ እና በመርሳ ከተማ ህገ ወጡ መጅሊሶች መስጂዶች እንዳይታደሱ እና እንዳይሰሩ እያገዱ መሆናቸው ተገለፀ ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 24/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በውርጌሳ ከተማ የሚገኘውን የአቡበከር መስጂድን በአዲስ መልኩ ለማሰራት የታሰበውን እቅድ ህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታገድ ማድረጉን ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ ይህ መስጂድ ከተገነባ 20 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ለአካባቢው ሙስሊሞች በበቂ ሁኔታ እንዲገለገሉበት ለማስቻል መስጂዱን ዳግም ለማስገንባት የተደረገው እንቅስቀሴ በአህባሽ መራሹ መጅሊስ እንዲታገድ መደረጉ ታውቋል፡፡ በመስጂዱ በአፍሪካ ቲቪ በጄሉ መልቲ ሚዲያ አማካኝነት ቀረፃ ተደርጎለት በሃላል መዝናኛ ፕሮግራም ተሰርቶለት መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን መስጂዱን ለማስገንባት ለቀረበው ጥሪም ሙስሊሙ ትልቅ ተነሳሽነት ቢያሳይህም ህገ ወጡ መጅሊሶች ግ መስጂዱ እንዳይገነባ እገዳ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡ መስጂዱ በጁምዓ ቀን እና በረመዳን ወር ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝበ ሙስሊም የማያስተናግድ በመሆኑ ከመስጂዱ በር ፊት ለፊት አስፋልት ላይ በፀሃይ እየተቃጠሉ እና በዝናብ ወቅትም ዝናብ እየመታቸው ሙስሊሙ ለመስገድ እንደሚገደድ ታውቋል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍም የመስጂዱን በረንዳ በ 130 ቆርቆር ጣሪያ ለማልበስ እቅድ ተይዞ እንቅስቃሴ ቢጀመርም ይህንንም እንቅስቃሴ ህገ ወጡ መጅሊሶች ለማሳገድ ጥረት አድርገው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ለመስጂዱ በረንዳ ጣሪያ ማሰሪያ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በጁምዓ ቀን ለማካሄድ በታሰበበት ቀን ህገ ወጡ...

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ታላቁ አሊም ሼህ አብዱልቃድር ወደ አኼራ መሄዳቸው ተዘገበ

Posted on Apr 28, 2017

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

ታላቁ አሊም ሼህ አብዱልቃድር ወደ አኼራ መሄዳቸው ተዘገበ

ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 19/2009

۩ ○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○ ۩

በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞን በአብዳላ ወረዳ ነዋሪ የነበሩት የእድሜ ባለፀጋው ታላቅ አሊምሼህ አብዱልቃድ ወደ አኼራ መሄዳቸው ታውቋል፡፡

የ80 አመት አዛውንት የነበሩት የኢልም አባት ባደረባቸው የልብ ህመም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው እለት ሚያዚያ 20/2009 ሁሉም ወደማይቀርበት የአኼራ ጉዞ መጓዛቸው ተገልፆል፡፡

ሼህ አብዱልቃድር እድሜያቸውን በሙሉ ኢልም በማስተማር እና በርካታ ደረሶችን በማፍራት ዲንን ሲያስተምሩ የነበሩ አሊምመሆናቸው ተገልፆል፡፡

የቀብር ስነ ስርአታቸውም በሺዎች የሚቆጠር ህዝበ ሙስሊም እና ታላላቅ አሊሞች በሚገኙበት በነገው እለት ሚያዚያ 21 እንደሚፈፀም ታውቋል፡፡

ለሼህ አብዱልቃድ ማረፊያቸውን ጀነት እንዲያደርግላቸው ለቤተባቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብም መፅናናትን አላህ ይወፍቃቸው ዘንድ እየተመኘን ፍትህ ራዲዬ የተሰማትን ልባዊ ሐዘን መግለፅ ትወዳለች፡፡

የወልድያ ሰላም መስጂድ ለታላቁ የረመዳን ወር መስጂዱን ለማደስ እና አዲስ ምንጣፍ ለማንጠፍ የተደረገውን ዝግጅት በህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታገድ ተደረገ

Posted on Apr 25, 2017

ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ የወልድያ ሰላም መስጂድ ለታላቁ የረመዳን ወር መስጂዱን ለማደስ እና አዲስ ምንጣፍ ለማንጠፍ የተደረገውን ዝግጅት በህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታገድ ተደረገ ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 17/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ የሚገኘው ታላቁ የሰላም መስጂድ ለታላቁ የረመዳን ወር ለሙስሊሙ ምቹ ለማድረግ መስጂዱን ለማሳደስ እና አዲስ ምንጣፍ ለማንጠፍ የተደረገው ዝግጅት በወልድያ ከተማ ህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታገድ መደረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ አንድ ወር ለቀረው የረመዳን ወር መስጂዱን ለማሳደስ እና አዲስ ምንጣፍ ለማንጠፍ ዝግጅት ከተጠናቀቀ ቡሃላ የወልዲያ ሙስሊሞችን እያንገላታ የሚገኘው የህገ ወጡመጅሊስ አመራር አቶ ሰይድ ኢድሪስ ከወልድያ ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ከሆነው ከአቶ ሙሉቀን ማርዬ ጋር በመሆን መስጂዱም እንዳይታደስ አዲሱ ምንጣፍም በመስጂዱ እንዳይነጠፍ ማሳገዳቸው ታውቋል፡፡ በሚያዚያ 16 /2009 መስጂዱን ለማሳደስ ሲያስተባብሩ የነበሩ የከተማዋን ሙስሊሞ የወረዳው የጸጥታ ቢሮ በማስጠራት ለመስጂዱ ተብሎ የተላከው ምንጣፍ ማነው የላከው፣አድራሻውን አምጡ፣ለመስጂዱ እድሳትም ግዘቡን ያዋጡት እነማን ናቸው ስም እና ስልክ ቁጥራቸውን አምጡ ፣አልያ ግን ትታሰራላችሁ በሚል ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንደተፈፀመባቸው ተዘግቧል፡፡ በየአመቱ የረመዳን ወር ሲመጣ ህዝበ ሙስሊሙ በየአቅራቢያው የሚገኙ መስጂዶችን በማሳደስ አዲስ ምንጣፍ እንደሚቀይር የሚታወቅ ሲሆን በወልዲያ ሰላም መስጂድም በተመሳሳይ መስጂዱን በማሳደስ አዲስ ምንጣፍ...