በትግራይ ክልል በሼህ አብዱልመናን የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሙስሊሞች ከ3አመት እስከ6 ወር የሚደርስ እስራት ቅጣት ተበየነባቸው

Posted on Jul 13, 2017

በትግራይ ክልል በሼህ አብዱልመናን የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሙስሊሞች ከ3አመት እስከ6 ወር የሚደርስ እስራት ቅጣት ተበየነባቸው ፍትህ ራዲዬ/ ሐምሌ 6/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በራያ አዘቦ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ለእስር የተዳረጉት በሼህ አብዱልመናን የክስ መዝገብ የተከሰሱት ኡለሞች እና ኡስታዞች በቀነ ቀሯቸው መሰረት ሰኔ 17/2009 ፍርድ ቤት ለብይን ቀርበው እንደነበር የፍትህ ራዲዬ በልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በግንቦት 25 በነበራቸው ችሎት ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን የሽብር ክስ በመሰረዝ መንግስትን በመሳደብ በሚል እንዲቀየር መወሰኑ ይታወቃል፡፡ አቃቤ ህጉ ለሽብር ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ አስደምጦ እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ከምስክሮችም መካከል ሸኽ ኣብድልመናን 2006 ላይ በሳዉዲ ኣረብያ ረያድ መንፉሓ በተባለ ቦታ መስጂድ ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስት ሙስሊም ወንድሞቻችን(እነ ኡስታዝ ያሲን ኑሩን) ስላሰረ ለቤተሰቦቻቸዉ የሚሆን እርዳታ እናድርግ ማለታቸዉ ለመንግስት ፖሊሲ ያላቸዉ ጥላቻ ያመላክታል የሚል የምስክር ቃል የሰጡ መኖራቸው ይታወሳል፡፡ ቀሪ ምስክሮች ባጠቃላይ ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ መስጂዶችን ያሰሩ ነበር፣ ብርድ ልብሶች ለደካሞች ያድሉ ነበር፣ ዱቄት ያከፋፍሉ ነበር ፣ቧምቧ ውሃ ያስሩ ነበር በማለት የምስክር ቃላቸውን መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሁሉንም ምስክሮች ቃል ካደመጠ ቡሃላ አቃቤ ህጉ ያቀረበው የሽብር ክስ ውድቅ እንዲሆን እና በመደበኛ የወንጀል ህግ መንግስትን በመሳደብ በሚል ወንጀል እንዲከላከሉ ውሳኔ...

ከእስር የተፈታው ወንድም ሷቢር ይርጉ ከአመት በፊት ለኡመራ ጉዞ እንዳይሄድ ቦሌ ላይ ፓስፖርቱ ከተነጠቀ ወዲህ እስካሁን ፓስፖርቱ እንዳልተመለሰለት ተሰማ

Posted on Jun 23, 2017

ከእስር የተፈታው ወንድም ሷቢር ይርጉ ከአመት በፊት ለኡመራ ጉዞ እንዳይሄድ ቦሌ ላይ ፓስፖርቱ ከተነጠቀ ወዲህ እስካሁን ፓስፖርቱ እንዳልተመለሰለት ተሰማ

ፍትህ ራዲዬ/ ሰኔ 16/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኡስታዝ አቡበከር አህመድ የክስ መዝገብ ተከሶ እስራት ተበይኖበት የነበረው እና በ 2 አመት በፊት መስከረም ወር በምህረት በሚል እንዲፈቱ ከተደረጉት ሙስሊሞ መካከል አንዱ የሆነው ወንድም ሷቢር ይርጉ ባለፈው አመት የኡምራ ጉዞ ለማድረግ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመጓዝ እንዳይችል ቦሌ ላይ በኢሚግሬሽን ሰራተኞች መታገዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ድምፀ ደርባባው፣የመድረኩ ፈርጥ ተብሎ የሚጠራው ወንድም ሷቢር ይርጉ ከኮሚቴዎቻን ጋር የረጅም አመት እስራት ቅጣት ተበይኖበት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን መንግስት በራሱ ፈቃድ በምህረት በሚል እንዲፈታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

መንግስት በነፃ በምህረት እንዲፈታ ቢያደረግም ከሃገር እንዳይወጣ ፓስፖርቱ ተወስዶበት እስካሁን እንዳልተሰጠው ተሰምቷል፡፡

ከአንድ አመት በፊት ወንድም ሷቢር ይርጉ ለጉዞ የሚያስፈልጉ የኡምራ ቪዣ እና የአይር መንገድ ቲኬት በመቁረጥ በበረራ ሰአቱ ቦሌ አየር ማረፊያ በሰአቱ ቢደርስም የቦሌ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ወንም ሷቢር ይርጉ ከሃገር እንዳይወጣ የታገደ በመሆኑ ኡምራ ለማድረግ መውጣት እንደማይችል እንደገለጸሉት እና የያዘውን የጉዞ ፓስፖርትም ደህንነቶቹ በመንጠቅ እስካሁን ድረስ አንሰጥም ብለው እንደከለከሉተ መሆኑ ታውቋል፡፡...

ከእስር የተፈቱት ኮሚቴዎቻችን ለኡምራ ስነ ስርአት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ማምራታቸው ተገለፀ

Posted on Jun 15, 2017

ከእስር የተፈቱት ኮሚቴዎቻችን ለኡምራ ስነ ስርአት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ማምራታቸው ተገለፀ

በመፍትህ ራዲዬ/ ሰኔ8/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ስከረም ወር በምህረት በሚል የተፈቱት ኮሚቴዎቻችን ለኡምራ ስራ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ማቅናታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የኮሚቴውን ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ጨምሮ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ሼህ ሱልጣን አማን፣ዶ/ር ጀይላን ኸድር፣ኡስታዝ ሃይደር ከድር ፣ኡስታዝ በድሩ ሁሴን እና ሌሎች ወንድሞችም ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመጓዝ የኡምራ ስነ ስርአታቸውን ያከናወኑ ሲሆን ለ 4 አመታት ከእስር ካሳለፉ ቡሃላ ከሃገር ሲወጡ የጀመሪያው መሆኑ ተገልፆል፡፡

ከዚህ ቀደም ወንድም ሷቢር ይርጉ ለኡምራ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለማምራት ቦሌአለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከደረሰ ቡሃላ ከሃገር መውጣት አትችልም በሚል እንዲመለስ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በዘንድሮ አመት መሰል ክልከላ ይኖራል ተብሎ ቢሰጋም ኮሚቴዎቻችን በሰላም ከሃገር መውጣታቸው ተገልፆል፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ከእስር ከተፈታ ቡሃላ ለህክምና ወደ ውጪ ሄዶ ለመታከም በተደጋጋሚ ቢፈልግም ደህንነቶች ከሃገር እንዲወጣ ባለመፈለጋቸው ሳይሳካ የቀረ ሲሆን አሁን ለኡምራ ስነ ስርአት ሁሉም ተፈቅዶላቸው ከሃገር መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡

ከተወሰነ ሳምንታት በፊት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በድጋሚ በማከላዊ ታስረው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በየቦታው እያካሄዱ ያሉትን...

በደቡብ ወሎ ዞን በደጋን ከተማ በሳርምድር መስጂድ አህባሾች በመስጂዱ ካላሰገደን መስጂዱን እናሻሽገዋለን በሚል እየረበሹ መሆናቸው ተገለፀ

Posted on Jun 15, 2017

በደቡብ ወሎ ዞን በደጋን ከተማ በሳርምድር መስጂድ አህባሾች በመስጂዱ ካላሰገደን መስጂዱን እናሻሽገዋለን በሚል እየረበሹ መሆናቸው ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ ሰኔ 8/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ በደጋን ከተማ አህባሽ መራሹ ህገ ወጡ መጅሊስ በከተማው ያሉትን ዋና ዋና መስጂዶች በግዳጅ ከተቆጣጠረ ቡሃላ በነሱ ቁጥጥር ስር ሊገባላቸው ያልቻለውን የሳርምድር መስጂድን መስጂዱን እናሽገዋለን በሚል ማስፈራሪያ መስጂዱን ለመንጠቅ እየተንቀሳቀሰ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በደጋን ከተማ ያሉት ትላልቅ መስጂዶች በአህባሽ መራሹ መጅሊሶች ተነጥቆ የአህባሽ ኢማሞች ተመድበውበት የአህባሽ አስተሳሰብ እየተሰበከበት እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የከተማው ህዝበ ሙስሊም በአህባሾች የተነጠቀውን መስጂድ በመተው ወደ ሳርምድር መስጂድ እየሄዱ እየሰገዱ መሆናቸው ተገልፆል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም ወደ ሳርምድር መስጂድ መሄዱ ያበሳጫቸው የአህባሽ መራሹ መጅሊስ አመራሮች ፊታቸውን ወደ ሳርምድር መስጂድ በማዞር ይሄ ሁሉ ሙስሊም እዚህ መስጂድ ለምን ይመጣል፣በመስጂዱ ሰላት የምናሰግደው እኛ ነን በማለት መስጂዱን እያወኩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ መስጂዱ የራሱ ኢማም አለው ሌላ ኢማም አያስፈልግም በማለት እየተቃወማቸው የሚገኝ ሲሆን በመስጂዱ ከሰላት በተጨማሪ የቁርአን እና ሃዲስ ትምህርት፣ዳዕዋ እና ሌሎችም ትምህርቶች እንዳይሰጡ መጅሊሱ እየከለከለ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በመስጂዱ ምንም ትምህርት...

የደሴው ወንድም እስማኤል ሐሰን የእስር ጊዜውን ጨርሶ መፈታቱ ተገለፀ

Posted on Jun 7, 2017

የደሴው ወንድም እስማኤል ሐሰን የእስር ጊዜውን ጨርሶ መፈታቱ ተገለፀ ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 30/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሶ የ 5 አመት የግፍ እስራት ተበይኖበት የነበረው ወንድም እስማኤል ሐሰን የእስር ጊዜውን ጨርሶ መፈታቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ወንድም ኢስማኤል በቀረበበት ክስ በዝቅተኛ አንቀፅ ጥፋተኛ ተብሎ የ 5 አመት የግፍ ብይን ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን የአመክሮ ጊዜ ሳይታሰብለት የእስር ጊዜውን ጨርሶ መፈታቱ ታውቋል፡፡ ወንድም እስማኤል ሐሰን ጥፋተኛ በተባለበት አንቀፅ እስካሁን የታሰረበት ጊዜ ያህል ሊያስፈርድበት የሚችል ብቻ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 5 አመት እስራት እንደበየነበት ይታወሳል፡፡ የደሴው እስማኤል ሐሰን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ በከፍተኛ ውጤት የተመረቀ ሲሆን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም በሌክቸረርነት ተማሪዎችን ሲያስተምር ቆይቷል፡፤ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታም ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ውጤታቸውን የሚመለከቱበት የሞባይል ሶፍት ዌር በመስራት ለዩኒቨርሲቲው ያበረከተ ሲሆን ለዚህ ድንቅ ስራውም ዩኒቨርሲቲው የእውቅና ሰርተፍኬት እና ገንዘብ ሽልማት አበርክቶለታል፡፡ በተለያዩ የፈጠራ ችሎታው ሃገሩን እያገለገለ የሚገኘው ይህ ወጣት ለእረፍት ወደ ደሴ ከተማ በተመለሰበት የሼህ ኑሩን መገደል ተከትሎ ለእስራት መዳረጉ ይታወቃል፡፡ ለ4 አመታት በግፍ እስራት ከቆየ ቡሃላ የእስር ጊዜውን አጠናቆ ከማረሚያ ቤት መፈታቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የታላቁ የረመዳን ፆም የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 19 እንደሚጀመር ተገለፀ ረመዳን ሙባረክ

Posted on May 25, 2017

የታላቁ የረመዳን ፆም የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 19 እንደሚጀመር ተገለፀ

ረመዳን ሙባረክ

ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 17/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በመላው አለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የታላቁ የረመዳን ፆም የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 19 እንደሚጀመር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የሳኡዲ አረቢያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው መግለጫ መሰረት በዛሬው እለት ሃሙስ ግንቦት 17 ጨረቃ ልትታይ ባለመቻሏ የረመዳን ፆም ቅዳሜ አንድ ብሎ እንደሚጀመር አስታውቋል፡፡

በነገው እለት ጁምዓ ግንቦት 18 የሻዕባን ወር የመጨረሻ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ቅዳሜ የረመዳን የመጀመሪያ ቀን መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡

የታላቁ የረመዳን ወር በመላው አለም የሚገኙ ሙስሊሞች በፆም የሚያሳልፉት ሲሆን ይህን የተከበረ ወር ለመቀበል ሁሉም በየፊናው ሲዘጋጅ መቆየቱ ታውቋል፡፡

በዘንድሮ ረመዳን 4 ጁምዓዎች እንደሚኖሩ የተገለጸ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፆሙን ሲፆም ሚስኪኖችንም በማሰብ አብሯቸው በማፍጠር አጋርቱን ሊያሳይ እንደሚገባ ተገልፆል፡፡

በእስር ላይ የሚገኙትንም ሙስሊሞች ሄዶ በመዘየር፣በማስፈጠር እና ቤተሰቦቻቸውን በመንከባከብ አጋርነቱን እና ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ፍትህ ራዲዬም ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ 1438 የታላቁ የረመዳን ፆም በሰላም አደረሰን ለማለት ትወዳለች

የኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል አመራሮች ቁርአን ሃፊዞችን ለማስመረቅ በሄዱበት መታሰራቸው ተዘገበ

Posted on May 24, 2017

የኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል አመራሮች ቁርአን ሃፊዞችን ለማስመረቅ በሄዱበት መታሰራቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 16/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአዲስ አበባ በሼህ ሆጀሌ መስጂድ ውስጥ የሚገኘው ግዙፉ የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል የሆነው የኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል አመራሮች የቁርአን ሃፊዞችን ለማስመረቅ ወደ አሶሳ በተጓዙበት ለእስር መዳረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ የኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል የአሶሳ ቅርንጫፍ ቁርአን ሲያሳፍዛቸው የነበሩ ተማሪዎቹን ለማስመረቅ በአሶሳ ከተማ በሚገኘው የሰልፊያ መስጂድ ባዘጋጀው የምረቃ ስነ ስርአት ላይ ለመካፈል ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ያቀኑት የመርከዙ ሃላፊዎች ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው በአሶሳ ከተማ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የቁርአን ሃፊዞች የምረቃ ፕሮግራም በህገ ወጡ መጅሊስ እና በፖሊስ ሃይሎች እንዳይካሄድ መደረጉ ተዘግቧል፡፡ ይህን ተከትሎም በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ከአዲስ አበባ የተጓዙት ኡስታዞች መንገድ ላይ ለእስር የተዳረጉ ሲሆን እስካሁን ታስረው እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡ የኢብኑ ከሲር የቁርአን ሂፍዝ ማዕከልን በሼህ ሆጀሌ መስጂድ የመሰረተው እና መርከዙን በበላይነት የሚመራው ኡስታዝ መሐመድ አብዱልቃድር(ባኮ)፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ(የመርከዙ ምክትል ሃላፊ) እና ሌሎች ወንድም እና ኡስታዞችም ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል፡፡ በአሶሳ ከተማ በሰለፊያ መስጂድ ሊካሄድ የነበረው የሃፊዞች ምረቃ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች እንዳይካሄድ የተከለከለ ሲሆን በምረቃ ስነ...

ፍትህ ሬዲዮ ፕሮግራም አስደምጠኝ