የብሄራዊው ጭቆና ዋነኛ መገለጫዎች ምን ምን ናቸው? (ባለቀጣይ ክፍል)

Posted on Feb 29, 2016

ተከታታይ ግንዛቤ ማስጨበጫ - ክፍል 3 ሰኞ የካቲት 21/2008

በተከታታይ ከሚወጣው የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሁፍ ክፍል አንድ እና ሁለትን ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ በክፍል አንድ የአህባሽ አመለካከት በመንግስት ሃይል መጫን ከብሄራዊ ጭቆናው መገለጫዎች አንዱ መሆኑን ያየን ሲሆን በክፍል ሁለት ደግሞ ከመደራጀት መብቶች እና መንግስት ከሚያደርገው የማጠልሸት ዘመቻ ጋር የተያያዙ 3 ነጥቦችን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ ዛሬ ደግሞ በአላህ ፈቃድ አምስተኛውን የብሄራዊ ጭቆና መገለጫ እናያለን፡፡

ጥያቄ 1 - የብሄራዊ ጭቆናው መገለጫዎች ምን ምን ናቸው? (ባለቀጣይ ክፍል)

5/ በመላው አገሪቱ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› የኃይል እርምጃዎችን መውሰዱ፤

የመንግስት በሀይማኖት ጣልቃ ገብነት የእምነት አቅጣጫን እስከመምረጥና በግዳጅ እስከመጫን ጭቆና መድረሱ ብቻ ብሄራዊ ጭቆና ለመሆኑ በቂ መገለጫ ነው፡፡ ይሁንና ህዝበ ሙስሊሙ ለአገር በማሰብ ዲፕሎማሲያዊ መንገድን በመምረጥ ነበር ጥያቄውን አዋቅሮ በሂደት የትግሉን አቅጣጫ የመሰረተው፡፡ ይህ ሰላም እና አገር ወዳድነቱ ግን እንደተከተለው የትግል መስመር ያማረ ምላሽ አላስገኘለትም፡፡ በየካቲት 26/2004 ማግስት ነበር መንግስት የህዝብ ውክልና በተሸከሙት ኮሚቴዎች ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ማድረስ የጀመረው፡፡ በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ከሚደረግባቸው አፈና ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት ከመንገድና ከተለያዩ ቦታዎች ውድ ኮሚቴዎቻችን በማፈን ከመተናኮስም ባለፈ በአንዋር መስጂድ ከሚደረጉ ሰላማዊ ተቃውሞዎች በኋላ ህዝብን ማደን እና ማሰር ቋሚ...

በፍልውሃ (ተውፊቅ) መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ ተቃውሞ ተካሄደ!

Posted on Feb 26, 2016

ሰበር ዜና!!! መፈክሮች የተጻፉባቸው ባሉኖች ተውለብልበዋል! አርብ የካቲት 18/2008

በፍልውሃ (ተውፊቅ) መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ ተቃውሞ ተካሄደ!

ከጁሙዓ መልስ በተካሄደው በዚሁ ተቃውሞ መፈክሮች የተጻፉባቸውን ባሉኖች ተውለብልበው ወደሰማይ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡ በባሉኖች ላይ ከተጻፉት መፈክሮች መካከል ‹‹ብሄራዊ ጭቆናን እንታገላለን!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድራማው ይብቃ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› እና ‹‹ጭቆናው ይብቃ!›› የሚሉት መፈክሮች ጎልተው የወጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአ

በአንዋር መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ ታላቅ የድምጽ ተቃውሞ ተካሄደ!

Posted on Feb 19, 2016

ሰበር ዜና!!! አርብ የካቲት 11/2008

ዛሬ የካቲት 11/2008 በአንዋር መስጂድ ከጁሙዓ መልስ የድምጽ ተቃውሞ ተካሄደ! ባለፈው ሳምንት ከተደረገው የጽሁፍ መፈክር የማሳየት ተቃውሞ በኋላ መንግስት ወደመስጊዱ የሚመጣውን ሰው በፍተሻ ሲያጉላላ የነበረ ቢሆንም የድምጽ መፈክሮች በድምቀት ተሰምተዋል!

ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ብሄራዊ ጭቆናው እስኪገታ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም በተደጋጋሚ ሲገልጽ የቆየ ሲሆን በዛሬው ተቃውሞውም ‹‹ብሄራዊ ጭቆናው ይብቃ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹መንግስት የለም ወይ?›› በሚሉ መፈክሮቹ ቁርጠኝነቱን እና የትግል ወኔውን ገልጿል!

ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማል! አላሁ አክበር!