በቢሾፍቱ በሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ መንግስት የወሰደውን እርምጃ በጽኑ እናወግዛለን!!!! 

Posted on Oct 5, 2016

በወገኖቻን እልቂት የተሰማንን መሪር ሐዘን እንገልፃለን!!! ለተጎጂ ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን መፅናናትን እንመኛለን! ግፍ ማለፉ ብቻ ሳይሆን ድልን አስከትሎ መመጣቱ አይቀርምና ኢትዮጵያዊያን ለፍትህ፣ ለነጻነት እና ለሰላም የምናደርገው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!! ረቡእ መስከረም 25/2009

ከመንግስት በርካታ ኃላፊነቶች መካከል የአገርን ህልውና እና የህዝብን ሰላም ማስጠበቅ ቀዳሚዎቹ ናቸው። በአገራችን ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው። በሚያሳዝን መልኩ በአገራችን እየተከሰቱ ያሉ ሰላም የሚያደፈርሱና ህልውናችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ ክስተቶች በአብዛኛው ምንጫቸው መንግስት ሆኖ እናገኘዋለን። ከሰሞኑም ኃላፊነት በጎደለው የመንግስት እርምጃ በርካታ ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ለሞት ተዳርገዋል። ይህ ድርጊት በየትኛውም መመዘኛ በጽኑው የሚወገዝ ሲሆን ስርዓቱ ምንግዜም ከስህተቱ የማይማር፣ ሰላማዊ ጥያቄን ከሚያነሱ ዜጎች ጋር ለመግባባት ከኃይል እና አፈሙዝ ውጭ ሌላ ቋንቋ እንደሌለው በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዜጎችን መብት በኃይል ረግጦ እና ፍላጎታቸውን አፍኖ ለመያዝ የሚታትር ስርዓት እድሜው ረጅም እንደማይሆንም የሚያጠያይቅ አይደለም።

በህዝቦች ላይ ጭቆናው ሲበረታና ግፉ ከሚሸከሙት በላይ ሲሆን ጠንክረው ከመታገል ውጪ አማራጭ እንደሌላቸው ይገነዘባሉ። በዚህም ራሳቸውን ለተሻለ ትግልና መስዋእትነት ያዘጋጃሉ። አለመታገል ከስቃይ እና እንግልት በማያድኑበት ተጨባጭ ሁኔታ መታገል አማራጭ ሳይሆን የህልውና ዋስትናም ጭምር ነው። የሚከፈለው መስዋዕትነት የቱንም አይነት ይዘት ይኑረው...

መንግሥት አሁንም በእብሪተኝነቱ ቀጥሏል!

Posted on Aug 4, 2016

እኛም እስከመጨረሻው በፅናት ከመታገል ውጭ ሌላ አቋራጭ መንገገድ የለንም! ሐሙስ ሐምሌ 28/2008

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መንግስት መራሹን ሃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት ስንታገል ይኸው ዓመታትን አሳልፈናል፡፡ በዚህ ወቅት ሁሉ መብታችንን በዘላቂነት ለማስከበር በጽናት የቆምን ሲሆን በሂደትም ዘርፈ ብዙ ልምድን፣ ጠንካራ የእምነት ትስስርን እና መደጋገፍን መሠረት ያደረገ ወንድማማችነት መመስረት ችለናል። በዚህም እኛን ለመከፋፈል የተደረጉ የመንግስትን በርካታ ሴራዎች ለማምከን ችለናል - አልሐምዱሊላህ! በመንግስት ጋሻ ጃግሬነት እየተካሄደ ያለውን የብሄራዊ ጭቆና ዘመቻ ጸንተን ከመታገል ውጭ ሌላ አቋራጭ መንገድ አለመኖሩን በትግላችን ሂደት ለመረዳትም ችለናል፡፡ መንግስት በእብሪተኝነቱ መቀጠሉ እና የህዝብን ድምጽ ከምንም ባለመቁጠር በአምባገነንነት ጭቆናውን አጠናክሮ መቀጠሉ ይህንን እውነታ ያጠናክራል።

ሙስሊሙ ህብረተሰብ መንግስታዊውን ህገወጥ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ተቃውሞ ያነሳቸው ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ህጋዊ እና ፍትሃዊ ሲሆኑ ጥያቄዎቻችን ይመለሱ ዘንድ የተጓዝንበት የትግል ጎዳናም እጅግ ሰላማዊ ነው። ምንም እንኳን ለፍትሃዊ ጥያቄዎቻችን እና ለሰላማዊ ሂደታችን ከመንግስት ያገኘነው መልስ በኢሰብአዊነት የተሞላ እና ህግን የጣሰ ሆኖ ቢቀጥልም እስካሁንም ድረስ ግን ህዝበ ሙስሊሙ ከሰላማዊነት መርሁ አንዳችም ፈቀቅ ሳይል የትግል ሂደቱን ማእቀፍ በማጠናከር እና በማስፋት በትግሉ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

ከሕዝበ ሙስሊሙ ትግል ጎን ለጎን መንግስት ለሙስሊሙ ጥያቄ እልባት ይሰጥ...

ፍትህ በኢትዮጵያ የተቀበረባት፣ ለፍትህ ፈላጊው ሙስሊም የትግል ጽናት ግድ የሆነባት ቀን!

Posted on Aug 3, 2016

ሐምሌ 27 ረቡእ ሐምሌ 27/2008

በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የትግል ሂደት ውስጥ ወርሃ ሐምሌ ልዩ ቦታን ይዞ የሚገኝ ወር ነው። የአገሪቱን ህጎች ጠብቆ እና አስጠብቆ ሰላማዊ በሆነ ልዩ ስርዓት ፍትህን ለማግኘት ድፍጹን ከፍ በማድረግ ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የሚል ጥሪ ባደረገ ህዝብ ላይ የጥቁር ሽብር የታወጀበት እና የተፈጸመበት ወር ብቻ ሳይሆን ይህን የፍትህ ፈላጊነት መርሁን ሳይለቅ ጥያቄዎቹ እስከሚመለሱበት ቀን ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል ቃል የተጋባበት ወር ነው። ሙስሊሙ ህብተሰብ በገባው ቃል መሰረት ትግሉን በመቀጠል በአምባገነኑ ስርዓት የስለላ፣ የፓሊስ እና የወታደራዊ ሃይል ኢሰብዓዊ እርምጃ የደረሰበትን በደል እና ግፍ በፍርድ ቤት መድረክም ዳግም እውን ለማድረግ ከሁለት ዓመታት በላይ የቆየ ግብግብ ያደረገ ሲሆን በዚህ ትግል መካከል ፍትህ በአገሪቱ መቀበሯ እውን የሆነበትን ሐምሌ 27ን እናገኛለን።

አዎ! ሐምሌ 27 በኢትዮጵያዊያን፣ በተለይም ደግሞ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የማትረሳ እለት ሆና አልፋለች - የሰላም መልእክተኞች ላይ የአሸባሪነት ታፔላ የተለጠፈባት እለት! ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ ያፈላልጉለት ዘንድ ፈርሞ በላካቸው ንጹሃን ሙስሊሞች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፏል፡፡ እኒህ ሙስሊም ግለሰቦች ከቀድሞውም የሚታወቁት መልካምን በመስራት፣ ሌሎችን በመርዳት እና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል መከባበርን፣ መተሳሰብን እና መደጋገፍን በመስበክ ነበር፡፡ ራሳቸውን የስብከታቸው ምልክት በማድረግም መታወቅ ችለው ነበር፡፡ ግና ፍትሃዊ ሳይሆን...

የትግላችን መሰረት ህዝባችን ነው እና ህዝባችንን ተደራሽ ለማድረግ የምናደገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

Posted on May 18, 2016

ረቡእ ግንቦት 10/2008

ትግል ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው፡፡ ይህን ሂደት የሚፈጥሩትም ሆነ ከዳር የሚያደርሱት ደግሞ የትግሉ ባለቤት የሆኑት ህዝቦች ናቸው፡፡ እንደአገራችን ባሉ ዲሞክራሲ ባልዳበረባቸው አገራትና አሁን ባለው አለም አቀፍ ተለዋዋጭ ፓለቲካ የትግል ሂደት እንደ ሜዳ ለጥ ያለና የተደላደለ አይደለም፡፡ እንቅፋትና አሜኬላ የበዛበት፣ በዳገትና ቁልቁለት የተሞላ ነው፡፡ የትግሉ ባለቤቶች በእነዚህ የትግል ተፈጥሯዊ ሂደቶች ውስጥ ሲያልፉ የሚኖራቸው ምላሽ እንደግለሰባዊ ጥንካሬያቸው፣ ለትግሉ እንዳላቸው እምነት፣ እንደ ልምድና እንደተሞክሯቸው ይለያያል፡፡ ጥቂት ነገሮች ውዥንብር የሚፈጥርባቸው እንዳሉ ሁሉ በፕሮፓጋንዳ እና በአሉባልታ ቀርቶ በኃይልም የማይፈቱ ቆራጥ ታጋዮች በርካቶች ናቸው፡፡

የአንድ የትግል ሂደት ከሚገጥሙት ተግዳሮቶች መካከል የብዙሀኑን ህዝብ ስሜት ከነባራዊው ሁኔታ ጋር በማጣጣም ትግሉን ስኬታማ የሚያደርግ የትግል አቅጣጫ መንደፍ ነው፡፡ ይህን የትግል አቅጣጫም የትግሉ ባልተቤት የሆነው ህዝብ በሚገባ ሊረዳው ይገባል። የትግሉን አቅጣጫ ህዝብ በትክክል ካልተረዳው ትግሉን ከዳር ማድረስ አስቸጋሪ ይሆናል። የትግሉ አቅጣጫ በትክክል ለህዝብ ባልደረሰበት ሁኔታ በትግሉ እና በደል በሚፈጥረው ህዝባዊ ቁጭት፣ ይህም በተራው በሚወልደው የህዝብ ስሜት መካከል ክፍተት ይፈጠራል፡፡ አንድ ህዝባዊ ትግል በቀዳሚነት ከሚይዛቸው ተግባራት መካከል የትግልን ሂደት እና አቅጣጫ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ታጋዩ ህዝብ ዘንድ ማድረስ እና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወን...

የመፍትሄ አቅጣጫዎቻችን ምን ምን ናቸው? (ባለቀጣይ ክፍል)

Posted on Apr 26, 2016

ተከታታይ ግንዛቤ ማስጨበጫ - ክፍል 6 የመፍትሄ አቅጣጫዎቻችን ምን ምን ናቸው? (ባለቀጣይ ክፍል) ማክሰኞ ሚያዝያ 18/2008

የትግላችን መነሻ የሆነውን ብሄራዊ ጭቆና መገለጫዎች በተከታታይ 4 ክፍሎች በወጡ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ስንመለከት የቆየን መሆኑ ይታወሳል፡፡ በመቀጠልም የጭቆናውን ይዘት እና የመፈፀም አቅማችንን ግምት ውስጥ ያስገቡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን መዘርዘር የጀመርን ሲሆን ከዚህም ውስጥ ክፍል አንድን ባለፈው አቅርበናል፡፡ ዛሬ ደግሞ በክፍል ሁለት የመፍትሄ ጥቆማችን ተጨማሪ ነጥቦችን የምንዳስስ ይሆናል - ኢንሻአላህ!

ጥያቄ 2 - የመፍትሄ አቅጣጫዎቻችን ምን ምን ናቸው? (ባለቀጣይ ክፍል)

3/ በኢኮኖሚው እና ልማት ዘርፍ መንቀሳቀስ፤

መንግስት ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለማዳከም ሲሸርብ የቆየውን ሴራ በቅጡ ከሚያስገነዝቡ ነገሮች አንዱ ሙስሊሙ በአገሪቱ የኢኮኖሚ እና የልማት ስራዎች ላይ ያለው ተሳታፊነት እንዲገደብ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ እንደአንድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍል (ኮሚውኒቲ) የራሱ የሆኑ የፋይናንስ እና የኢንቨስትመንት ተቋማት በማደራጀት የራሱን ህይወት አሻሽሎ አገሩን እና ወገኑንም መጥቀም የሚችልበትን እድል ተነፍጓል፡፡ ወደተሻለ የኢኮኖሚ አቅም እና የተደራጀ እንቅስቃሴ የሚያደርሱት በሮች ሁሉ ተዘግተውበታል። ሃይማኖታዊ ማንነቱን ከግምት ያስገቡ የፋይናንስ ድጋፍ አማራጮችን እንዳይጠቀም በተለያዩ አዋጆች እና መመሪያዎች እቀባ የተደረገበት ሲሆን ይህም ለሙስሊሙ ጭቆና፣ ለአገሪቱም በደል መሆኑ...

ሕዝበ ሙስሊሙ ዛሬም ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ቀጥሏል!

Posted on Mar 26, 2016

በሜክሲኮ ተውፊቅ (ጀርመን) መስጂድ ከጁሙዓ በኋላ መፈክሮች የተጻፉባቸው ወረቀቶች በማውለብለብ ድምፅ አልባ ተቃውሞ ተካሄደ! አርብ መጋቢት 16/2008

ሙስሊሙ ህብረተሰብ መንግስት የጫነበትን ብሄራዊ ጭቆናን በመቃወም ዛሬም ሜክሲኮ አደባባይ አቅራኒያ በሚገኘው ተውፊቅ (ጀርመን) መስጂድ ከጁሙዓ ሰላት በኋላ ድምፅ አልባ ተቃውሞ አካሄደ!

በዚሁ ከጁሙዓ ሰላት በኋላ በተካሄደው ተቃውሞ የተለያዩ መፈክሮች የተጻፉባቸው ወረቀቶች የተውለበለቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ‹‹የነቃ ህዝብን ያሸነፈ አፈና የለም!››፣ ‹‹ሰላማዊ ያደረገን የአሚሮቻችን ቃል እንጂ የአምባገነን ጡጫ አይደለም!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!!!››፣ ‹‹ሰላም ከነሳችሁን ተመሳሳይ ኑሮ እንድንኖር ታስገድዱናላችሁ!!››፣ ‹‹ፍትህን ቀበሯት!!!››፣ ‹‹ትግላችን ይቀጥላል!!››፣ ‹‹እምነታችንን አናስንቅም!!›› እና ‹‹ድምፃችን ይሰማል!!›› የሚሉት ጎልተው የወጡ መሆናቸው ታውቋል።

እኒህ እና ሰሞኑን ሲካሄዱ የቆዩ ሰላማዊ ተቃውሞዎች በእርግጥም ብሄራዊ ጭቆናው ሳይቆም ሙስሊሙ ህብረተሰብ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል እንደማያቆም እና አራት ዓመታት የዘለቀው ሰላማዊ ትግልም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጫዎች ናቸው።

ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማል! አላሁ አክበር!

በቦረና ዞን የምትገኘው ያቤሎ ከተማ በግራፊቲ ጽሑፎች ተጥለቅልቃ አደረች!

Posted on Mar 4, 2016

ሰበር ዜና!!! ‹‹ለበደል እጅ አንሰጥም!›› የሚሉ ድምጾች ተጠናክረው ቀጥለዋል! አርብ የካቲት 25/2008

በቦረና ዞን በምትገኘው ያቤሎ ከተማ ሌሊቱን የግራፊቲ ፅሁፎች ተጽፈው አደሩ! የሕዝቡን ተቃውሞ የሚያሳዩ መፈክሮች እና ጽሁፎች ተበትነው እና በስልክ እንጨቶች ላይ ተለጥፈው ባደሩበት በዚሁ ተቃውሞ የከተማው ደህንነቶች የተደናገጡ ሲሆን መፈክሮቹን በመገንጠል እና በማጥፋት ላይ ተሰማርተው ያረፈዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከተጻፉት መፈክሮች መካከል ‹‹ብሔራው ጭቆና ይብቃ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹የታሰሩት ይፈቱ!››፣ ‹‹ድራማ ይብቃ!››፣ ‹‹የኦሮሞን ህዝብ መግደል ይቁም!››፣ ‹‹አምባገነን ፍርድ አንቀበልም!››፣ ‹‹ህዝብ ያልተቀበለው ማስተር ፕላን ተቀባይነት አይኖረውም!›› እና ‹‹የኢቢሲ ውሸት በቃን!›› የሚሉት ጎልተው የወጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማል! አላሁ አክበር!