7 ሙስሊሞች በሽብር ወንጀል ተከሰው እስከ ዘጠኝ አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተበየነባቸው ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 2/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ተንቀሳቅሰዋል በሚል የሃሰት ክስ የመሰረተባቸው ሰባት ሙስሊሞች ላይ ከሁለት እስከ ዘጠኝ አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ተዘገበ፡፡ ፍርድ ቤቱ የእስር ቅጣቱን የወሰነው 1ኛ መሐመድ አብዱራህማን፣ 2ኛ መሐመድ አህመድ፣ 3ኛ መሐመድ አብዱላሂ፣ 4ኛ መሐመድ አሊ፣ 5ኛ አነሰ ኡስማን፣ 6ኛ ኡስማን ሀሰን፣ 7ኛ መሀመድ አዌስ በተሰኙ ሙስሊሞች ላይ ነው፡: የኢትዬጲያ መንግስት ላልፉት 6 አመታት ሙስሊሞችን በሽብርተንነት በመወንጀል ከአልሸባብ እና ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ ነበር በሚል በርካቶችን ለግፍ እስራት መዳረጉ የሚታወስ ነው፡፡ የመሀመድ አብዱላሂ የክስ መዝገብ ተከሰው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩት እነዚህ 7 ሙስሊሞች የ አልሸባብ ቡድን አባል በመሆን፣ ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድና የሽብር ቡድኑ አስታጥቋቸው ሞቃዲሾ ከቆዩ በሁዋላ በተለያዩ ጊዜያት በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመግባት ለሽብር ተግባር ተንቀሳቅሰዋል የሚል ውንጀላ እንደቀረበባቸው ታውቋል፡፡ ጥቅምት 3 ቀን 2006 በ አዲስ አበባ ውስጥ ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ፈንጂ በማፈንዳት ጥቃት ለማድረስ ተሰማርተው ከነበሩ ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ጋር በመገናኘት በሽብር ተግባሩ ላይ ተባባሪ ሆነው ተግኝተዋል ሲል አቃቤ ህግ ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ በአቃቤ ህግ ከቀረበባቸው የክስ ማክበጃዎች መካከል የተወሰኑትን ባለመቀበል በተከሳሾቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በማስተላለፍ በፅኑ እንስራት እንዲቀጡ ማድረጉ ተገልፆል፡፡ በፍርድ ቤቱ መሰረትም አንደኛ ተከሳሽ በዘጠኝ አመት ፅኑ እስራት 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በስምንት ዓመት ጽኑ እስራት 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲሁም ሰባተኛ ተከሳሽ በሁለት ዓመት ከስምንት ወር ጽኑ እስራት እጃቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላፉ ተዘግቧል፡፡ መንግስት በሃሰት ሙስሊሞችን በመክሰስ እና በካንጋሮ ፍርድ ቤት በማቅረብ በእስራት እንዲቀጡ እያደረገ ሲሆን በርካታ ሙስሊሞም በማረሚያ ቤት ሆነው የግፍ ፍርዳቸውን በመጠባበበቅ ላይ ይገኛሉ፡ ሐስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል