"ፍቅርህ አሸነፈኝ" የተሰኘውን የኡስታዝ አለላህ መህዲን መፅሃፍ ውጫዊ ሽፋን በመጠቀም የአክፍሮት ሃይላት የራሳቸውን መፅሃፍ ማሳተማቸው ታወቀ
ፍትህ ራዲዬ/ የካቲት 24/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ፍቅርህ አሸነፈኝ በሚል በወጣቱ ዳዒ በኡስታዝ አለላህ መህዲ ተዘጋጅቶ ለንባብ የበቃውን መጽሃፍ የአክፍሮት ሃይላት መፅሃፉን በማመሳሰል የራሳቸውን መፅሃፍ አስመስለው ማሳተማቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
የፕሮቴስታን እምነት ተከታዬቹ የኡስታዝ አለላህን ፍቅርህ አሸነፈኝ የተሰኘውን መፅሃፍ ውጫዊ የሽፋኑን ገፅ ሙሉ በሙሉ በመስረቅ ለራሳቸው መፅሃፍ ውጪዊ ሽፋን በማድረግ ሙስሊሙን ለማታለል መሞከራቸው ታውቋል፡
'ፍቅር አሸነፈኝ" የተሰኘው መፅሃፍ ጀርባ ላይ በተለያዩ ኡስታዞች የተሰጡትን አስተያየቶች ሳይቀር ለራሳቸው በሚመች መልኩ በማስተካከል መጠቀማቸው ተዘግቧል፡፡
መፅሃፉን አንዳርጌ አረጋ የተሰኘ የፕሮቴስታን እምነት ተከታይ ግለሰብ እንዳዘጋጀው የታወቀ ሲሆን ከፍቅርህ አሸነፈኝ ከተሰኘው መፅሃፍ የሰረቁትን ውጫዊ ሽፋኑንም በፓስተር ቴዎድሮስ በዛብህ እንደተዘጋጀ ተደርጎ በመፅሃፉ ላይ መገለፁ ታውቋል፡፡
መፅሃፉ ወርቁን መዳብ አልኩት በሚል የራሱ አርዕስት በውስጠኛው የመፅሃፉ ገፅ ላይ የተፃፈ ሲሆን ውጫዊ የመፅሃፉ ሽፋን ግን ሙሉ በሙሉ የኡስታዝ አለላህ መህዲ መፅሃፍን የሽፋን ገፁን ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
የአክፍሮት ሃይላት ሙስሊሙ የሚጠቀምባቸው ነገሮች በመጠቀም እና በማጭበርበር ሙስሊሙን ወደነሱ እምነት በማታለል ለማስገባት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ የተዘገበ ሲሆን የሙስሊሙን ልብስ በመልበስ የጀመሩት እንቅስቃሴ መንዙማ የመሰለ መዝሙር በማዘጋጀት ሲጠናከር አሁን ደግሞ በሙስሊሙ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸውን መፅሃፍቶች የፊት ሽፋናቸውን አስመስሎ በማዘጋጀት የራሳቸውን መፅሃፍ አሳትመው እያሰራጩ መሆናቸው ተገልፆል፡፡
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሚያደርጉት ሰበካ መልዕክታቸውን ሊቀበል ባለመቻሉ የዚህ መሰሉን ማጭበርበሪያ በመጠቀም መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ እየሞከሩ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
በመፅሃፉ እግዝአብሄር ይወድሃል፣ እግዝአብሄርን ብቻ አምልክ፣ሰዎችን አገልግላቸው፣ ቅደም ተከተል አታዛበ፣ አመፀኛ አትሁን እና የበረከት መንገድ በሚል 6 ምዕራፍ ያለው ሲሆን በኡስታዝ አለላህ መህዲ ከተዘጋጀው ፍቅርህ አሸነፈኝ ከተሰኘው መፅሃፍ አላህዬ እወድሃለው ፣የአላህን ውዴታ የሚያስገኙ ተግባራት በሚል ከተዘረዘሩት ተግባራት ለራሳቸው በሚመች መልኩ ማዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአክፍሮት ሃይላት እየተደረገ ያለበትን መጠነ ሰፊ ዘመቻ ለመመከት ሁል ጊዜም ንቁ መሆን እንዳለበት የተጠቆመ ሲሆን የሚገዛቸውን መፅሃፍቶችም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ኢስላማዊ ስራዎች ትክክለኛ መሆናቸውን ማጣራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ተጨማሪ ምስል