የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት “ሙስሊም ጀምዓ” የተሰኘ የሽብር ቡድን ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል በሚል 23 ሙስሊም እስረኞች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ
ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 2/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በእስማኤል በቀለ የክስ መዝገብ ለእስር በተዳረጉት 23 ሙስሊሞች ላይ የጥፋተኝነት ብይን ማስተላለፉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
አቃቤ ህጉ በነዚህ 23 ሙስሊሞች ላይ የሽብር ክስ ያቀረበባቸው ሲሆን በኢትዬጲያ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል ሲል ቅስ እንዳቀረበባቸው ታውቋል፡፡
ተከሳሽ ሙስሊሞቹ ከ 2004 እስከ 2014 ድረስ ሙስሊም ጅመዓ የተሰኘ የሽብር ቡድን መመስረታቸውን አቃቤ ህጉ በክሱ ያቀረበ ሲሆን ከሽብር ክሱ በተጨማሪ በግድያ እና በዘረፋ ወንጀልም ተጨማሪ ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡
የሙስሊም ጀምዓ የተሰኘ ቡድን ከመመስረታቸው በተጨማሪም “አቂዳ” የተሰኘ ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ አባል እንደነበሩም በክሱ ላይ ሰፍሯል፡፡

ክስ የተመሰረተባቸው ወንድሞች የአዲስ አበባ፣የኦሮምያ እና የደቡብ ክልል ነዋሪ የነበሩ ሙስሊሞች ሲሆኑ በነዚህ ክልሎች ላይም ዘረፋ ሲያካሄዱ ነበር በሚል ክስ እንደቀረበባቸው ታውቋል

አቃቤ ህጉ ለዚህ ላቀረበው ሃሰተኛ ክስ 41 የሐሰት ምስክሮችን እና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾችም የቀረበባቸውን ሃሰተኛ ክስ አለመፈፀማቸውን የተለያዩ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ መከላከላቸው ታውቋል፡፡
ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በማስተላለፍ የቅታት ውሳኔውን ለማስተላለፍ ለግንቦት 9 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
የክሱ ተጠሪ ወንድም እስማኤል በቀለ ከዚህ ክሱ በተጨማሪ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥለዋል በሚል የሐሰት ክስ ከተመሰተባቸው ወንድሞች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ምስል