የጅማ ከተማ ወጣት ሙስሊም ጀምዓዎች በዝዋይ ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ሙስሊም እስረኞችን ዘየሩ
ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 11/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ከኦሮሚያ ክልል ከጅማ ከተማ የተሰባሰቡ ጀምዓዎች በዝዋይ ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙትን ወንድሞች መዘየራቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረበች ዘግበዋል፡፡
እሁድ ሚያዚያ 8 ከጅማ ከተማ በለሊት በመነሳት ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት በመሄድ ዚያራቸውን ማከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡
በዚያራቸው በከድር መሐመድ መዝገብ ተወንጅለው 5 አመት ከ6ወራት የተበየነባቸውን ሙስሊም ወንድሞች የዘየሩ ሲሆን በዚያራውም እስር ላይ ያሉት ወንድሞች መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
ከጅማ ከተማ 590ኪሜ ርቀት በማቋረጥ ለሊት ሙሉ በመጓዝ ወደ ዝዋይ ለዚያራ ያመሩ ሲሆን 43 የሚደርሱ ወጣቶች በዚያራው ላይ መካፈላቸው ተዘግቧል፡፡
ከጅማ ከተማ ድረስ ለዚያራ የሚሆን ስጦታ በመያዝ ዚያራውን ያካሄዱ ሲሆን በእስር ላይ ያሉ ወንድሞችን የጅማ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች እንዳልዘነጓቸው በዚያራቸው አረጋግጠውላቸዋል፡፡
በተደረገላቸው ዚያራም መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን ከጅማ ዝዋይ ድረስ እነሱን ለመዘየር በመምጣታቸው መደሰታቸውን በመግለፅ ሙስሊሙ ለነሱ ያለው ትልቅ ቦታ ይበልጥ እንዲረዱት እንዳደረጋቸው ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የሚገኙ ሙስሊሞችም የጅማ ወጣቶችን ዚያራ እንደ አርአያ በመውሰድ በዝዋይ፣በቂሊንጦ እና በቃሊቲ በእስር ላይ ያሉትን ወንድሞች ሊዘይሩ እና ሊያበረታቱ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል