የደሴው ወንድም እስማኤል ሐሰን የእስር ጊዜውን ጨርሶ መፈታቱ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 30/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሶ የ 5 አመት የግፍ እስራት ተበይኖበት የነበረው ወንድም እስማኤል ሐሰን የእስር ጊዜውን ጨርሶ መፈታቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
ወንድም ኢስማኤል በቀረበበት ክስ በዝቅተኛ አንቀፅ ጥፋተኛ ተብሎ የ 5 አመት የግፍ ብይን ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን የአመክሮ ጊዜ ሳይታሰብለት የእስር ጊዜውን ጨርሶ መፈታቱ ታውቋል፡፡
ወንድም እስማኤል ሐሰን ጥፋተኛ በተባለበት አንቀፅ እስካሁን የታሰረበት ጊዜ ያህል ሊያስፈርድበት የሚችል ብቻ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 5 አመት እስራት እንደበየነበት ይታወሳል፡፡
የደሴው እስማኤል ሐሰን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ በከፍተኛ ውጤት የተመረቀ ሲሆን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም በሌክቸረርነት ተማሪዎችን ሲያስተምር ቆይቷል፡፤
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታም ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ውጤታቸውን የሚመለከቱበት የሞባይል ሶፍት ዌር በመስራት ለዩኒቨርሲቲው ያበረከተ ሲሆን ለዚህ ድንቅ ስራውም ዩኒቨርሲቲው የእውቅና ሰርተፍኬት እና ገንዘብ ሽልማት አበርክቶለታል፡፡
በተለያዩ የፈጠራ ችሎታው ሃገሩን እያገለገለ የሚገኘው ይህ ወጣት ለእረፍት ወደ ደሴ ከተማ በተመለሰበት የሼህ ኑሩን መገደል ተከትሎ ለእስራት መዳረጉ ይታወቃል፡፡
ለ4 አመታት በግፍ እስራት ከቆየ ቡሃላ የእስር ጊዜውን አጠናቆ ከማረሚያ ቤት መፈታቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ተጨማሪ ምስል