ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ
የየቲሞች አባት በመባል የሚታወቀው ኡስታዝ አብዱልፈታህ ሙስጠፋን ጨምሮ8 ሙስሊም ወንድሞች ክስ ተመስርቶባቸው ፍ/ቤት መቅረባቸው ተዘገበ
ፍትህ ራዲዬ/ መጋቢት 22/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአዲስ አበባ በአዲስ ክ/ከተማ በሚገኘው በባዩሽ እና በፈትህ አባቦራ መስጂድ ዙሪያ ሲንቀሰቀቀሱ የነበሩ 8 ሙስሊም ወንድሞች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
የየቲሞች አባት በመባል የሚታወቀው ኡስታዝ አብዱልፈታህ ሙስጠፋን ጨምሮ ሌሎች 7 ሙስሊሞች በአንድ የክስ መዝገብ መከሰሳቸው የታወቀ ሲሆን አቃቤ ህጉ በፌደራሉ የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት ክሱን እንዳቀረበባቸው ታውቋል፡፡
አቃቤ ህጉ በአንድ የክስ መዝገብ ውስጥ 3 ክሶችን ያካተተ ሲሆን ክስ 1 ፣ክስ 2 እና ክስ 3 በሚል እንደከፋፈለው ጠበቃቸው አቶ ሙስጠፋ ለፍትህ ራዲዬ ገልፆል፡፡
በክስ 1 ላይ ከ1ኛ ተከሳሽ እስከ 4ኛ ተከሳሾች የተካተቱ ሲሆን በክስ 2 ላይ ደግሞ 5ኛ፣6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች መካተታቸው ታውቋል፡፡
በክስ ሶስት ላይ ለብቻው የየቲሞች አባት በመባል የሚታወቀው ኡስታዝ አብዱልፈታህ ሙስጠፋ እንደተካተተበት ተዘግቧል፡፡
አቃቤ ህጉ በክስ አንድ ላይ ከ ለአመትከ 8 ወር በፊት ማለትም 14/8/2007 በተለምዶ አደሬ ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ መንግስትን በሃይል መገልበጥ አለብን፣ኢስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን፣ኮሚቴው ይፈታ የሚል ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት ህዝቡን ቀስቀሰዋል በሚል በኢፌደሪ የወንጀል መቅጫ ህገ ደንብ አንቀፅ 32 ንዑስ ሀ እና 486 ተላልፋቹሃል በሚል መሆኑ ተገልፆል፡፡
በክስ ሁለት ላይ ደግሞ በኢፌደሪ የወንጀል መቅጫ ህገ አንቀፅ 32/1 /ሀ እና 486/ለ የተመለከተውን ተላልፋቹሃል የሚል ክስ ያቀረበ ሲሆን በ26/10/2007 በተለምዶ አደሬ ሰፈር ተብሎ ቢጣው አካባቢ ድምፃችን ይሰማ፣ቃላችን አይቀየርም፣.የታሰሩት ኮሚቴዎች ይፈቱ፣ የክርስቲያን መኪና መቆም የለበትም በሚል መኪናውን በሃይል አስነስዋል በሚል አቃቤ ህጉ ክሱን ማቅረቡ ተዘግቧል፡፡
በክስ ሶስት ላይ ደግሞ ኡስታዝ አብዱልፈታህ ሙስጠፋን የተመለከተ ክስ የቀረበ ሲሆን በ20/10/2007 በፈትህ አባቦራ መስጂድ ውስጥ የኢማሙ ቦታ በመቆም ትምህርት ለመስጠጥ የኢማመኑን ፈቃድ አትጠይቁ በማለት ቅስቀሳ አድጓል በሚል ክስ እንደተመሰረተበት ታውቋል፡፡
የአቃቤ ህግ ክስ ለተከሳሾች በ14/4/2009 እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን ተከሳሾች ለመጀመሪያ ጊዜም በ የካቲት 8/2009 ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል፡፡
አቃቤ ህጉ ላቀረበው ክስም የተከሳሽ ጠበቆች የቃል መከላከያ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት 4ኛ ተከሳሽ የሆነው ሰይፈዲን ሃይረዲን ከአንድ አመት በፊት በተመሳሳይ ክስ ተከሶ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዳሰናበተው በመግለፅ በድጋሚ ሊከሰስ አይገባም በማለት ጠበቆች መቃወሚያቸውን ማቅረባቸው ታውቋል፡፡
በክስ 1 እና 2 የተገለፀው ክስም ተብራርቶ እንዲቀርብ በሚል መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በኡስታዝ አብዱልፈታህ ሙስጠፋ ላይ የቀረበው ክስም ከሌሎቹ 7 ተከሳሾች ጋር በቦታም ሆነ በአቅጣጫ የተለየ በመሆኑ በአንድ መዝገብ ከነሱ ጋር ተከሶ ሊቀርብ አይገባም በሚል መቃወሚ ማቅረባቸውን ጠበቃቸው ሙስጠፋ ለፍትህ ራዲዬ ገልፆል፡፡
አቃቤ ህጉም ለቀረበበት የክስ መቃወሚያ ምላሹን መጋቢት 19/2009 ለፍርድ ቤቱ በፅሁፍ ያቀረበ ሲሆን በተከሳሾች ጠበቃ እና በከሳሽ አቃቤ ህግ መካከል የተካሄደውን ክርክር በማድመጥ በዛሬ እለት መጋቢት 22 ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተካለፉ ተዘግቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረትም አራተኛ ተከሳሽ ወንድም ሰይፈዲን ኸይረዲን በድጋሚ ሊከሰስ አይገባም በሚል በነፃ እንዲሰናበት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን በ8ኛ ተከሳሽ በሆኑት በኡስታዝ አብዱልፈታህ ላይ የቀረበውም ክስ ከሌሎቹ ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ አቃቤ ህጉ ከሌሎቹ ተከሰሾች ጋር አብሮ አጣምሮ ክሱን ማቅረብ የለበትም በማለት ከክሱ ላይ እንዲወጣ ውሳኔ ማስተላለፉ ተዘግቧል፡፡
በተቀሩት ተከሳሾች ላይ ክሱ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ የወሰነ ሲሆን አቃቤ ህጉ በተቀሩት ተከሳሾች ላይ ያሉትን ምስክሮች በሚያዚያ 19 ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ውሳኔ ማስተላለፉ ጠበቃ ሙስጠፋ ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
በኡስታዝ አብዱልፈታህ ላይም አቃቤ ህጉ ክስ ማቅረብ ከፈለገ ለብቻው በሌላ መዝገብ አድረጎ በሚያዚያ 19 አቃቤ ህጉ ምስክሮቹን ለማስደመጥ ሲመጣ አብሮ ክሱን ይዞ እንዲመጣ ትዕዛዝ መሰጠቱ ታውቋል፡፡
ከጠበቃ ሙስጠፋ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በዛሬው ምሽት የእለታዊ ዜናችን ላይ ይጠብቁን

ተጨማሪ ምስል