ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በአህባሾች ሰበብ እየታሰሩ እና እየተዋከቡ መሆኑ ተዘገበ

ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር26/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች ወሃቢይ አክራሪ በሚል ለእስር እየተዳረጉ መሆናቸውን ተማሪዎቹ ለፍትህ ራዲዬ ገልጸዋል፡፡

ፅንፈኛ የአህባሽ አመራሮች የሚመሩት የአማራ ክልል ህገ ወጡ መጅሊስ በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ አህባሽን የማስፋፋት ስራ እየሰራ የሚገኘው ሲሆን ጠንካራ ሙስሊሞች ይወጡበታል ተብሎ የሚገመተውን የዩኒቨርሲቱ ሙስሊም ጀምዓዎችንም በመበታተን ተማሪዎችን እያሳሰሩ መሆናቸው ተገልፆል፡፡

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች የሚገለገሉበትን መስጂድ ህገ ወጡ የአህባሽ መጅሊስ ባሳፍነው ሃሙስ አዲስ የአህባሽ ኢማም የሾመባቸው ሲሆን ኢማሙን ተከትለን አንሰግድም ያሉ ተማሪዎች ለእስራት መዳረጋቸውን ተማሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በሳለፍነው ጁምዓ የአህባሽ ኢማሙን ተከትለን አንሰግድም በሚል ሁለተኛ ጀምዓ የሰገዱ 9 ተማሪዎች መታሰራቸው የተዘገበ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሁለተኛ ጀምዓ የሰገዱ ሶስት ተማሪዎች መታሰራቸው ታውቋል፡፡

አህባሾቹ ከመንግስት ሃይሎች ጋር በመተባበር ጠንካራ ሙስሊሞችን እያሳሰሩ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በወሎ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥም በየዶርሙ የወሃቢይ መፅሃፍ ይዘዋል በሚል በጥቆማ ተማሪዎች እየታሰሩ መሆናቸውን ተማሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

እስካሁን የታሰሩት 12 ተማሪዎች በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ እና በቧንቧ ውሃ ፖሊስ ጣብያዎች ታስረው የሚገኙ ሲሆን የግቢው ሙስሊም ጀምዓ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የአህባሽን አስተሳሰብ የማይቀበለውን ተማሪ አክራሪ ነው፣ፀረ ሰላም ነው እያሉ በየዶርሙ ኪታቦች እየተጠቆመ እየተወሰደ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ዜጎች የፈለጉትን እምነት የማመን መብታቸው በዩኒቨርሲቲው አህባሾች እየተጣሰ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ህገ ወጡ የአህባሽ መጅሊስ ተማሪዎች የሚያነቡትን እና የሚማሩትን ኪታብ ሳይቀር ለመቆጣጠር እየጣረ ሲሆን በግቢው ተማሪዎች እና በዙሪያው ላይ በርካታ ሰላዬችን እና ወሬ አቀባዬችን በማሰማራት ሙስሊም ተማሪውን እንዳይነጋገር እና በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ እያሸማቀቁት መሆናቸው ታውቋል፡:

በህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ላይ የዜጎችን የእምነት ነፃነት በግልፅ ቢደነግግም አህባሾች እና የመንግስት አካላትን ይህን ድንጋጌ በመተላለፍ ተማሪዎችን በግዳጅ የአህባሽ አስተሳሰብ እንዲቀበሉ እያስገደዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ላይ ማንኛውም ሠው የመረጠውን ሀይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ሀይማኖቱን አና እምነቱን ለብቻው ወይንም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ የመከተል የመተግበር የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ሲደነግግ በሌላ ንዑስ አንቀጽ ወይም ንዑስ 3 ላይ ደግሞ ማንኛውም ሠው የፈለገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነጻነት በኀይል ወይም ሁኔታ በማሥገደድ መገደብ ወይም መከልከል አይቻልም የሚል ድንጋጌ መስፈሩ ይታወቃል፡፡

ተማሪዎቹ እየተፈፀመባቸው የሚገኘውን እስራት እና እንግልት በግልፅ ለመናገር በስጋት ላይ ሲሆኑ በአህባሾች የተነሳም የጀምዓ ሰላት ለመስገድ መቸገራቸውን ገልፀዋል፡፡

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ በአሁኑ ወቅት እየተፈፀመ የሚገኘው በደል እና ግፍ እየጨመረ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአህባሾች እና በመንግስት አካላት በተማሪዎቹ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን በደል እና ግፍ ይወቅልን ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡

ሐስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል

ተጨማሪ ምስል