ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ
የወልድያ ሰላም መስጂድ ለታላቁ የረመዳን ወር መስጂዱን ለማደስ እና አዲስ ምንጣፍ ለማንጠፍ የተደረገውን ዝግጅት በህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታገድ ተደረገ
ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 17/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ የሚገኘው ታላቁ የሰላም መስጂድ ለታላቁ የረመዳን ወር ለሙስሊሙ ምቹ ለማድረግ መስጂዱን ለማሳደስ እና አዲስ ምንጣፍ ለማንጠፍ የተደረገው ዝግጅት በወልድያ ከተማ ህገ ወጡ መጅሊስ እንዲታገድ መደረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
አንድ ወር ለቀረው የረመዳን ወር መስጂዱን ለማሳደስ እና አዲስ ምንጣፍ ለማንጠፍ ዝግጅት ከተጠናቀቀ ቡሃላ የወልዲያ ሙስሊሞችን እያንገላታ የሚገኘው የህገ ወጡመጅሊስ አመራር አቶ ሰይድ ኢድሪስ ከወልድያ ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ከሆነው ከአቶ ሙሉቀን ማርዬ ጋር በመሆን መስጂዱም እንዳይታደስ አዲሱ ምንጣፍም በመስጂዱ እንዳይነጠፍ ማሳገዳቸው ታውቋል፡፡
በሚያዚያ 16 /2009 መስጂዱን ለማሳደስ ሲያስተባብሩ የነበሩ የከተማዋን ሙስሊሞ የወረዳው የጸጥታ ቢሮ በማስጠራት ለመስጂዱ ተብሎ የተላከው ምንጣፍ ማነው የላከው፣አድራሻውን አምጡ፣ለመስጂዱ እድሳትም ግዘቡን ያዋጡት እነማን ናቸው ስም እና ስልክ ቁጥራቸውን አምጡ ፣አልያ ግን ትታሰራላችሁ በሚል ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንደተፈፀመባቸው ተዘግቧል፡፡
በየአመቱ የረመዳን ወር ሲመጣ ህዝበ ሙስሊሙ በየአቅራቢያው የሚገኙ መስጂዶችን በማሳደስ አዲስ ምንጣፍ እንደሚቀይር የሚታወቅ ሲሆን በወልዲያ ሰላም መስጂድም በተመሳሳይ መስጂዱን በማሳደስ አዲስ ምንጣፍ በማንጠፍ ታላቁን የረመዳን ወር መስጂዱ ለኢባዳ ምቹ ለማድረግ የአካባቢው ሙስሊሞች ያደረጉት ጥረት በህገ ወጡ መጅሊስ እና በወረዳው የጸጥታ ቢሮ እንዲታገድ መደረጉ የአካባቢውን ሙስሊም ማህበረሰብ ማሳዘኑ ተዘግቧል፡፡
ህገ ወጡ መጅሊስ የሙስሊሙን ገንዘብ በመመዝበር ጫት ከመቃም ውጪ የሚሰራው ስራ ባለመኖሩ ሙስሊሙ በየቦታው ለሚያደረገው ኢስላማዊ እንቅስቃሴ በሙሉ ከመንግስት ጋር በመሆን ሙስሊሙን እያገደ መሆኑ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ምስል