የወልድያው መድረሰተል ሰላም አል ኢስላሚያ መምህራን በህገወጡ መጅሊስ ላይ ባቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ ዳግም ለታህሳስ 11 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 1/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ ከአወልያ ቀጥሎ ለሙስሊሙ ትልቁ ተቋም የነበረው የወልዲያ መስጂዶች እና ትምህርት ቤቶች ማዕከል ከህዝብ ተወስዶ ለህገ ወጡ መጅሊስ ከተሰጠ ቡሃላ ህገ ወጡ መጅሊስ ለማስተዳደር ባለመቻሉ ዳግም ለህዝቡ ቢመለስም በተቋሙ ስር የነበሩትን የዲን መድረሳዎች አህበሽ መራሹ መጅሊስ ማስተዳደር የሚገባኝ እኔ ነኝ የሚል ጥያቄ በማንሳቱ መንግስት መድረሳዎቹን ለመጅሊሱ አሳልፎ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ የወልዲያ ከተማ የመንግስት አካላት በተቋሙ ስር የነበሩትን ትምህርት ቤቶች የዲን እና የአካዳሚክ ትምህርቶች ተለይተው እንዲሰጡ ማስደረጉ የሚታወስ ሲሆን በህዝብ የተመረጠውን ኮሚቴ አካዳሚኩን ብቻ እንዲያስተዳደር፣ የዲን መድረሳዎችን ግን በአህባሾች እንዲተዳደር እንዲደረግ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ የወልዲያ መድረሳዎች የሚተራደሩበት የነበረው የማዕከሉ ገቢ ማስገኛዎችን ህገ ወጡ መጅሊስ በጉልበት የተረከባቸው ቢሆንም በመድረሳዎቹ የሚያስተምሩትን መምህራኖች ደሞዝ ሊከፍል አለመቻሉ ተዘግቧል፡፤ በተደጋጋሚ መምህራኖቹ ለ 11 ወራት የሰሩበትን ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው ለህገ ወጡ መጅሊስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሊያገኙ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸውን የፍትህ ራዲዬ መዘገቧ ይታወሳል፡፤ መምህራኖቹ ህገ ወጡ መጅሊስ እየፈፀመበቸው የሚገኘውን በደል ለፍርድ በቱ በማስረጃ በማቅረባቸው ህገ ወጡ መጅሊስ ለቀረበበት ክስ በቂ የሆነ መከላከያ ማቅረብ ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ የሰጠበት ሲሆን በዚህ ውሳኔ የተደናገጡት የህገ ወጡ መጅሊ አመራሮች ይህን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለማስቀየር ሲንቀሳቀሱ ቆይታዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የመጨረሻ ውሳኔውን በግንቦት 16/2008 ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን ህገ ወጡ መጅሊስ ለመምህራኖቹ ደመዞቸውን እንዲከፍል መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎም የክልል እና የሰሜን ወሎ ህገወጡ መጅሊስ አመራሮችም በተወሰነው ውሳኔ በመደናገጥ የተለያዩ ሰዎችን መርጠው ከመንግስት አካላት ጋር ሲነጋገሩ መቆየታቸውን የ ፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡ ህገ ወጡ የወልዲያ መጅሊስ የተሰጠበትን ውሳኔ በመቃወም ለሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኘው ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን በመንግስት የሚሾፈረው ፍርድ ቤቱን የህገ ወጡን መጅሊስ ይፍባኝ በመቀበል የታችኛው ፍርድ ቤት ለመምህራኖቹ ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው የወሰነውን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ በባዶ እንዲሰናበቱ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ የታችኛው ፍርድ ቤት ከህግ አግባብ ውጪ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሁለቱን ወገኖች ሲያከራከር ቆይቷል፣ በሃይማኖት ጉዳዬች ጣልቃ ገብቶ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፍም አልነበርበትም በሚል ለሰላም መድረሳ መምህራኖች ተበይኖላቸው የነበረውን ውሳኔ የሰሜን ወሎ ከፍተኛው ፍርድ ቤቱ እንዲቀለበስ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎም የ 11 ወር ደሞዛቸው የተከለከሉት መምህራን በድጋሚ ይግባኝ በመጠየቅ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት ሲሆን ይግባኛቸውን ለመመልከት ለትላንት ጥቅምት 29 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 29/2009 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በቀነ ቀጠሮ መሰረት ጉዳያቸው እንዲታይላቸው ቢጠባበቁም ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ለታህሳስ 11 እንደሰጣቸው የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡