የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ አዲሱ መጽሃፍ በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 27/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከ4አመት ከ 2 ወራት በግፍ እስር ያሳለፈው እና በቅርቡ የተፈታው የየቲሞች አባት በመባል የሚታወቀው ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የቲምነት የማህበረሰቡ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው የተሰኘ አዲስ መፅሀፍ ፅሆ በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ በእምቢልታ አዳራሽ ማስመረቁን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ይህን መፅሃፍ ያዘጋጀው በዝዋይ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን የግድያ ሙከራ ከተደረገበት ቡኋላ ለኡማው የሚጠቅም ምንም ሳላበረክት ሞቼ ነበር በሚል ተነሳሽነት የቲምነት የማህበረሰቡ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው የተሰኘ አዲስ መፅሀፍ ለማዘጋጀት መቻሉን ለፍትህ ራዲዬ ገልፆል፡፡ መፅሃፉ 112 ገፆች ያሉት እና የቲም ምን ማለት እንደሆነ፣ የቲሞችን መንከባከብ በኢስላም ያለውን ደረጃ፣የቲሞችን መበደል ያለውን አደጋ ከቁርአን እና ከሃዲስ በማጣቀስ ሰፊ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ያለውን የየቲሞች ችግር እና መፍትሄዎቻቸውንም በመፅሃፉ ተዳሰዋል፡፡ በዛሬው እለት ጥቅምት 27/2009 በእምቢልታ አዳራሽ በርካታ ህዝበ ሙስሊም በታደመበት በደማቅ ሁኔታ የተመረቀ ሲሆን በምረቃ ነ ስርአቱ ላይም የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣የተለያዩ ኡስታዞች እና መሻይኮች መካፈላቸው ተዘግቧል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የክብር እንግዶች ከነበሩት አሊሞች እና ኡስታዞች መካከል ሸኽ ሰኢድ፣ሀጅ መሀመድ አወል ረጃ ፣ኡስታዝ አብዱፈታህ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ፣ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፣ኡስታዝ ሰኢድ አሊ፣ኡስታዝ ራያ ፣ኡስታዝ ሀይደር ፣ኡስታዝ መሀመድ ፈረጅ ፣ኡስታዝ ነስሩ ኸድር እና ሌሎችም መካፈላቸው ተገልፆል፡፡ የምረቃ ስነ ስርአቱን ወንድም ዲን አሊ እና ሙሳ ኑረዲን ሲመሩት የነበረ ሲሆን ፕሮግራሙ በቁርአን ከተከፈተ ቡሀሏ የመፅሃፉ አዘጋጅ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ስለመፅሃፉ አጭር ገለፃ በማድረግ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን መፅሃፍ በወላጅ እናቱ እና ባለቤቱን እንዲመረቅ ማስደረጉ ታውቋል፡፡ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የቲሞችን በመንከባከብ እና በመደገፍ ላቅ ያለ ስራ እየሰሩ ለሚገኙ ሰዎች የሽልማት እና የምስክር ወረቀት ያበረከተ ሲሆን እነሱም ሃጂ መሃመድ አወል ረጃ፣ ወንድም ዲኑ ዓሊ ፣ ኡስታዝ አ/ፈታህ ሙስጠፋ እና ወንድም ሃሺም መሆናቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ይህ መፅሃፍ የመጀመሪያ እትሙ 3000 ኮፒዎች ታትመው ለምረቃ ቀርበው የነበረ ሲሆን ባስደቂ ሁኔታ ሁሉም መፅሃፍቶች በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ ተሽጦ ማለቁ ተዘግቧል፡: ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የመፅሃፉ ዋጋ በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ በሚገኘው ህዝበ ሙስሊም ይወጣለታል ባለው መሰረት ከታዳሚው በኩል በተሰጠ ዋጋ መሰረት ለምረቃ ስነ ስርአቱ መፅሃፉ በ 100 ብር ለገበያ ደግሞ በ 50 ብር እንዲሸጥ የዋጋ ተመን እንደወጣለት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ 2 መፅሃፎች እያንዳንደቸው በ 20ሺህ ብር፣ ከአምስት በላይ መፅሀፎች አያንዳንዳቸው በ10,ሺህ ብር ከ7 በላይ መፅሀፎች ደግሞ አያንዳንዳቸው በ5 ሺህ ብር ባስደናቂ ሁኔታ መሸጣቸው ተዘግቧል፡፡ ከ20 በላይ ታዳሚያኖች እያንዳንዳቸው 100 መፅሀፍ በ50 ብር ተመን በመግዛት ለምረቃ ነ ስርአቱ የቀረበው የመጀመሪያው እትም ሙሉ ለሙሉ ተሸጦ መጠናቀቁ ተገልፆል፡፡ ሁለተኛው እትምም በቀጣይ ቀናቶች ታትሞ ለገበያ እንደሚቀርብ የተገለጸ ሲሆን መፅሃፉን ከህዳር 2 ቡኋላ በሁሉም ኢስላማዊ መፅሃፍት መደብር ውስጥ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡ የፈትህ አባቦራ የየቲሞች መርጃ ተቋም በአዳራሹ ውስጥ የተገኘውን ህዝበ ሙስሊም በማስተናገድ የምረቃ ስነ ስርአቱ የተሳካ እንዲሆን ሃላፊነታቸውን ሲወጡ የነበረ ሲሆን በመድረኩ ላይም ከእስር የተለቀቁት ኡስታዞች እና ወንድሞች ስለ መፅሃፉ አጠር ያለ ገለፃ በየተራ ማድረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦችዘ ዘግበዋል፡፡ ይህን መፅሃፍ ከሃገር ውጪ የሚገኙ ጀምዓዎችም እንዲያሳትሙት ጥሪ የቀረበ ሲሆን በቅርቡም በዱባይ እና ሳኡዲ አረቢን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራትም ይህ መፅሃፍ ታትሞ ለንባብ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል፡፡ አላሁ አክበር