የታላቁ የረመዳን ፆም የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 19 እንደሚጀመር ተገለፀ

ረመዳን ሙባረክ

 ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 17/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በመላው አለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የታላቁ የረመዳን ፆም የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 19 እንደሚጀመር የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የሳኡዲ አረቢያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው መግለጫ መሰረት በዛሬው እለት  ሃሙስ ግንቦት 17 ጨረቃ ልትታይ ባለመቻሏ የረመዳን ፆም ቅዳሜ አንድ ብሎ እንደሚጀመር አስታውቋል፡፡

በነገው እለት ጁምዓ ግንቦት 18 የሻዕባን ወር የመጨረሻ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ቅዳሜ የረመዳን የመጀመሪያ ቀን መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡

የታላቁ የረመዳን ወር በመላው አለም የሚገኙ ሙስሊሞች በፆም የሚያሳልፉት ሲሆን ይህን የተከበረ ወር ለመቀበል ሁሉም በየፊናው ሲዘጋጅ መቆየቱ ታውቋል፡፡

በዘንድሮ ረመዳን 4 ጁምዓዎች እንደሚኖሩ የተገለጸ ሲሆን  ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፆሙን ሲፆም ሚስኪኖችንም በማሰብ  አብሯቸው በማፍጠር አጋርቱን ሊያሳይ እንደሚገባ ተገልፆል፡፡

በእስር ላይ የሚገኙትንም ሙስሊሞች ሄዶ በመዘየር፣በማስፈጠር እና ቤተሰቦቻቸውን በመንከባከብ አጋርነቱን እና ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ፍትህ ራዲዬም ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ 1438 የታላቁ የረመዳን ፆም በሰላም አደረሰን ለማለት ትወዳለች

ተጨማሪ ምስል