የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በሜልቦርን ተቃውሞ ላይ የተሳተፉ ዜጎችን ለመበቀል ሃገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸው እንዲታሰሩ ማድረጉ ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 29/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ የተለያዩ ሰብአዊ መብት ጥሰት በመፈፀም የሚታወቀው በአቶ አብዲ መሐመድ የሚመራው የሶማሌ ክልል አስተዳደር በሰኔ ወር በአውስትራሊያ ሜልቦርን በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ የሶማሌ ተወላጆችን ለመበቀል በሀገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸውን እንዲታሰሩ ማስደረጉን ሂውማን ራይተስ ዎች የተሰኘው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ የሶማሌ ክልል የልኡካን ቡድንን ወደ አውስትራሊያ ባመራበት ወቅት የአውስትራሊያ የኢትዬጲያውያን ኮሚኒቲ አባላት በተለይም የሱማሌ ክልል ተወላጆች የልኡካን ቡድኑን በመቃወም ከባድ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያትም የልኡካን ቡድኑ በታሰበለት ፕሮግራም ላይ ሳይገኙ የቀረበ ሲሆን የተያዘላቸውም ፕሮግራም መሰረዙ ይታወቃል፡፡ በሜልቦርን በተካሄደው በዚህ ተቃውሞ ላይ የአውስትራሊያ መንግስት ለአንባገነኑ የኢትዬጲያ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ ኢትዬጲያውያኑ መቃወማቸው ተዘግቧል፡፡ በተቃውሞ ላይ የተሳተፉት የሶማሌ ክልል ተወላጆች የሆኑ ዜጎች ከሰልፉ መጠናቀቅ ቡኋላ በሶማሌ ክልል የሚኖሩ በርካታ ቤተሰቦቻቸው ለእስራት መዳረጋቸውን መስማታቸው ተገልፆል፡፡ በሰልፉ ላይ የተሳተፉ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በሃገር ቤት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለአስከፊ እስር የተዳረጉባቸው ሲሆን ያለምንም ፍትህ ለ 4 ወራት በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ሂውማን ራይተስ ዎች አስታውቋል፡፡ የኢትዬጲያ መንግስት በዲያስፖራ ያለውን ማህበረሰብ ለማፈን የተለያዩ ዘዴዎችን እንደሚጠመቀም ይህ የሰብአዊ መብት ተቋም ያስታወቀ ሲሆን በሃገር ቤት ያለውንም ተቃውሞ ለማፈን እየወሰደ ያለውን የሃይል እርምጃ በተደጋጋሚ ይህ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማጋለጡ የሚታወስ ነው፡፡ በአቶ አብዲ መሀመድ የሚመራው የክልሉ መንግስት የራሱ የሆነ ታጣቂ ልዩ ሃይል ያለው ሲሆን በኦጋዴን ከፍተኛ የዘር ፍጅት ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የክልሉ መንግስት በተለይም አቶ አብዲ መሐመድ በአምባገነንነት የሚፈፅመውን ግድያ እና የመብት ረገጣ የሚያጋልጡ በስደት ላይ የሚገኙ የሶማሌ ክልለ ተወላጆችን ቤተሰቦቻቸውን በሃገር ቤት ውስጥ እንዲገደሉ በማድረግ እየተበቀለ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡ አቶ አብዲ መሐመድ በክልሉ በሚገኘው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የአህባሽ እና ሺዓ አስተሳሰብ እንዲሰርፅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የክልሉን መጅሊስ እና የሸሪአ ፍርድ ቤት በአህባሾች እንዲመራ በማድረግ በየመሳጂዶቹ የሱና ኢማሞችን በማባረር የአህበሽ ኢማሞች እንዲተኩ ማስደረጉ ይታወቃል፡፡ በዲናቸው ጠንካራ የሆኑ ኡለሞች እና ዱአቶችንም ያለ በቂ ምክንያት በማሰር እና በማስፈራራት በክልሉ ምንም አይነት ዳዕዋ እንዳደርጉ ሲከለክል እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡