የሙስሊሙ ቀንደኛ ጠላት የሆነው ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የትምህርት ሚኒስተር ተደርጎ ተሾመ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 22/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከምርጫ 2007 ቡኋላ አቋቁመውት የነበረውን ካቢኔ በመበተን አዲስ የአካቢኔ አባላትን በዛሬ እለት ይፋ ማድረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በዘንድሮ አመት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የተከሰተውን ከባድ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነኝ በሚል ፕሮፖጋንዳ እየሰራ የሚገኘው ገዢው መንግስት ህዝቡን ያስቆጡትን ችግሮች እቀርፋለው በሚል አዲስ ካቢኔ መመስረቱ ታውቋል፡፡ በዛሬው እለት ጠ/ሚኒስተር ሃይለማርያም የተወካዬች ምክር ቤት ቀርበው አዲሱ ካቢኔያቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከህዝቡ በኩል ሲነሳ የነበረውን የብሄር ጭቆና ምላሽ እንዳገኘ ለማስመሰል ከኦሮሚያ ክልል ከፍ ያለ ቁጥር ያለው ሚኒስተሮችን መሾማቸው ተዘግቧል፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዶ/ር ወርቅነህ ገበየው ሲተኩ ውሸት በሚዲያዎች በማሰራጭ ወደር የማይገኝለት የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ጉዳዬች ፅ/ቤት ሃላፊ ሚኒስተር አቶ ጌታቸው ረዳ በዶ/ር ነገሪ ሌንጮ መተካታቸው ታውቋል፡፡ በጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነኝ እያለ የሚገኘው መንግስት ስልጣንን ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ አመራሮችን ከቦታቸው በማንሳት ብቃት ያላቸውን አመራሮችን እንተካለን ሲል ቢቆይም በሙስሊም ኢትዬጲያውያን ላየ ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ አሳርፎ የሚገኘውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያምን የትምህርት ሚኒስተር አድረጎ መሾሙ ሙስሊሙን አበሳጭቷል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር በነበረበት ወቅት አህባሽን ከሊባኖስ በማስመጣት በሙስሊም ኢትዬጲያውያን ላይ በግዳጅ እንዲጫን የመሪነቱን ሚና ሲጫወት የነበረ ሲሆን የሙስሊም ተቋም የሆነውን መጅሊስን ለአህባሾች አሳልፎ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ፅንፈኛ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሲሆን የመንግስትን ስልጣን ተገን በማድረግ የግሉን ሓይማኖት ለማስፋፋት ከመጣሩም በላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላለፉት 5 አመታት የስቃይ እና የመከራ ጊዜያቶችን እንዲያሳልፉ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡ በፉደራል ጉዳዬች ሚኒስተርነትን በሚሰራበት ወቅት የፕሮቴስታንት የእርዳታ ድርጅቶች በስፋት ፍቃድ አግኝተው በመላው ሃገሪቱ እንዲንቀሳቀሱ ጥረት ሲያደረግ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን አብዛኘውን የሙስሊም እርዳታ ድርጅቶችን በአክራሪነት ስም እንዲዘጉ እና ፍቃዳቸው እንዲነጠቅ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በአህባሽ ስልጠናዎች ላይ በመገኘትም ሃይማኖታዊ ብይን ወይም ፈትዋ እስከመስጠት የደረሰ ጣልቃ ገብነት ሲፈፅም የቆየ ሲሆን አክራሪነትን ለመዋጋት ከ 18 አመት በታች የሆኑ ሙስሊም ህፃናት ቁርአን መማር የለባቸውም የሚል ሃሳብ ማቅረቡም ይታወሳል፡፡ በሙስሊሙ ላይ ፅንፍ የወጣ ጥላቻ ያለበት ይህ ግለሰብ ከፌደራል ሚኒስተርነት ተነስቶ የደን እና ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስተር እንዲሆን ተደርጎ የነበረ ሲሆን በሙስሊሙ ላይ ሲያደረስ በነበረው ግፍ እና ጭቆና አመርቂ ስራ ሰርቷል በሚል የትምህርት ሚኒስተር ተደርጎ እንዲሾም መደረጉ ታውቋል፡፡ በሴኩላሪዝም ሽፋን በርካታ ሙስሊሙን የማዳከም ስራ ሲሰራ የቆየው ዶ/ር ሽፈራው በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ለማፈናቀል በሚችልበት ቁልፍ ቦታ ላይ መሾሙ በቀጣይ ለሙስሊሙ ከባድ ፈተና እንደሚሆን ተዘግቧል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ሙስሊሙን ብቻ ሳይሆን በኦርቶዶክስ እምነትም ጣልቃ በመግባት የኦርቶዶክስ እምነትን ለማዳከም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደረግ የቆየ ሲሆን ማህበረረ ቅዱሳን የተሰኘውን ተቋምም በአክራሪነት በመፈረጅ ለማፍረስ ብዙ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በተለይም ሙስሊሙ እና የኦርቶዶክስ ተማሪዎች በግቢያቸው ውስጥ ሃይማኖታዊ ስብስቦችን በመመስረት የሚታወቁ ሲሆን ይህን ስብስብ ለማፍረስ መንግስት ብዙ ጥረት ሲያደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው የትምህርት ሚኒስተርነትን ቦታ በመያዙ በሴኩላሪዝም ሽፋን የጀምዓ ሰላት፣የሂጃብ ክልከላ እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎች ሙስሊም ተማሪዎች እንዳይፈፅሙ የሚያደርገውን ህገ ደንብ በጥብቅ እንዲተገበር እና ሙስሊሙ ከሃይማኖቱ ትምህርቱን እንዲመርጥ አልያ ከትምህርት ገበታው እንዲፈናቀል እንደሚያደረግ ይጠበቃል፡፡ በትልቅ ተሃድሶ ውስጥ ነኝ ሲል የነበረው መንግስት የግል ስልጣኑን በመጠቀም በግል የሚከተለውን እምነት ለማስፋፋት ሲሞክር እና የሌሎችን እምነት በአክራሪነት እና በሽብርተኝነት ስም ለማዳከም ሲሞከር የነበረውን ግለሰብ በሚኒስተርነት መሾሙ መንግስት በቀጣይም በሙስሊሙ ላይ እያደረሰ ያለው አፈና እና በደል አጠናክሮ ለመቀጠል እቅድ እንዳለው አመላካች መሆኑ ተገልፆል፡፡ በህዝብ ዘንድ ከተጠሉ ሚኒስትሮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ዶ/ር ሽፈራው የትምህርት ሚኒስተርን እንዲመራ መመረጡ መንግስት አሁንም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለውን ትልቅ ንቀት ያሳየ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በኢትዬጲያ ውስጥ ሙስሊሙ በትምህርት ዘርፍ እያሳየ የሚገኘውን መነቃቃት እና ተሳትፎ ዳግም ለማቀጨጭ ዶ/ር ሽፈራው ተግቶ እንደሚሰራ እንደመጠበቅ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡