የመቱ ነጃሺ መስጂድ ምክትል ኢማም ኡስታዝ ሚስባህ መሀመድ  ከእስር ተፈቱ

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 3/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኦሮሚያ ክልል የህዝበ ሙስሊሙን የመብት ትግል ተከትሎ በመቱ ከተማ በነጃሺ መስጂድ ይካሄድ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ለእስር ተዳርገው የነበሩት የመቱ ነጃሺ መስጂድ ምክትል ኢማም የሆኑት ኡስታዝ ሚስባህ መሀመድ   ከእስር መፈታታቸውን የፍህ ራዲዬ በልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በጥር 23/2008   የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 7 አመት ከ8 ወር የግፍ እስራት በይኖባቸው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የተበየነባቸውን የእስር ጊዜ በአመክሮ በማጠናቀቃቸው ከእስር መፈታታቸው ተዘግቧል፡፤

ኡስታዝ ሚስባህ ለእስር ሲዳረጉ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በመጀመሪያው እስራታቸው   ለስምንት ወራት ያክል በኢሊባቡር ዞን ማረሚያ ቤት ቆይተው የዞኑ አስተዳደር በነፃ አሰናብቷቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኡስታዝ ሚስባህ በነፃ ከተለቀቁ ከአራት ቀናት ቆይታ በኋላ ዳግም እንደሚፈለጉ ተነግሮአቸው የዞኑ ፖሊስ ወደ ማረሚያ ቤት ዳግም እንደወሰዳቸው ይታወቃል፡፡

የክስ ሂደታቸው በውል ሳይታወቅ ለስምንት ወራት ያለ ምንም ፍርድ በእስራት ከቆዩ በኋላ ዳግም ሲታሰሩ የኦርሞያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶባቸው ነበር፡፡

በክሱም ላይ ሰዎቹን ለጅሃድ አነሳስታችኋል ፣ህገ መንግስቱን በሃይል ለመናድ ሙከራ አድርጋችኋል በሚል እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ኡስታዝ ሚስባህ መሀመድ በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ተወዳጅ እንደነበሩ እና ብዙ ተማሪዎችን ቁርዓን በማቅራት ይታወቁ እንደነበር የመቱ ከተማ ሙስሊሞች የሚገልፁ ሲሆን እኚህን ኢማም መንግስት በግፍ የሃሰት ምስክሮች እንዲቀርቡባቸው አድርጎ የ 7 አመት ከ 8 ወራት እስራት እንዲበየንባቸው ማስደረጉ ይታወሳል፡፡

ኡስታዝ ሚስባህ የእስር ቅጣት ከተበየነባቸው ቡሃላ በማረሚያ ቤት ለ 4 አመት ከ 8 ወራት በግፍ የታሰሩ ሲሆን የአመክሮ ጊዜ ታይቶላቸው  የእስር ጊዜያቸውን አጠናቀው መፈታታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ተጨማሪ ምስል