የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞች በከተማው ለሚገኙ የቲሞች እና ወላጆቻቸው ደካማ ለሆኑባቻው ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 29/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በሃርቡ ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች በከተማቸው የሚገኙ የቲሞችን እና አቅመ ደካማ ወላጆቸች ላሏቸውን ታዳጊዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ ህፃናቱ የቲም በመሆናቸው እና ወላጆቻቸው አቅመ ደካማ በመሆናቸው ለትምህርት የሚስፈልጋቸውን ነገሮች ማሟላት ባለመቻላቸው ተቸግረው የነበረ ሲሆን የሃርቡ ከተማ ሙስሊም ጀምዓዎች የነዚህን ታዳጊ ህፃናት ችግር በመረዳት ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ተዘግቧል፡፡ በዛሬዉ እለት ጥቅምት 29 የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞች ለየቲሞች እና ወላጆቻቸዉ ደካማ ለሆኑባቸዉ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ሰሰላ ተማሪዎች ሙሉ ዩኒፎርም አሰፍተው እንዳለበሷቸው ተገልፆል፡፡ የከተማው ሙስሊሞች ይህን ኸይር ስራ ለመሰራት ከእስር የተለቀቁትን ኮሚቴዎች እና ሃያተል ኩብራን ዘይረው በተመለሱበት ወቅት በገቡት ቃልኪዳን መሰረት መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተማሪዎቹ የቲም በመሆናቸው እና ወላጆቸቸው አቅመ ደካማ በመሆናች ከትምህርት ገበታቸው ሊሰናከሉ አይገባም በሚል ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ተዘግቧል፡፡ የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞች 360 ኪሎሜትር በማቋረጥ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ከእስር የተፈቱትን ኮሚቴዎች መዘየራች የሚታወስ ሲሆን በዚያራቸውም ለሁሉም ለተፈቱት ኮሚቴዎቻችም የሰላም መገለጫ የሆነውን ነጭ ሻል እንዲሁም ለእህት አያተል ኩብራም መስዋትነት የከፈለችለትን ሂጃብ አንድ ሙሉ ጅልባበ ከክሬም ጋር በስጦታነት እንዳበረከቱላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ቀሪ እስረኞች እስኪፈቱ እና ጥያቄዎቻችን እስኪመለሱ ድረስ ትግላችንን እቀጥላል ያሉ ሲሆን ርቀት ሳገድባቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ለኮሚቴዎቹ ያላቸውን አጋርነት ማሳየታቸውን መዘገባችብ ይታወሳል፡፤ በዚህ የዚያራ ጉዞ ወቅት ቃል በተግባቡት መሰረት በዛሬ እለት በከተማው የሚገኙ 30 የቲሞች እና አቅመደካማ ወላጅ ያሏችን ታዳጊ ህፃናት ሙሉ ዩኒፎርም በማሰፋት ተደስተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ታውቋል፡፡ በቀጣይም ለተማሪዎቹ አቅም የፈቀደውን ሁሉ በማድረግ የነገ ሃገር ተረካቢ ሙስሊሞችን ለማፈራት ጀምዓው በኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡