ወጣት ሙጂብ አሚኖ በሃሰት ምስክርነት ቃል በመስጠት በሚል ለቀረበበት 2ኛ ክስ የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ለሚዚያ 14 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው

ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 23/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኤልያስ ከድር መዝገብ በተከሰሱት የአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊሞች ላይ በሃሰት እንዲመሰክር የማዕከላዊ ደህንነቶች እና መርማሪዎች አስፈራርተውት ፍድ ቤት ቀርቦ እውነታውን በመመስከሩ በሃሰት በመመስከር ወንጀል በሚል ክስ የተመሰረተበት ወጣት ሙጂብ አሚኖ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተብሎ እንዲከላከል በተወሰነበት መሰረት ሰባራ ባበሩ በሚገኘው የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ የመከላከያ ምስክሩን ለፍርድ ቤቱ ማስደመጡ የሚታወስ ነው፡

አቃቤ ህጉ ወጣት ሙጂብ አሚኖ ፍርድ ቤት ቀርቦ በሃሰት የምስክር ቃሉን ሰጥቷል በማለት ክስ ያቀረበበት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ወንድም ሙጂብ አሚኖም ተገዶ በሃሰት ምስክር መባሉን በድጋሚ ለፍርድ ቤቱ ቢያስረዳም ፍርድ ቤቱ በቀረበበት ክስ ላይ እንዲከላከል በህዳር 24/2008 በተሰየመው ችሎት ውሳኔ እንዳስተላለፈበት የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ለሙጂብ አሚኖ የመከካለያ ምስክር ሆነው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ፣ የሙጂብ አሚኖ እህት ቀደሪያ አሚኖ፣ ኤልያስ ከድር፣ ፋሩቅ ሰኢድ፣አብዱልመጂድ አብዱልከሪም ፣ እህት ሃያተልኩብራ እና ሌሎች ወንድሞችም በችሎቱ መቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ተከሳሽ ሙጂብ አሚኖ ተገዶ በሐሰት እንዲመሰክር መደረጉን የሰው ምስክሮቹን ለፍርድ ቤቱ ካስደመጠ ቡሃላ ውሳኔ ለመስጠት ፍር ቤቱ ተለዋች ቀጠሮ ሰጥቶት የነበረ ሲሆን በዛሬው ችሎትም የምስክሮቹ ቃል ወደ ፅሁፍ ተገልብጦ አላለቀም በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ በድጋሚ እንደተሰጠው ታውቋል፡፡

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እየተከታተለ የሚገኘው ወንድም ሙጂብ አሚኖ ዛሬም ችሎት ቢቀርም የምስክሮች የሰጡት የድምፅ ማስረጃ ወደ ፅሁፍ ባለመገልበጡ ፣ድምፁ ወደ ፅሁፍ ተገልብጦ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 14 ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጠው የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ወንድም ሙጂብ አሚኖ ከዚህ ክስ በተጨማሪ በከድር መሀመድ የክስ መዝግብ በሽብር ወንጀል 19ኛ ተከሳሽ በመሆን የ 5አመት ከ 6 ወራት እስራት ቅጣት እንደተበየነበት ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ምስል