ወደዝዋይ ማረሚያ ቤት ተዘዋውረው ከነበሩት እስረኞች መካከል 300 የሚሆኑት ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት መመለሳቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 5/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተነሳውን እሳት ቃጠሎ ተከትሎ ወደ ዝዋይ እና ሸዋሮቢት እንዲዘዋወሩ ከተደረጉት እስረኞች መካከል በዝዋይ ማረሚያ ቤት ተወስደው ከነበሩት እስረኞች መካከል 300 የሚሆኑትን ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲመለሱ መደረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በጥቅምት 2/2009 ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እስረኞቹን የመለሷቸው ሲሆን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በዞን 2 ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል፡፡ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት የተመለሱትን እስረኞች በዞን ሁለት ውስጥ በልዩ ጥበቃ ስር እንዲታሰሩ መደረጉ የታወቀ ሲሆን ከማንም ታሳሪም ሆነ ከቤተሰባቸው ጋር እንዳይገናኙ መደረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ ታሳሪዎቹ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መዘዋወራቸውን የሰሙ ቤተሰቦች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለመጠየቅ በዛሬው እለት ሄደው የነበረ ቢሆንም መጠይቅ አትችሉም እንደተባሉ ታውቋል፡፡ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በነበረው በሶስት ዞን ውስጥ ታስረው የነበሩ እስረኞች በአሁኑ ወቅት በዞን 1 ውስጥ በአንድ ላይ ተፋፍነው ታስረው እንደሚገኙ ከዚህ ቀደም መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ከቤተሰብ ጋርም 15 ደቂቃ ባልበለጡ ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ እንዲገናኙ እየተደረገ መሆኑ ተገልፆል፡፡ ከዝዋይ ወደ ቂሊንጦ የተመለሱት ታሳሪዎች ቤተሰቦች ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ቤተሰበቸውን መጠየቅ እንዲችሉ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ታሳሪዎችን አሁን መጠየቅ እንደማይቻል እና ከሰኞ ቡኋላ ተመለሰው እንዲመጡ እንደተነገራቸቸው የታሳሪ ቤተሰቦች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡ በሸዋሮቢት የሚገኙት ታሳሪዎች ግን አሁንም በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን በምርመራ ሰበብ እየተሰቃዩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ወደ ሸዋሮቢት ቤተሰብ ለዚያራ በሄደ ቁጥር የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ቤተሰብን እያመናጨቋቸው እና እያንገላቷቸው መሆኑ የታወቀ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ በዱዓ እንዲያስተውሳቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡