ከእስር የተፈታው ወንድም ሷቢር ይርጉ  ከአመት በፊት ለኡመራ ጉዞ እንዳይሄድ ቦሌ ላይ  ፓስፖርቱ  ከተነጠቀ ወዲህ እስካሁን ፓስፖርቱ እንዳልተመለሰለት ተሰማ

 ፍትህ ራዲዬ/ ሰኔ 16/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኡስታዝ አቡበከር አህመድ የክስ መዝገብ ተከሶ እስራት ተበይኖበት የነበረው እና በ 2 አመት በፊት መስከረም ወር በምህረት በሚል እንዲፈቱ ከተደረጉት ሙስሊሞ መካከል አንዱ የሆነው ወንድም ሷቢር ይርጉ ባለፈው አመት    የኡምራ ጉዞ ለማድረግ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመጓዝ እንዳይችል ቦሌ ላይ በኢሚግሬሽን ሰራተኞች መታገዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ድምፀ ደርባባው፣የመድረኩ ፈርጥ ተብሎ የሚጠራው  ወንድም ሷቢር ይርጉ ከኮሚቴዎቻን ጋር የረጅም አመት እስራት ቅጣት ተበይኖበት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን መንግስት በራሱ ፈቃድ በምህረት በሚል እንዲፈታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

መንግስት በነፃ በምህረት እንዲፈታ ቢያደረግም ከሃገር እንዳይወጣ  ፓስፖርቱ ተወስዶበት እስካሁን እንዳልተሰጠው ተሰምቷል፡፡

ከአንድ አመት በፊት  ወንድም ሷቢር ይርጉ ለጉዞ የሚያስፈልጉ የኡምራ ቪዣ እና የአይር መንገድ ቲኬት በመቁረጥ በበረራ ሰአቱ ቦሌ አየር ማረፊያ በሰአቱ  ቢደርስም የቦሌ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች  ወንም ሷቢር ይርጉ ከሃገር እንዳይወጣ የታገደ በመሆኑ ኡምራ ለማድረግ መውጣት እንደማይችል እንደገለጸሉት እና የያዘውን የጉዞ ፓስፖርትም ደህንነቶቹ በመንጠቅ እስካሁን ድረስ አንሰጥም ብለው እንደከለከሉተ መሆኑ ታውቋል፡፡

ወንድም ሳቢር ይርጉ በወቅቱ ፓስፖርቱ ተቀምቶ ከኡምራ ጉዞ ቢሰናከልም የተወሰደበትን ፓስፖርት እንዲመለስለት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ደህንነቶቹ ፓስፖርቱን ሊመልሱለት ፈቃደኛ  አለመሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ደህንነቶቹ ፓስፖርቱን አንሰጥህም በሚል ለአንድ አመታት ያህል በመቆየታቸው በዘንድሮ አመትም ለኡምራ ጉዞ ሊሄድ አለመቻሉ ታውቋል፡፡

በዘንድሮ አመት በእስር ላይ የነበሩት ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ጨምሮ፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ኡስታዝ በድሩ ሁሴን እና ሌሎች ወንድሞችም የኡምራ ጉዞ ለማድረግ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መጓዛቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ቦሌ አየር መንገድ  ሲደርሱ መሄድ አትችሉም በሚል አለመከልከላቸው ተዘግቧል፡፡

ወንድም ሷቢር ይርጉ ለድፍን 1 አመታት ህጋዊ ፓስፖርቱን  የደህንት እና ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት  እንዲመልስለት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምክንያቱ ሳይገለፅለት  ፓስፖርቱን ለመመለስ ፈቃደኛ ሊሆኑለት አለመቻላቸው ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል