ከእስር የተፈቱት ኮሚቴዎቻችን ለኡምራ ስነ ስርአት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ማምራታቸው ተገለፀ
 

በመፍትህ ራዲዬ/ ሰኔ8/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ስከረም ወር በምህረት በሚል የተፈቱት ኮሚቴዎቻችን ለኡምራ ስራ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ማቅናታቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የኮሚቴውን ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ጨምሮ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ሼህ ሱልጣን አማን፣ዶ/ር ጀይላን ኸድር፣ኡስታዝ ሃይደር ከድር ፣ኡስታዝ በድሩ ሁሴን እና ሌሎች ወንድሞችም  ወደ ሳኡዲ አረቢያ በመጓዝ የኡምራ ስነ ስርአታቸውን ያከናወኑ ሲሆን ለ 4 አመታት ከእስር ካሳለፉ ቡሃላ ከሃገር ሲወጡ የጀመሪያው መሆኑ ተገልፆል፡፡

ከዚህ ቀደም ወንድም ሷቢር ይርጉ ለኡምራ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለማምራት ቦሌአለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከደረሰ ቡሃላ ከሃገር መውጣት አትችልም በሚል እንዲመለስ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በዘንድሮ አመት መሰል ክልከላ ይኖራል ተብሎ ቢሰጋም ኮሚቴዎቻችን በሰላም ከሃገር መውጣታቸው ተገልፆል፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ከእስር ከተፈታ ቡሃላ  ለህክምና ወደ ውጪ ሄዶ ለመታከም በተደጋጋሚ ቢፈልግም ደህንነቶች ከሃገር እንዲወጣ ባለመፈለጋቸው ሳይሳካ የቀረ ሲሆን አሁን ለኡምራ ስነ ስርአት ሁሉም ተፈቅዶላቸው ከሃገር መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡

ከተወሰነ ሳምንታት በፊት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በድጋሚ በማከላዊ ታስረው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በየቦታው እያካሄዱ ያሉትን የዳዕዋ እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ በደህንነቶች እንደተነገራቸው መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ተጨማሪ ምስል