ከሊቢያ ጠረፍ የተነሱ 239 ስደተኞች ሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው መሞታቸው ተዘገበ ፍትህ ራዲዬ/ጥቅምት 25/2009 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ከተለያዩ ሃገራት ወደ አውሮፓ ለመግባት ከሊቢያ የተነሱ ስደተኞች በሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ ስደተኞቹ ከሊቢያ ኮስት በመነሳት ወደ ጣልያን ለመጓዝ ጥረት ሲያደረጉ በነበረበት ወቅት ጀልባው ተገልብጦ ህይወታቸውን ማለፉ ተዘግቧል፡፡ በሁለት የተለያዩ ጀልባዎች ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 31 የሚሆኑ ስደተኞች በህይወት መትረፋቸው የተዘገበ ሲሆን በመጀመሪያው ጀልባ የነበሩ 29 ሰዎች ሲተርፉ ከሁለተኛው ጀልባ ውስት ደግሞ ሁለት ሴቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲዋኙ በህይወት አድን ሰራተኞች መትረፋቸው ተገልፆል፡፡ ሕይወታቸውን ያጡት ስደተኞች ከምዕራብ አፍሪካ እና ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሃገራት ዜጎች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ዝርዝር መረጃቸው እስካሁን አለመታወቁ ተዘግቧል፡፡ ከኤርትራ እና ከኢትዬጲየ በርካታ ስደተኞች በባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን የሚገቡ ሲሆን በርካቶችም በባህር ላይ ሰምጠው ህይወታቸው እንደሚያልፍ ይታወቃል፡፡ በዚህ አመት ብቻ 4220 የሚሆኑ ስደተኞች በባህር ሰምጠው መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን ከጊዜ ወደጊዜ አደጋው እየጨመረ ቢመታም ስደተኛው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በተያያ ዜናም በባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን የሚገቡ ስደተኞችን የጣሊያን ፖሊስ ስደተኞችን በኤሌክትሪክ ማሰቃያና በድብደባ ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃ ይፈጽምባቸዋል ሲል ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል፡፡ ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ መሰረት የጣሊያ የፖሊስ ሃይሎች በሊቢያ በኩል በባህር ወደ ጣሊያን የሚገቡ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ የማሰቃየት ተግባር ይፈጽማል ሲል ገልጿል። መግለጫው ከስደተኞችና ከጣሊያን ፖሊሶች ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ እንዳለው በድብደባ በኤሌክትሪክ ማሰቃያና በተለያዩ የቶርች ዘዴዎች ከፍተኛ ስቃይ በስደተኞቹ ላይ ይፈጸማሉ ሲል ኣጠንክሮ የፖሊሶቹን እኩይ ተግባር ኣውግዟል። ይህ ከፍተኘ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊከሰት የቻለው የኣውሮፓ ሕብረት ስደተኞቹ እንዳይገቡ በጣሊያን ላይ በሚያደርገው ጫና ሲሆን እጅግ ኣደገኛ የሆኑ ቶርቾች በሰው ላይ ይፈጸማሉ ሲሉ ሪፖርቱ አጋልጧል፡፡