ከሊቢያ ወደ ጣልያን በጀልባ ለመሻገር የሞከሩ 127 ስደተኞች ጀልባው ሰጥሞ ህይወታቸውን ማጣታቸው ተዘገበ
ፍትህ ራዲዬ/ የካቲት 21/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ከተለያዩ ሃገራት ወደ አውሮፓ ለመግባት ከሊቢያ የተነሱ ስደተኞች በሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው መሞታቸውን በስደት በሊቢያ የሚገኙ ምንጮች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡
ባሳለፍነው ሳምንት እሮብ ምሽት ከሊቢያ ጠረፍ ተነስተው ወደ ጣልያን ጉዞ የጀመሩ 127 ስደተኞች ጀልባው ተገልብጦባቸው ሁሉም ሰምጠው መሞታቸው ተዘግቧል፡፡
ሕይወታቸውን ያጡት ስደተኞች ከምስራቅ አፍሪካ እና ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሃገራት ዜጎች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ዝርዝር መረጃቸው እስካሁን ባይታወቅም በርካታ ኢትዬጲያውያን እንደሚገኙበትም ከሊቢያ መረጃውን ያደረሱን ስደተኞች ጠቁመዋል፡:
ከኤርትራ እና ከኢትዬጲየ በርካታ ስደተኞች በባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን የሚገቡ ሲሆን በርካቶችም በባህር ላይ ሰምጠው ህይወታቸው እንደሚያልፍ ይታወቃል፡፡
ባለፈው በፈረንጆቹ አመት ብቻ 4220 የሚሆኑ ስደተኞች በባህር ሰምጠው መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን ከጊዜ ወደጊዜ አደጋው እየጨመረ ቢመታም ስደተኛው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ይህ አሳዛኝ አደጋ በተሰማበት ወቅትም በርካታ ስደተኞች ወደ ጣልያን በጀልባ ለመሻገር ተራቸውን እየጠበቁ መገኘታቸው ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን የሚገቡ ስደተኞችን የጣሊያን ፖሊስ ስደተኞችን በኤሌክትሪክ ማሰቃያና በድብደባ ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃ ይፈጽምባቸዋል ሲል ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ከዚህ ቀደም ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ይህ ከፍተኘ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊከሰት የቻለው የኣውሮፓ ሕብረት ስደተኞቹ እንዳይገቡ በጣሊያን ላይ በሚያደርገው ጫና ሲሆን እጅግ ኣደገኛ የሆኑ ቶርቾች በሰው ላይ ይፈጸማሉ ሲሉ በሪፖርቱ ማጋለጡ ይታወቃል፡፡
ይህ ሁሉ ስቃይ እየተፈፀመም የስደተኛው ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ ወደላይ እያሻቀበ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን በሺወች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከሊቢያ እና ከግብፅ ወደ ጣልያን እና አውሮፓ ለመሻገር በህገ ወጥ ደላሎች ተራቸውን እየጠበቁ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡
የስደተኞቹን መስጠም ለፍትህ ራዲዬ መረጃውን ያደረሰው ወንድም አብረውት የነበሩት ወገኖች በባህር ሰምጠው መሞታቸው ቢያሳዝነው እና ቢያስደነግጠውም እሱም ተራው ሲደርስ በጀልባከመሻገር እንደማያፈገፍግ ለፍትህ ራዲዬ ገልፆል፡፡

ተጨማሪ ምስል