ከሃርቡ ከተማ በግፍ ታስረው በዋስ የተፈቱት ሙስሊሞች በፍትህ እጦት እየተንገላቱ እንደሚገኙ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ መጋቢት 21/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በሃርቡ ከተማ በግፍ ታስረው በከፍተኛ የዋስ ገንዘብ የተፈቱት ሙስሊሞች በፍትህ እጦት እስካሁን እየተንገላቱ መሆናቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
የሃርቡ ከተማ ሙስሊም ወጣቶቹ በህዳር 24/2008 በግፍ ለእስራት ተዳርገው የነበረ ሲሆን በኮምቦልቻ ከተማ ማረሚያ ቤትም ለብዙ ወራት በእስር ስቃይ ማሳለፋቸው ይታወሳል፡፤
እነዚህ ሙስሊሞች ከፍተኛ የገንዘብ ዋስ እንዲያሲዙ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን ጉዳያቸው እስካሁን እልባት ሳያገኝ ፍርድ ቤት እየተመላለሱ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡
ከ 15ሺህ እስከ 25ሺህ ብር የሚደርስ የዋስ ማሲያዣ ተጠይቀው ከእስር የተለቀቁት እነዚህ ሙስሊም ወንድሞች በደሴ ከተማ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እየተመላለሱ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
አቃቤ ህጉ ላቀረበባች ክስ ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ተደጋጋሚ ቀነ ቀጠሮ ሲሰጠው የቆየ ሲሆን እስካሁን ድረስ ሊያቀርብ አለመቻሉ ተዘግቧል፡፡
አቃቤ ህጉ ቀነ ቀጠሮ በደረሰ ቁጥር ምስክሮቼን አላገኘዋቸውም የሚል ምክንያት በማቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው እያደረገ ሲሆን በግፍ የተወነጀሉት የሃርቡ ከተማ ሙስሊሞችም ከሃርቡ ወደ ደሴ በመመላለስ ጉዳያቸውን ለመከታተል እየተንከራተተ መሆናቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ተጨማሪ ምስል