ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

 ታላቁ አሊም ሼህ አብዱልቃድር ወደ አኼራ መሄዳቸው ተዘገበ

ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 19/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞን በአብዳላ ወረዳ ነዋሪ የነበሩት የእድሜ ባለፀጋው ታላቅ አሊምሼህ አብዱልቃድ ወደ አኼራ መሄዳቸው ታውቋል፡፡

የ80 አመት አዛውንት የነበሩት የኢልም አባት ባደረባቸው የልብ ህመም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው እለት ሚያዚያ 20/2009 ሁሉም ወደማይቀርበት የአኼራ ጉዞ መጓዛቸው ተገልፆል፡፡

ሼህ አብዱልቃድር እድሜያቸውን በሙሉ ኢልም በማስተማር እና በርካታ ደረሶችን በማፍራት ዲንን ሲያስተምሩ የነበሩ አሊምመሆናቸው ተገልፆል፡፡

የቀብር ስነ ስርአታቸውም በሺዎች የሚቆጠር ህዝበ ሙስሊም እና ታላላቅ አሊሞች በሚገኙበት በነገው እለት ሚያዚያ 21 እንደሚፈፀም ታውቋል፡፡

ለሼህ አብዱልቃድ ማረፊያቸውን ጀነት እንዲያደርግላቸው ለቤተባቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብም መፅናናትን አላህ ይወፍቃቸው ዘንድ  እየተመኘን  ፍትህ ራዲዬ የተሰማትን ልባዊ ሐዘን መግለፅ ትወዳለች፡፡

ተጨማሪ ምስል