ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰረቱ ሞክረዋል በሚል  በእስማኤል በቀለ መዝገብ የተወነጀሉት 23 ሙስሊሞች ከ 3 አመት አስከ 15 አመት የሚደርስ እስራት ቅጣት ተበየነባቸው 
ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 9/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በእስማኤል በቀለ የክስ መዝገብ ለእስር በተዳረጉት 23 ሙስሊሞች ላይ ከ 3 አመት እስከ 15 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እንደበየነባቸው  የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
አቃቤ ህጉ በነዚህ 23 ሙስሊሞች ላይ የሽብር ክስ ያቀረበባቸው ሲሆን በኢትዬጲያ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት  ተንቀሳቅሰዋል ሲል ቅስ እንዳቀረበባቸው ታውቋል፡፡
ተከሳሽ ሙስሊሞቹ ከ 2004 እስከ 2014 ድረስ  ፊርቀቱል ናጂያ የተሰኘ  የሽብር ቡድን መመስረታቸውን አቃቤ ህጉ በክሱ ያቀረበ ሲሆን ከሽብር ክሱ በተጨማሪ በግድያ እና በዘረፋ ወንጀልም ተጨማሪ ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡
ተከሳሾቹ ከ2002  እስከ 2006  ባለው ጊዜ ውስጥም በወሊሶ፣ ወልቂጤ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ ከሚሴ፣ አዲስ አበባ እና በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች "ሃይማኖታዊ ዓላማን ለማራመድ በመንግስት መመራት የለብንም፣ ለመንግስት ግብር ሊከፈል አይገባም እና እስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን" በማለት ተንቀሳቅሰዋል በሚል እንደተወነጀሉ ይታወቃል፡፡
ክስ የተመሰረተባቸው ወንድሞች የአዲስ አበባ፣የኦሮምያ እና የደቡብ ክልል ነዋሪ የነበሩ ሙስሊሞች ሲሆኑ በነዚህ ክልሎች ላይም ዘረፋ ሲያካሄዱ ነበር በሚል ክስ እንደቀረበባቸው ታውቋል
አቃቤ ህጉ ለዚህ ላቀረበው ሃሰተኛ ክስ 41 የሐሰት ምስክሮችን እና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾችም የቀረበባቸውን ሃሰተኛ ክስ አለመፈፀማቸውን የተለያዩ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ መከላከላቸው ታውቋል፡፡
ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው   የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት  በሁሉም  ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስተላለፉን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን   በዛሬው እለት ግንቦት 9 በዋለው ችሎት  ከ 3 አመት እስከ 15 አመት የሚድስ እስራት እንደበየነባቸው ተዘግቧል፡፡
የክሱ ተጠሪ ወንድም እስማኤል በቀለ ከዚህ ክሱ በተጨማሪ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥለዋል በሚል የሐሰት ክስ ከተመሰተባቸው ወንድሞች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት የቅጣት ውሳኔ ያስተላለፈባቸው ተከሳሾች 1ኛ እስማኤል በቀለ፣ 2ኛ ሱልጣን አህመድ፣ 3ኛ አንሱ አብዱ ከድርን ጨምሮ 23 ሙስሊሞች ላይ ነው ።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎትም ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ይዘናል በማለት 1ኛ፣ 4ኛ፣ 18ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ተከሳሾችን ከ9 ዓመት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት  እንዲቀጡ ሲወስን ከ4ኛ ተከሳሽ በስተቀር ከ2ኛ እስከ 10ኛ ያሉ እና 13ኛ ተከሳሾች በ3 ዓመት ጽኑ እሰራት እንዲቀጡ መወሰኑ ተዘግቧል፡፡
ከ13ኛ ተከሳሽ ውጭ ከ11ኛ እስከ 21ኛ ያሉ ተከሳሾች በ4 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ መበየኑ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ምስል