ሰበር ዜና ፍትህ ራዲዬ
አህባሽ መራሹ መጅሊስ በየቦታው መስጂድ እና መድረሳ ለማሰራት እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኡስታዞች ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድባቸው ጠየቁ
ፍትህ ራዲዬ/ ሚያዚያ 26/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በመንግስት ተሹመው በግዳጅ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተጫኑት የፌደራሉ መጅሊስ አመራሮች በተለያዩ ክልሎች ስብሰባ በማካሄድ በኮሚቴዎቻችን እና በኡስታዞቻችን ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድባቸው እየጠየቁ መሆናቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
በሐዋሳ፣በሐረር እና በአዲስ አበባ ከተሞች በተካሄደው የአህባሽ መራሹ ህገ ወጡ መጅሊስ ጉባኤዎች ላይ ተቀዛቅዞ የነበረው የአክራሪዎች እንቅስቃሴ ዳግም እያንሰራራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙን መስጂድ እና መድረሳ እናሰራላቹሃለን በማለት እያታለሉ የፖለቲካ ቅስቀሳ እያደረጉ ናቸው ሲሉ መወንጀላቸው ታውቋል፡፡
ፀረ አክራሪነትን አስመልክቶ በተሰጡት የአህባሽ ስልጠናዎች ላይ መስጊድና መድረሳ እንሰራላችኋለን በሚል ሽፋን የሚካሄዱ ገንዘብ የማሰባሰብ ኮንፈረንሶች በአስቸኳይ ይቁሙልን ሲሉ አህባሾቹ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡
መጅሊስና መንግስት ሳያውቀው ሰባቱ ቤተእምነቶች ሳይነገራቸው የሚካሄደው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ህገወጥ ተግባር በመሆኑ መቆም አለበት ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በየቦታው የገቢ ማሰባሰቢ በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ሀገር ለማተራመስ የሚንቀሳቀሱ አሉና መንግስት አፋጣኝ እርምጃ ይውድባቸው ሲሉ መንግስትን አበክረው መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡
በአዲስ አበባ ባደረጉት ምክክር በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች መስጊድና መድረሳ እንሰራላችኋለን የቁርአን ምርቃት እናካሂዳለን በሚል ሽፋን የሚካሄዱ ኮንፈረንሶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ያሳሰቡ ሲሆን መንግስትም ሀገር ለማተራመስ በሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እርምጃ እንዲወሰድ አበክረው መጠየቃቸው ታውቋል፡፡
በደቡብ ክልል በሚገኙ መስጂዶችም ሙሉ ለሙሉ ከሙስሊሙ በመንጠቅ ለአህባሾች የሚያስረክብ ግብረሃይል ማቋቋማቸውን ያስታወቁ ሲሆን ከመስጂዱ አስተዳደር ጀምሮ ኢማሙ.ሙአዚኑ ፣ኻዲሞቹ እና ጥበቃዎች የአህባሽ አስተሳሰብን የማይከተሉ ከሆኑ ከመስጂዱ እንዲባረሩ መወሰናቸው በአቋም መግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
በመንግስት ከመዘጋት ተርፈው በአሁኑ ሰአት የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢስላማዊ ድርጅቶች እና ተቋሞችም ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ህገ ወጡ መጅሊስ የጠየቀ ሲሆን አዲስ ፈቃድ ለማውጣት ለሚፈልጉ ሁሉ የመጅሊሱ ፈቃድ ካልተሰጣቸው በስተቀር መንግስት ፈቃድ እንዳይሰጣቸው መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡

ህገ ወጡ መጅሊስ በህጋዊነት ሽፋን የዜጎችን የእምነት ነፃነት እየተጋፋ የሚገኝ ሲሆነ የአህባሽን አስተሳሰብ ያልተከተለውን ሁሉ አክራሪ እና ፅንፈኛ ነው በሚል ከመስጂድ እንዲባረር በማድረግ በግዳጅ የራሳቸውን ጠባባ አስተሳሰብ በሙስሊሙ ላይ በግዳጅ ለመጫን ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በህገ መንግስቱ ዜጎች  የሌሎችን መብት እስካልንነኩ ድረስ የፈለጉትን እምነት እና አስተሳሰብ የማራመድ ሙሉ ነፃነት  እንዳላቸው የተደነገገ ቢሆን አህባሽ መራሹ መጅሊስ ግን ከአህባሽ አስተሳሰብ ውጪ በኢትዬጲያ መኖር የለበትም በሚል የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት ከመናዳቸውም በተጨማሪ ሙስሊሙ በሃገሩ እምነቱን በነፃነት እንዳያራምድ በማገድ በየቀብሩ የሚልከሰከስ ፣በጫት እና በሱስ የደነዘዘ ለሃገር የማይጠቅም ብኩን  ዜጋ ለማድረግ እየጣሩ መሆናቸው ታውቋል

ተጨማሪ ምስል