በግብፅ እየተካሄደ ባለው ፍተሻ በርካታ ኢትዬጲያውያን ስደተኞች ለእስር መዳረጋቸው ተዘገበ
ፍትህ ራዲዬ/ የካቲት 23/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በግብፅ ለሃገሪቱ ደህንነት እና ጥበቃ በሚል እየተካሄደ በሚገኘው ድንገተኛ ፍተሸ በርካታ ኢትዬጲያውያን ለእስር መዳረጋቸውን የግብፅ የኢትዬጲያ ኮሚኒቲ አስታውቋል፡፡
በግብፅ እየተካሄደ የሚገኘው ፍተሻ ድንገተኛ እና ቦታ እና ሰአቱ የማይታወቅ ሲሆን ፍተሻው መኖሪያ ቤቶችንም ያካተተ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
በሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች እየተካሄደ ባለው ቤት ለቤት ፍተሻ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው እና ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር የተለያየ እክል ያለባቸው ኢትዬጲያውያን ስደተኞች መታሰራቸው ታውቋል፡፤
እየተካሄደ ያለው ፍተሻ ጊዜያዊ አለመሆኑን ኮሚውኒቲው ያስታወቀ ሲሆን መንገዶችና መኖሪያ ቤቶች በተደጋጋሚ እየተፈተሹ መሆኑን ገልፆል፡፡
ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ኮሚውኒቲው ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ስደተኛ እራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ማቅረቡ ተዘግቧል፡፡
የስደተኛ ወረቀት የሌላቸው፣ የጠፋባቸው እንዲሁም የመኖሪያ ፈቃድ ኢቃማ ያላሳደሱ ጉዳዩ ጠንከር ያለ በመሆኑ ለእስር ከመዳረግ እና ወደ ሃገር የመባረር ፈተናን ለመቋቋም ህጋዊ ሆነን ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ኮሚውኒቲው አስታውቋል፡፡
ሁሉም ስደተኛ ኢቃማ ካላሳደሰ እንዲያሳድስ እንዲሁም ያሳደሱት ደግሞ የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያቸውን ይዞ በመንቀሳቀስ ያለውን ፍተሻ እና ቁጥጥር ህጋዊነቱን በማስታወቅ እራሱን እንዲጠብቅ ኮሚኒቲው ማሳሰቡ ተዘግቧል፡፤

ተጨማሪ ምስል