በደቡብ ወሎ ዞን በደጋን ከተማ በሳርምድር መስጂድ አህባሾች በመስጂዱ ካላሰገደን መስጂዱን እናሻሽገዋለን በሚል እየረበሹ መሆናቸው ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ ሰኔ 8/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ በደጋን ከተማ አህባሽ መራሹ ህገ ወጡ መጅሊስ በከተማው ያሉትን ዋና ዋና መስጂዶች በግዳጅ ከተቆጣጠረ ቡሃላ በነሱ ቁጥጥር ስር ሊገባላቸው ያልቻለውን የሳርምድር መስጂድን መስጂዱን እናሽገዋለን በሚል ማስፈራሪያ መስጂዱን ለመንጠቅ እየተንቀሳቀሰ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በደጋን ከተማ ያሉት ትላልቅ መስጂዶች በአህባሽ መራሹ መጅሊሶች ተነጥቆ የአህባሽ ኢማሞች ተመድበውበት የአህባሽ አስተሳሰብ እየተሰበከበት እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የከተማው ህዝበ ሙስሊም በአህባሾች የተነጠቀውን መስጂድ በመተው ወደ ሳርምድር መስጂድ እየሄዱ እየሰገዱ መሆናቸው ተገልፆል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም ወደ ሳርምድር መስጂድ መሄዱ ያበሳጫቸው የአህባሽ መራሹ መጅሊስ አመራሮች ፊታቸውን ወደ ሳርምድር መስጂድ በማዞር ይሄ ሁሉ ሙስሊም እዚህ መስጂድ ለምን ይመጣል፣በመስጂዱ ሰላት የምናሰግደው እኛ ነን በማለት መስጂዱን እያወኩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ መስጂዱ የራሱ ኢማም አለው ሌላ ኢማም አያስፈልግም በማለት እየተቃወማቸው የሚገኝ ሲሆን በመስጂዱ ከሰላት በተጨማሪ የቁርአን እና ሃዲስ ትምህርት፣ዳዕዋ እና ሌሎችም ትምህርቶች እንዳይሰጡ መጅሊሱ እየከለከለ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በመስጂዱ ምንም ትምህርት እንዳይሰጥ የመስጂዱን ማይክራፎን ዝጉ በማለት የመጅሊሱ አመራሮች እየረበሹ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በመስጂዱ ዳዕዋ ማድረግ፣ቁርአን መቅራት እና ዲን መማማር የማይቆም ከሆነ መስጂዱን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያሻሽጉት እየዛቱ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በአህባሽ መራሹ መጅሊስ ሰበብ የሳር ምድር መስጂድ ለ ሁለት አመት ተዘግቶ መቆየቱ የተሰማ ሲሆን መስጂዱ በህዝበ ሙስሊሙ ትብብር ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር መስጂዱን በድጋሚ ለማዘጋጀት መጅሊሶች እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡ አህባሽ መራሹ መጅሊስ በየቦታው መስጂዶችን በመንጠቅ የራሳቸውን አስተሳሰብ ለማሰራጨት ጠንክረው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን የነሱን አስተሳሰብ ያልተቀበለውን ሁሉ ዋሃቢያ ነው በሚል ከመስጂድ ኢማምነት እንዲባረር እያደረጉ መሆናቸው ተገልፆል፡

ተጨማሪ ምስል