በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዬጲያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ
ፍትህ ራዲዬ/ የካቲት 16/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በደቡበ አፍሪካ ከዚህ ቀደም የውጪ ዜጎች ከሃገራችን ይውጡልን በሚል በተካሄደ የጥላቻ ዘመቻ በርካታ የውጪ ዜጎች መገደላቸው እና ንብረቶቻቸው መዘረፉ እና መውደሙ የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ተመሳሳይ የጥላቻ ቅስቀሳ በደቡብ አፍሪካ የተወሰኑ ቡድኖች እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል፤፤
ኣሁኑ ሰዓት በደቡብ ኣፍሪካ በተለይ ደግሞ በ ጋውተንግ ኣውራጃ የሚኖሩ : የደቡብ ኣፍሪካ ተወላጆች የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ በስደተኞችና ስደተኞችን ቀጥረው በሚያሰሩ የተለያዩ ድርጅቶች ላይ የፊታችን አርብ 24/02/2017 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እና በድርጅቶቹ ላይ ጥቃት ለማድረስ በማህበራዊ ሚዲያዎች ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ይህን የጥላቻ ዘመቻ ተከትሎ በደቡብ ኣፍሪካ በተለይ ደግሞ በ ጉተንግ ዲስትሪክት በፕሪቶርያና ጆሃንስበርግ ኣካባቢ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ከተለያዩ አገሮች ለመጡት ስደተኞች ከፍተኛ ፍርሃት እና ስጋት ውስጥ መግባታቸው ተዘግቧል፡፡
ይህን የጥላቻ ቅስቀሳ ተከትሎ ባለፉት ቀናቶች ዓርብ 17/02/2017 እና እሁድ 19/02/2017 የሃበሻ ኮሚኒቲ የደቡብ ኣፍሪካ የሰራተኞች ሶሻሊስት ፓርቲ ባዘጋጀው: ከሌሎች ከተለያዩ አገሮች የመጡ ድርጅቶች: ጋር በመሆን ስለኣንገብጋቢው የዜኖፎቢያ ጉዳይ መወያየቱን አስታውቋል፡፡
የሃበሻ ኮሚኒቲ : እንዲሁም ከኮንጎ ብራዛቢል: ከሶማልያ: ዚምባብዌ: ኡጋንዳ: ጋና እና ከተለያዩ ሌሎች አገሮች የመጡ ምሁራን: ነጋዴዎች: ጠበቃዎች : እና የኮሚኒቲ መሪዎች በስብሳበው የተካፈሉ ሲሆን በስደተኞች ላይ ሊከሰት ከሚችለውን ጥቃት ለመከላከል መንግስትና የመንግስት አካላት አንድ ላይ በመሆን ኣስፈላጊ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ: ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ወዳልተፈለገው ኣመጽ እንዳይሄዱ መንግስት አስቀድሞ ማድረግ ያለበትን ነገር እንዲያደርግ ለማሳሰብ ስብሰባው መካሄዱ ተዘግቧል፡፡
የደቡብ አፍሪካ መንግስት እና የጸጥታ ሃይሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘውን የጥላቻ ቅስቀሳ መረጃው እንደደረሰው ያስታወቀ ሲሆን ለሃገሪቱ ዜጎችም ሆነ ለውጪ ዜጎች በቂ ጥበቃ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሃበሻ ኮሚኒቲም ለመላው ሃበሻ በተለይ ደግሞ በጉቴንግ ክልል በፕሪቶርያና ጆሃንስበርግ: እንዲሁም በማሜሎዲ: ሾሻንጉቬ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዬጲያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳሰበ ሲሆን ጥቃቱ እንዲደረግ ቅስቀሳ እየተደረገ ያለበት ቀን ለ February 24 ቢሆንም: ከዛ በፊትም ሊጀምር እንደሚችል በማሰብም ከአሁኑ አስፈላጊ ጥንቃቄዎች እንዲያድርጉ ኮሚኒቲው አሳስቧል፡፡
የስጋት ቀጠና ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ያሉ ባለሱቆች በተቻለ መጠን ዕቃዎቻቸውን ቀስ በቀስ ለጥንቃቄ ቢያስወጡ ተመራጭ መሆኑን ኮሚውኒቲው ምክሩን የለገሰ ሲሆን በከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዬጲያውያንም ይህ ወቅት እስኪያልፍ ድረስ ለጥቃቱ ሰለባ ሊያደርግ ከሚችሉ ቦታዎች ከመገኘት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሩ መቅረቡ ተዘግቧል፡፡
ከደቡብ አፍሪካ ውጪ የሚገኘው ኢትዬጲያውያንም በስጋት ውስጥ ላሉት ወገኖች ከታሰበው ጥቃት አላህ አንዲታደጋቸው ዱዓ በማድረግ ሊያግዛቸው እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ተጨማሪ ምስል