በይግባኝ የእስር ቅጣቱ ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰለት የወልቂጤው ወንድም ጃፈር ዲጋ ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ ጥር 11/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት 10 የሚሆኑት ከእስር ሲለቀቁ ከወልቂጤ ከተማ የታሰሩት 3 ሙስሊሞች ደግሞ እስካሁን ሳይፈቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ ጠበቃቸው አዲስ መሐመድ ለፍትህ ራዲዬ መግለፆ የሚታወስ ሲሆን ወንድም ጃፈር ዲጋም በዚሁ መሰረት የተበየነበትን የ 3 አመት ከአራት ወር እስራት ሲጨርስ በዛሬው እለት መፈታቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው ለእስር ከተዳረጉት ሙስሊም ወንድሞች መካከል ሶስት የሚሆኑት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን የተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ ያት ከቀናት ቡሃላ ስለሚጠናቀቅ ቀሪዎቹ ሁለት ወንድሞችም ከእስር ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልፆል፡፡
በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ የወልቂጤ ከተማ ሙስሊም ወንድሞች ወንድም ፋሩቅ ሰኢድ እና ወንድም አብዱልአዚዝ ፈትሁዲን ሲሆኑ በቀጣይ ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁ ማረሚያ ቤቱ ለቤተሰቦቻቸው ማስታወቁ ተዘግቧል፡፡
ከ3 አመት ከ4 ወራት በላይ በማዕከላዊ፣በቂሊንጦ፣በዝዋይ እና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግፍ እስር ሲንገላታ የቆየው ወጣት ጃፈር ዲጋ በዛሬው እለት ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ እና ከናፈቀው ህዝበ ሙስሊም ጋር የተቀላቀለ ሲሆን መላው ሙስሊም ማህበረሰብ የጀመረው የጀነት ጉዞ በአንድ ጀመበር የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ ስንቁን ካሁኑ ሊያዘጋጅ ይገባል ሲል መልዕክቱን ከፍትህ ራዲዬ ጋር ባደረገው ቆይታ አስተላልፏል፡:
አልሃምዱሊላህ

ተጨማሪ ምስል