በይግባኝ የእስር ቅጣቱ ወደ 3አመት ከ 4ወር የተቀነሰለት ወንድም ኤልያስ ከድር ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉ ተገለፀ

ፍትህ ራዲዬ/ ታህሳስ 28/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ከተማ ተይዘው በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ 3 አመታት በላይ በግፍ እስር እና ስቃይ ያሳለፉት ወንድሞች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ተበይኖባቸው የነበረው የ 7 አመት ግፍ እስራት ወደ 3 አመት ከ 4 ወራት ዝቅ እንዲል በተወሰነላቸው መሰረት እንደሚፈቱ መገለፁ ይታወሳል፡፡

እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ወንድሞች መካከል የመዝገቡ ተጠሪ ወንድም ኤልያስ ከድር ከእስር እንደሚፈታ የሚገልፅ ደብዳቤ ከማረሚያ ቤቱ  በደረሰው መሰረት በዛሬው እለት ከእስር መፈታቱን  የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ዝቅ ካደረገላቸው ቡኋላ የተያዙበት ቀን ታሳቢ እየተደረገ ከእስር እንደሚለቀቁ ጠበቃቸው አዲስ መሐመድ ለፍትህ ራዲዬ መግለፆ የሚታወስ ሲሆን ወንድም ኤልያስ ከድርም በዚሁ መሰረት ከተበየነበት 3 አመት ከአራት ወር በተጨማሪ 5 ቀን እላፊ ታስሮ በዛሬው እለት መፈታቱ ተገልፆል፡፡

የታሳሪ ቤተሰቦች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ከሰሙ ወዲህ ወደ ማረሚያ ቤቱ በመሄድ በተደጋጋሚ ይፈታሉ ብለው ቢጠብቁም ከማረሚያ ቤቱ በኩል ምንም ፍንጭ ሊያገኙ ባመለመቻላቸው በትዕግስት ሲጠባበቁ መቆየታቸው ታውቋል፡

ከ3 አመት ከ4 ወራት በላይ በማዕከላዊ፣በቂሊንጦ፣በዝዋይ እና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግፍ እስር ሲንገላታ የቆየው ወጣቱ ኤልያስ ከድር በዛሬው እለት ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉ ተገልፆል፡፡

ወንድም ኤልያስ ከድር በሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶበትም ተስፋ ባለመቁረጥ የትዳር አጋር የምትሆነውን እህት መዲናን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ የኒካህ ስነ ስርአቱን ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን በእስር ጨለማ ውስጥ ሆኖም ሩቅ በማሰብ ኒካህ ማሰሩ ለብዙ ወጣቶች አርአያ እንደሆን ማስቻሉ ተዘግቧል፡፤

ለዲኑ ሲለፋ የነበረውን ወንድም ኤልያስ ከድር በዛሬው እለት ታህሳስ 28 የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቶት ከእስር መፈታቱ የተዘገበ ሲሆን  በእስር ላይ የቀሩትን ቀሪ ሙስሊሞችም ሙስሊሙ በዱዓ እንዲያግዛቸው ጥሪ መቅረቡ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ምስል