በወሎ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የአክፍሮት ሃይላት በተደራጀ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ የካቲት 21/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ስር በሚገኘው የወሎ ዩኒቨርሲቲ እና አካባቢው የአክፍሮት ሃይላት በተደራጀ ሁኔታ የማክፈር ዘመቻቸውን ለማካሄድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
የአክፍሮት ሃይላቱ በሰሜን ኢትዬጲያ በተለይም ሙስሊሙ በሚበዛበት በደቡብ ወሎ ዞን ብዙም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንዳልነበር የሚታወቅ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ መልኩ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል፡፡
የአክፍሮት ሃይላቱ የዩኒቨርሲቲውን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ታሳቢ ያደረግ የማክፈር ዘመቻ እያካሄዱ ሲሆን በአካባቢውን በነፃነት ሰበካቸውን እያካሄዱ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ሙስሊም ተማሪዎች በአህባሾች ከፍተኛ ፈተና እየገጠማቸው ባለበት በዚህ ወቅት የአክፍሮት ሃይላት ይህን ክፍተት በመጠቀም ሙስሊም ተማሪዎችን ሳይቀር ወደ ኩፍር ለማስገባት ስራዎችን እየሰሩ መሆኑ ታውቋል፡፡
የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ በነፃነት ዲኑን ለመማር እና ለማወቅ በአክራሪ ስም እየጠሸማቀቀ እና እየተከለከለ የሚገኝ ሲሆን የአክፍሮት ሃይላት ግን በተደራጀ መልኩ በአካባቢው በነፃነት ሰበካቸውን እያካሄዱ መሆኑን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
ሙስሊም ተማሪዎች በመስጂድ ውስጥ የአህባሽ ኢማምን ተከትለን አንሰግደም በሚል ሁለተኛ ጀምዓ ሰህዳቹሃል በሚል ለእስር እየተዳረጉ ባለበት በዚህ ወቅት የአክፍሮት ሃይላት ሙስሊሙ ድረስ ዘልቀው በመግባት ወንጌልን ለሙስሊሞች የተባለውን ዘመቻቸውን ለማስፋፋት እየሰሩ እንደሚገኑ ተዘግቧል፡፡
የአክፍሮት ሃይላት በከፍተኛ ደረጃ በደቡብ ክልል ስኬታማ መሆን የቻሉ ሲሆን አሁን ወደ ሰሜኑ ክፍል በመሄድ ሙስሊሙን ለማክፈር እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታውቋል፡፡
በኮምቦልቻ ከተማም የተለያዩ መፅሃፍቶችን በመበተን እና በማሳጨት ሙስሊሙን ለማደናገር እየተንቀሳቀሱ መሆኑ መዘገቡ የሚታወቅ ሲሆን የየኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ወጣቱን ክፍል ስልጠና በሚል አበል እየከፈሉ ሰበካቸውን እያካሄዱ መሆኑ ተዘግቧል፡፤
ሙስሊሙ ከመንግስት ጋር የገባበትን ግጭት እንደ ክፍተት በመጠቀም የአክፍሮት ሃይላት ሙስሊም በመምሰል፣መንዙማ የመሰሉ መዝሙሮችን በተለያዩ ቋንቋዎች በማዘጋጀት እና መፅሃፎችን በማሰራጨት ሙስሊሙን ከዲኑ ለማሶጣት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ምስል