በወልዲያ ሰላም መስጂድ የአህባሽ ኢማም ለተራዊህ ሰላት በሚል በህገ ወጡ መጅሊስ መመደቡ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ ግንቦት 15/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞንበወልዲያ ከተማ በሚገኘው በታላቁ ሰላም መስጂድ አህባሽ መራሹ መጅሊስ አዲስ የአህባሽ ኢማም መመደቡን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
ህገ ወጡ መጅሊስ ለረጅም ጊዜ የመስጂዱን ኢማም በአህባሽ ኢማም ለመቀየር በተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም በወልዲያ ከተማ ሙስሊሞች ጠንካራ ትግል የመስዱን ኢማም ለመቀየር ሳይችሉ መቅረታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከፊታችን እየመጣ የሚገኘውን የረመዳን ፆም በማስታከከል የተራዊ ሰላትን የሚያሰግዱ ኢማም በሚል ህገ ወጡ መጅሊስ አዲስ ኢማም መመደቡ ታውቋል፡፡
በህገ ወጡ መጅሊስ ለረመዳን የተራዊ ሰላት እንዲያሰግዱ በሚል የተመደቡት ሰው ሼህ አህመድ ሷዲቅ ሲሆኑ የወልዲያን ሙስሊሞች አዛ በማድረግ የሚታወቁ ሰው መሆናቸው ታውቋል፡፡
አህባሽ መራሹ መጅሊስ እኚህን ሰው የተራዊ ሰላት ኢማምእንዲሆኑ በሚል ቢመድባቸውዋና አላማው የረመዳን ፆም ሲጠናቀቅ ወደ ዋና ኢማምነት ለመቀየር ታስቦ እንደሆነምንጮች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን በተለይም በወልዲያ ከተማ አህባሾች መሰረታቸውን መትከል የተቸገሩ ሲሆን ያላቸውን ሙሉ ሃይል በመጠቀም ከተማዋን በአህባሽ አስተሳሰብ ለመበከል እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከኮምቦልቻ ከተማም አዳዲስ ወጣት የአህባሽ ሰባኪያንን ወደ ወልዲያ ከተማ እያስመጡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆንበረመዳን ወር የአህባሽን አስተምህሮ በየመስጂዱ ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተሰምቷል፡፡
ከዚህ ቀደም ከኮምቦልቻ ከተማ የተመዳ የአህባሽ ዳዒ በወልዲያው የሰላም መስጂድ ውስጥ ዳዕዋ ለማድረግ ሲሞክር በመስጂዱ ጀምዓ ተደብድቦ መባረሩ የሚታወስ ሲሆን በዘንድሮ አመት በፖሊሶች ድጋፍ የዚህ መሰሉን ዳዕዋ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆኑ ታውቋል፡፡
ለሰላም መስጂድ በሙስሊሙ ማህበረሰብ የተገዛን ምንጣፍ በመስጂዱ አይነጠፍም በሚል ከልክለው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በሙስሊሙ በደረሰባቸው ጫና መልሰው ፍቃድ መስጠታቸው የሚታወስ ነው፡፡
የወልዲያ ከተማ ህዝበ ሙስሊምየሰላምመስጂን ኢማም በአህባሽ ኢማም ለመተካት እየተደረገ ያለውን ሴራ በመገንዘብ መስጂዱን ከአህባሾች ለመታደግ በጋራ ሊቆም እንደሚገባ ጥሪ የቀረበ ሲሆን እስካሁን መስጂዱን ለመጠበቅ እየተደረገ ለው እንቅስቃ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ምስል