በወልዲያው ሰላም መድረሳ ለመጀመሪየ ጊዜ የዲን ትምህርት ቀርቶ አካዳሚክ ትምህርት ብቻ እንዲሰጥ መደረጉ ታወቀ

ፍትህ ራዲዬ/መስከረም 26/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ ከአወልያ ቀጥሎ ግዙፉ የሙስሊሙ ተቋም የነበረው  የወልዲያ መስጂዶች እና ትምህርት ቤቶች ማዕከል በህገ ወጡ መጅሊስ  እና በመንግስት ለአህባሾች እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ ተቋሙን የማዳከም ስራ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በማዕከሉ ስር የነበረውን የሰላም መድረሳ የዲን ትምህርት መስጠት እንዲያቆም በማድረግ የአካዳሚክ ትምህርት ብቻ እንዲሰጥ መደረጉን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ከ 1965 ጀምሮ የወልዲያን ሙስሊም ማህበረሰብ ሲያገለግል የቆየው ይህ ተቋም በርካታ ምሁንን እና ለሃገር የሚጠቅሙ ዜጎች ያፈራ  ሲሆን የዲን እውቀትም ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ በማስተማር በአካዳሚክም በመንፈሳዊ እውቀትም የበለፀጉ እንዲሆኑ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአህባሽ መራሹ መጅሊሽ በሰላም መድረሳ የሚሰጠውን ትምህርት የአካዳሚክ እና የዲን ትምህርቱ እንዲለይ ከመንግስት ጋር በመተባበር ማድረጉ የታወቀ ሲሆን የአካዳሚክ ትምህርቱን በህዝባዊ ኮሚቴው እንዲመራ በማድረግ የዲን ትምህርቱን ደግሞ በአህባሽ መራሹ መጅሊስ እንዲመራ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ለረጅም አመታት የዲን ትምህረቱን ሲያስተምሩ የቆዩ መምህራንን ለረጅም ወራት ደሞዛቸውን በመከልከል  ከስራ ማሰናበቱ የሚታወቅ ሰሆን በመድረሳው ላይም አዳዲስ የአህባሽ መምህራንን በመቅጠር የወልዲያ ሙስሊም ልጆቹን ወደነሱ እየላከ እንዲያስተምር ማስታወቂያ ማስነገራቸው  ይታወቃል፡፡

ሆኖም በዘንድ የ 2009  የትምህርት ዘመን የዲን ትምህርቱ እንዲቆም በማድረግ አካዳሚክ ትምህርት ቤቱ ብቻ ስራ እንዲጀምር ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

በርካታ ሙስሊሞች በሚኖሩባት የወልዲያ ከተማ ሙስሊም የሌለ እስኪመስል ድረስ  ትልቁን የሙስሊሞች ተቋም በማዳከም  መደበኛ የአካዳሚክ ትምህርት ብቻ  እንዲሰጥ ማድረጋቸው ለሙስሊሙ ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት መሆኑ የታወቀ ሲሆን የወልዲያ ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ ትምህርት የመማር መብታች በግዳጅ እንዲገድ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና በሰኡዲ አረቢያ የሚኖሩ የወልዲያው ሰላም መስጂድ ቤተሰቦች ለመድረሳው የሚሆን የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማደረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ለመማር ማስተማሩ የሚያግዙ በርካተ መፅሃፍትን፣ኮምፑተሮችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በድጋፍ መልኩ ማበርከታቸው የተዘገበ ሲሆን ለመድረሳ የላይብረሪ አገልግሎትም የሚሆኑ መፅሃፍቶች በስጦታነት ማበርከታቸው ተዘግቧል፡፡

በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊሞች እንደ አይን ብሌን የሚሳሱለተ ይህ ተቋም በአህባሾች እጅ ወድቆ  እንዲዳከም እየተደረገ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብ እስከመጨረሻው ድረስ ተቋሙን ተስፋ ሳይቆርጥ ሊታደግ እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡ ታውቋል፡፡