በኮምቦልቻ ከተማ የካሊድ መስጅድ ቅጥር ግቢ ለአሮጌባጃጆች መጠገኛ እና ማቆሚያነት መሰጠቱ ተዘገበ

ፍትህ ራዲዬ/ የካቲት 8/2009

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በምትገኘው በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የታላቁ ካሊድ መስጅድ ቅጥር ግቢ ለአሮጌ ባጃጅ እና መኪኖች መጠገኛ እና ማሰባሰቢያነት መሰጠቱን የአካባቢው ሙስሊሞች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

በቦርከና ዳር በምዕራብ በኩል የሚገኘው ይህ መስጂድ ለረጅም አመታት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግል የቆየ ሲሆን መስጂዱም በህዝበ ሙስሊሙ መዋጮ መገንባቱ ይታወቃል፡፡

አህባሽ መራሹ መጅሊስ በኮምቦልቻ የሚገኙ መስጂዶችን በጉልበት ከተረከበ ወዲህ መስጂዶች ተገቢውን የሆነ ክብር እየተነፈጉ ሲሆን ለረጅም አመታት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግል የነበረው የካሊድ መስጅድ ቅጥር ግቢም ለአሮጌ ባጃጆች መጠገኛ መሰጠቱ ተሰምቷል፡፤

ስለመስጂዱ የሚከራከር አካል ባለመኖሩ በመስጂዱ ቅጥር ግቢ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኘውን ቦታ ለአሮጌዳ ባጃጆች መጠገኛነት ሲሰጥ በምዕራብ በኩል ያለውን ቦታ ለተበላሹ መኪናዎች ማቆሚያ እና ለእስፖርት ማዘውተሪያነት መሰጠቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

የህዝበ ሙስሊሙን መስጂድ በማን አለብኝነት የአሮጌ ባጃጅ መጠገኛ እና ማጠራቀሚያ እንዲሆን ያደረገው አካል አህባሽ መራሹ መጅሊስ ይሁን የመንግስት አካል እስካሁን ግልፅ አለመሆኑ ታውቋል፡፤

አህባሽ መራሹ መጅሊስ ለኪሳቸው ማደለቢያነት በሚል መስጂዱን ሸንሽነው አከራይተውት ይሁን መንግስት ለልማት በሚል ወስዶት ይሁን የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩ የታወቀ ሲሆን ለረጅም አመታት ህዝበ ሙስሊሙን ሲያገለግል የቆየው የካሊድ መስጅድ በተዳከመ ሁኔታ ላይ መገኘቱ የአካባቢው ሙስሊሞችን ማሳዘኑ ተዘግቧል፡፤

ተጨማሪ ምስል