በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ ኢስላማዊ መፅሃፍት ቤቶች የተውሂድ ኪታቦችን እንዳይሸጡ በአህባሾች መከልከላቸው ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ መጋቢት 21/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ኢስላማዊ መፅሃፍት መሸጫ ቤቶች የተውሂድ መፅሃፍቶችን እንዳይሸጡ በአህባሾች መከልከላቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡
አህበሽ መራሹ መጅሊስ በኮምቦልቻ የሚደረገውን ኢስላማዊ እንቅስቃሴ ሁሉ በመንግስት ድጋፍ እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በከተማው ያሉ መስጂዶችን በጉልበት ከህዝበ ሙስሊሙ ከነጠቁ ቡሃላ አሁን ደግሞ የተወሰኑ ሁሉንም ኢስላማዊ መፅሃፍቶችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዳይሸጡ መከልከላቸውን ተሰምቷል፡
በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ ኢስላማዊ መፅሃፍት ቤቶች የተውሂድ መፅሃፍቶችን እንዳይሸጡ የተከለከሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል ኡሱሉ ሰላሳ፣ኪታቡ ተውሂድ፣ኢርሻድ፣አቂደቱል ዋሲጢያ፣ከሽፈ ሹብሃት እና ሌሎች የተውሂድ እና የሱና መፅሃፍቶች እንዳይሸጡ መታገዳቸው ተዘግቧል፡፡
እነዚህን መሰል መፅሀፎች ሲሸጥ የተገኘ ለፖሊስ ተጠቁሞበት በእስራት እንደሚቀጣ ያስፈራሩ ሲሆን መፅሃፍ ቤቱም ሊታሸግባቸው እንደሚችል እንዳስጠነቀቋቸው ተዘግቧል፡
ከተውሂድ መፅሃፍቶች በተጨማሪ በሃገራችን የሚገኙ የተለያዩ ተወዳጅ ዳዒዎች እና ኡለሞች ያቀረቧቸውን ሙሃደራዎች የያዙ ካሴቶች እና ሲዲዎች እንዳይሸጡ እንደተነገራቸው ታውቋል፡፡
ከመፅሃፍት እና ከሲዲ በተጨማሪ አፍሪካ ቲቪን አትመልከቱ በሚል በየመስጂዱ ቅስቀሳ የሚደረግ ሲሆን አፍሪካ ቲቪ የካፊሮች ቲቪ በመሆኑ ልትመለከቱ አይገባም በማለት በየመስጂዱ አህባሾች እንደሚያስተምሩ ተዘግቧል፡፡
በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኙ መፅሃፍት መደብሮች ውስጥ በአማርኛ የተተረጎሙም የተውሂድ እና የአቂዳ ኪታቦች መሸጥ የተከለከለ ሲሆን የአህባሽን አስተሳሰብ የሚያስተምሩ መፅሃፍት ብቻ በብዛት በከተማው መፅሀፍት መደብሮች እንዲሸጡ እየተደረገ መሆኑ ተገልፆል፡፡
አህባሾች በየመስጂዱ ኢልም የሚቀሩ ደረሶችን ዋሃቢ ካፊር በማለት በድንጋይ እየወገሩ ለማባረር እና ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በሃሰት በመወንጀልም ደረሶቹን በፖሊስ እንዲያዝ በማድረግ ከቂርአት ቦታዎች አንዲርቁ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ ምስል