በኮምቦልቻ ከተማ በተቅዋ መስጂድ ቂርዓት የሚቀሩ ደረሶችን ዋሃቢ ካፊር በማለት በሙህዲን የሚመሩት አህባሾች እያባረሯቸው መሆኑ ተገለፀ
ፍትህ ራዲዬ/ መጋቢት1/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ ኢልም በመቅራት ላይ የነበሩ ደረሶችን ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ከቂርአን ቦታ እንዲባረሩ እያደረጉ መሆናቸውን ከዚህ ቀም መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በርበሬ ወንዝ ወይንም ተቅዋ መስጂድ ተብሎ በሚጠራው መስጂድ ሲቀሩ የነበሩ ደረሶችን ዋሃቢ ካፊር በማለት ከቂርአት ቦታው እንዲርቁ እየተደረጉ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
በተቅዋ መስጂድ ሼህ አህመድ ከተባሉ አሊም ቂርአት ቀርተው ሲወጡ የነበሩ ደረሶችን አህባሾች ተከትለዋቸው በመውጣት ዋሃቢ ካፊር፣ከዋሃቢነቱ ካፈርነቱ በማለት እየተሳደቡ እና ድንጋይ እየወረወሩ ደረሶቹን ሲያባርሩ እንደነብ ተዘግቧል፡፡
የተቅዋ መስጂድ ከዚህ ቀደም በአህለል ሱናዎች እጅ የነበረ ጠንካራ የሱና መስጂድ የነበረረ ሱሆን በአሁኑ ወቅት በመንግስት ድጋፍ መስጂዱ ለአህባሾች በግዳጅ ከሙስሊሙ ተነጥቆ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡
መስጂዱ በኮምቦልቻ ከተማ ደረሶችን በማሸማቀቅ እና በማሳሰር በሚታወቀው ሙህዲን በሚባለው ፅንፈኛ የአህባሽ አቀንቃኝ ቡድኖች ቁጥጥር ስር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በመስጂዱ በሼህ አህመድ ቂርአት የሚቀሩ ደረሶችን ካፊሮች ናችሁ በማለት ድንጋይ እየወረወሩ ከመስጂዱ እንዲርቁ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡
ከዚህ ቀደም በኮምቦልቻ ከተማ ቀንደኛ የአህባሽ አቀንቃኝ የሆኑት አቶ ሙህዲን እና አቶ ኢብራሂም የሚባሉት ግለሰቦች ቂርአን በመቅራት ላይ የነበሩ በርካታ ደረሶችን ዋሃቢያ ናችሁ በሚል ከቂርአን ቦታ እንዲባረሩ እያስደረጉ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በኮንቦልቻ ከተማ ሸይኽ መሐመድ ያሲን በሚባሉ አሊም ላይ ነህው ሲቀሩ የነበሩ ቁጥራቸው 27 የሚደርሱ ደረሶችን ዋሃብያ ናችሁ በሚል ከቂርአን ቦታው እንዲባረሩ ማስደረጋቸውን መዘገባችን ይታወቃል፡፡
ሱንይ በመሆናቸው በብቻ ከቂርአን ቦታ ዋሃቢያ ናችሁ በሚል እንዲፈናቀሉ የተደረጉት ጣሊበል ኢልሞች ከቂርአት ቦታው ከመባረር በተጨማሪ አራት የሚሆኑትን በሃሰት በመወንጀል በፖሊስ እንዲያዙ አስደርገው እንደነበር የአካባቢው ምንጮች ለፍትህ ራዲዬ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
በፖሊስ እንዲታሰሩ ተደርገው የነበሩት አራት ሙስሊሞችም ወደ ፖሊስ ጣብያ ከተወሰዱ ቡሃላ በሰላም የተለቀቁ ሲሆን በኮምቦልቻ ከተማ አህለል ሱናዎች ቂርአት በሚቀሩበት ቦታ ሁሉ አህባሾች እንቅፋት እየሆኑባቸው መሆኑ ተገልፆል፡፡
የአህባሽን የተበላሸ አቂዳ የማይከተለውን ሙስሊም ዋሃቢያ በሚል የሚፈርጁ ሲሆን የአህባሽ አቂዳ እስካልተቀበላችሁ ድረስ ካፊር በመሆናችሁ ከነሳራ እና ከአይሁድ ለይተን አናያችሁም እንደሚሏቸው ነዋሪዎች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ በሚገኘው በሸይኽ መሐመድ ያሲን በሚሰጠው የነህዉ ትምህርት ላይ እንዳይቀሩ የተባረሩት እነዚህ ደረሶች በስነ ምግባራቸው እና በኢልማቸው የሚታወቁ ሲሆኑ ከቂርአት ቦታቸው ወደ ቤት ሲመለሱ እንኳን በቃላቸው ሃዲስ እየሃፈዙ የሚጓዙ እንደነበሩ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
አህባሾች በኮምቦልቻ ከተማ መስጂዶችን በመንግስት ድጋፍ በጉልበት ከሙስሊሙ ከነጠቁ ወዲህ የተበከለ አስተምህሮታቸውን በህዝቡ ላይ እየረጩ የሚገኝ ሲሆን የነሱን ብልሹ አቂዳ የማይከተለውን ሁሉ ካፊር በማለት ከመስጂድ እና ከቂርአት ቦታዎች እያፈናቀሉ መሆናቸው ተዘግቧል፡፤

ተጨማሪ ምስል